DW Amharic Telegram Channel

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

View in Telegram

Recent Posts

ጋዜጠኞች ሥራቸውን ከፍርሃት እና ጫና ነፃ ሆነው ሊሰሩ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ጠየቀ። ምክር ቤቱ ከተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስ እና የበሕል ድርጅት(UNESCO) ጋር በመሆን "ጋዜጠኝነት በአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ውስጥ" በሚል ሀሳብ የዓለም ፕሬስ ነፃነት ቀንን ዛሬ አክብረዋል። https://p.dw.com/p/4fhlc?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾@dwamharicbot
በጋምቤላ ክልል ከወር በፊት ጆር በተባለ ወረዳ ውስጥ ከደቡብ ሱዳን የተሻገሩ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ታፍነው ተወስደው ከነበሩት ህጻናት መካከል እስካሁን 10 ህጻናት መመለሳቸውን የክልሉ መንግስት ገልጸዋል፡፡ https://p.dw.com/p/4fhrr?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾@dwamharicbot
በኦሮሚያ ክልል በሞጆ ከተማና አዳማ ከተማ መካከል በተለያዩ ምእራፎች የሚገነባ የተባለው የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በይፋ የስራ ማስጀመር መርሃግብር ተከናወነ፡፡ ከአዲስ አበባ 65 ኪ.ሜ ርቃ በምትገኘው ሞጆ ከተማ አቅራቢያ የተለያዩ ኢንደስትሪዎች፣ መኖሪያ ቤቶች፣ ግዙፍ መንገዶች፣ የሎጂስቲክ ማእከላትና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ይገነቡበታል፡፡ https://p.dw.com/p/4fi7n?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾@dwamharicbot
በፀጥታ ምክንያት ስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ባልተደረገባቸው አራት ክልሎች ሊደረግ በታቀደው ቀሪ እና ድጋሜ ምርጫ እንደማይሳተፉ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጀት (መኢአድ) እና እናት ፓርቲ አስታወቁ። https://p.dw.com/p/4fhh5?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾@dwamharicbot
የሰላም ስምምነቱ በሙሉእነት እንዲተገበር ሀገራት ጫና እንዲፈጥሩ በትግራይ የሚገኙ የፖለቲካ ፖርቲዎች ለተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች ጥሪ አቀረቡ። የአስር ሀገራት ዲፕሎማቶች በመቐለ ተገኝተው ከክልሉ ፖለቲከኞች ጋር ተወያይተዋል። በመቀለ ከተገኙት መካከል በኢንግሊዝ ኤምባሲ አስተባባሪነት ከብሪታንያ የመጡ16 ስድስት ሃገራት ዲፕሎማቶች ይገኙበታል። https://p.dw.com/p/4fiXo?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾@dwamharicbot
የግንቦት 2 ቀን 2016 የዓለም ዜና
• እናት ፓርቲ እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጀት በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በሚቀጥለው ወር ከሚካሔደው የ6ኛው ዙር ቀሪ የጠቅላላ እና የድጋሚ ምርጫ ራሳቸውን አገለሉ።
• የፍልስጤምን የተባበሩት መንግሥታት አባልነት የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት እንዲቀበል የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ጠየቀ
• በደቡብ አፍሪካ ባለፈው ሰኞ በግንባታ ላይ የነበረ ሕንጻ ሲደረመስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 12 ደረሰ። ዛሬ አርብ ከፍርስራሹ ውስጥ የሦስት ሰዎች አስከሬን መውጣቱን የሀገሬው ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
• በቻድ ምርጫ ጄኔራል ማሕማት ኢድሪስ ዴቢ ማሸነፋቸው ሲሰማ ደስታቸውን ለመግለጽ አደባባይ ከወጡ ሰዎች መካከል የተወሰኑት ለፌሽታ በተተኮሰ ጥይት ሲገገደሉ በርካቶች ቆሰሉ።
• እስራኤል በራፋሕ የምታደርገው የእግረኛ ወታደሮች ዘመቻ ከፍተኛ ሰብአዊ አደጋ እንደሚያስከትል የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አስጠነቀቁ።
• የእስራኤል ወታደሮች ወደ ራፋሕ መጠነ-ሰፊ ዘመቻ ካደረጉ ጀርመን የአሜሪካን ፈለግ በመከተል የጦር መሣሪያ ማቅረብ ልታቆም እንደምትችል የጀርመን መከላከያ ሚኒስትር ፍንጭ ሰጡ።
• የሩሲያ ወታደሮች በዩክሬን ኻርካይቭ ግዛት አንድ ኪሎ ሜትር ዘልቀው መግባታቸውን የዩክሬን ጦር ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ገለጹ።
ዜናውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ፦
https://p.dw.com/p/4fj2f?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾@dwamharicbot
የማላዊ መንግሥት ስምምነቱ ለወጣት ዜጎቹ ጥሩ የሥራ እድል የሚፈጥር ብቻ ሳይሆን ሀገሪቱም ከውጭ ምንዛሬ ትርፋማ የምትሆንበት ነው ይላል። የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን እቅዱን ተችተዋል። https://p.dw.com/p/4fdJZ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾@dwamharicbot
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ከሰሞኑ ወደ ነቀምቴ ከተማ አቅንተው ከአራቱ የወለጋ ዞኖች ለተውጣጡ ነዋሪዎች ንግግር ማድረጋቸው ፤ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በእንግሊዘኛ ምህጻሩ RSF የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ኃይሎች ከሱዳን ብሄራዊ ጦር ጋር ወግነው እየተዋጉ ነው በማለት ያቀረበውን ክስ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አስተባብሏል። https://p.dw.com/p/4fiBX?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾@dwamharicbot
የግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና • በሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት ተሰደው አማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ተጠልለው የነበሩ 1 ሺ 300 ገደማ ያህል ስደተኞች መጠለያ ጣቢያውን ለቀው ለመውጣት መገደዳቸውን ተናገሩ።


• የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ታዬ ደንደአ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ብይን ሰጠ፡፡ ፍርድ ቤቱ በተከሳሹ ጠ,በቆች የቀረቡለትን የዋስትና ጥያቄዎች ሳይቀበለው ቀርቷል።

• ዓለማቀፉ የሰብአዊ መብት ተመልካቹ ቡድን ሁማን ራይትስ ዎች አር ኤስ ኤፍ የተሰኘው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ቡድን እና አጋሮቹን በዳርፉር የዘር ማጽዳት ወንጀል ከሰሰ ። የሰብአዊ መብት ተመልካቹ ቡድን ዛሬ ባወጣው መግለጫው ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በምዕራብ ዳርፉር በማሳሊት ጎሳ አባላት ላይ እየፈጸመ ያለው የጅምላ ግድያ መጠን «የዘር ማጥፋት » ሊሆን ይችላል።

• በደቡብ አፍሪቃ ጆርጅ ከተማ ውስጥ በተናደ ህንጻ ፍርስራሽ ስር ከተቀበሩ አራተና ቀናቸውን ያስቆጠሩ የ44 የግንባታ ሰራተኞችን በህይወት ለማግኘት ተስፋቸው እየተመናመነ መምጣቱን ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ ።

• ሁለት ወራት ገደማ ያስቆጠረው የኬንያ የሆስፒታል ሐኪሞች የስራ ማቆም አድማ አበቃ ።

• የእስራኤል ወታደሮች በራፋህ በመኖሪያ አካባቢዎች በታንክ የታገዘ ጥቃት መክፈታቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ ።

https://p.dw.com/p/4fg9t?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾@dwamharicbot
„የጠቢባን ማእድ“ የስደተኛዉ ማስታወሻ
„ጠላትህ እንዳይሰማ የምትፈልገዉን ሚስጢር ለጓደኛህ አትናገር። -የንግግር ሰዎች ተግባር ይርቃቸዋል። -ፍቅርን በጥሩ ዋጋ ሊገዛዉ የሚችል ነገር ቢኖር ፍቅር ብቻ ነዉ። -በቁጣ ከሚደሰት ይልቅ መሳቅ የሚወድ ሰዉ የበለጠ ጠንካራ ነዉ። -ዓይን ራሱን ሲያምን ጆሮ ግን የሰማዉን ያምናል“ ከ„የጠቢባን ማእድ የተወሰደ።
https://p.dw.com/p/4fexL?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾@dwamharicbot
ስለ ጠቅላይ ሚንስትሩ የወለጋ ጉብኝት አስተያየት
በትናንትናው ዕለት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ላለፉት አምስት ዓመታ በግጭት ሲናጥ ወደ ቆየው የምዕራብ ኦሮሚያ አካል ወለጋ ነቀምቴ ስታዲየም ተገኝተው ንግግር አሰምተው ነበር ። ወለጋን የልማት እና የብልጽግና ተምሳሌት እና ማዕከል ስለማድረግም ተናግረዋል ። አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ ፖለቲከኛ ግን ይጠራጠራሉ ።
https://p.dw.com/p/4fg0V?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾@dwamharicbot
የሰሜን ኢትዮጵያ ሕዝቦች የሰላም ትርዒት
በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት በሚታይባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ሕዝቦችን ለማቀራረብ ያለመ የተባለ የባህል ትርዒት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ሊካሄድ ነው ። አዘጋጆቹ የዚህ ትርዒት ዓላማ፥ በሰላም አስፈላጊነት እና በሕዝቦች መቀራረብ ላይ ያተኮረ ነው ብለዋል ።
https://p.dw.com/p/4ffVl?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾@dwamharicbot
የአቶ ታዬ ደንደዓ የፍርድ ቤት ውሎ
የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታና የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ ታዬ ደንደዓ በቅርቡ ከጠበቆቻቸው ጋር ችሎት ከቀረቡ በኋላ የክስ ዝርዝር ደርሷቸው ክሱም በንባብ ከተሰማ በኋላ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው በጠበቆቻቸው ጥያቄ ቀርቦ ነበር።
https://p.dw.com/p/4fg3P?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾@dwamharicbot
የኢትዮጵያ አብዮት ከ50 ዓመት በኋላ
ኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ ስርዓቷን ከመሰረቱ የቀየረውን አብዮት ካስተናገደች ዘንድሮ ሃምሳ ዓመታት ገደማ አልፏል፡፡ በዚህም አገሪቱ ባለፈችበት ስርዓተ መንግስታት ቢያንስ ከ50 ዓመታት በፊት ከነበረው ስርዓተ መንግስት የተለየን መንገድ ብትከተልም ዛሬም ድረስ ግን በስርዓቶች ዴሞክራሲያዊነት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች በርካታ ናቸው፡፡
https://p.dw.com/p/4ffli?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾@dwamharicbot
ፍትሕ ፈላጊዎቹ የኮሬ ልጃገረዶች
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን «ልጆቻችን ተጠልፈውብናል» ያሉ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ለማስመለሰም ሆነ ጠላፊዎቹን በሕግ ለመጠየቅ የአካባቢው አስተዳደር ተባባሪ ሊሆን አልቻለም አሉ ። «ከአንድ ወር በፊት በጠላፊዎች የተወሰደችው ልጄ አሁን ላይ የት እንዳለች እንኳን አላውቅም።»
https://p.dw.com/p/4ffu3?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾@dwamharicbot
ከ1300 በላይ የሱዳን ስደተኞች ከመጠለያ ጣቢያ ወጡ
በሱዳን ባለው ጦርነት ተሰድደው በኢትዮጵያ መተማ አካባቢ ከሚገኙ ስደተኞች መካከል በፀጥታን በምገብ አቅርቦት ችግር ምክንያት አንድ ሺህ ያክሉ ካሉባቸው የስደተኛ ማዕከላት መውጣታቸውን ተፈናቃዮች አመልክተዋል ።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ችግሮችን ለመፍታት እየተሠራ እንደሆነ ባወጣው መግለጫ ገልጧል፡፡
https://p.dw.com/p/4ffrQ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾@dwamharicbot

View in Telegram

Telegram Channel