Amhara Education Bureau Canali Telegram

Quality Education

View in Telegram

Recent Posts

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የዘጠኝ ወር እቅድ አፈፃፀሙን ከምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ደብረማርቆስና ደብረብሐን ከተማ አስተዳደር የዞንና ወረዳ ትምህርት አመራሮች፣ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ጋር ከግንቦት 7_8/2016 ግምገማ አካሂዷል።
በግምገማ መድረኩም የተከበሩ ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ሃላፊ ያስተላለፉት መልዕክት!!
👉 በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮች ትምህርትን በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ለማስቀጠል ያደረጉት ጥረት፣ ችግሩን ተቋቁሞ ለመስራት ያሳዩት ተነሳሽነት አበረታች ነው ብለዋል
👉 የትምህርት ተቋማትና አመራሮች 6ኛ፣ 8ኛ፣ 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማብቃት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተስፋ ሰጪ እንደሆኑ ተገልጿል
👉 6ኛ፣ 8ኛ፣ 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማብቃት በሚደረገው ጥረት ውስጥ በአካባቢው ያሉ ዩኒቨርስቲዎችና መምህራን ኮሌጆች የራሳቸውን ድርሻ እንዲወጡ በቅርበት መስራት ይገባል ተብሏል
👉 ትውልዱ በምክንያት የሚያምን በምክንያት የሚቃወም በሀሳብ ልዕልና የሚያምን እንዲሆን የተማሪዎች ስነምግባር ላይ መስራት እንደሚገባ ሃላፊዋ አብራርተዋል
👉 በአንድ አካባቢ የተገኙ ተሞክሮዎችን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ማስፋት ለትምህርት ስራ ውጤታማነት እጅጉን አስፈላጊ ነው ብለዋል
👉 ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ የሁሉም አካላት ርብርብ ወሳኝ ቢሆንም የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ሚና በተለይ መምህራንን በማበረታታትና ተማሪዎችን በሙሉ አቅማቸው እንዲያግዙ ግብዓት በማሟላትና ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ረገድ ትልቅ ሃላፊነት አለባቸው ብለዋል
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ለ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ልዩ ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋል ተባለ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ9ወር እቅድ አፈጻጸሙን ከማዕከላዊ ጎንደር፣ ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብ ጎንደር፣ ጎንደር ከተማ እና ወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ ዞን የዞንና ወረዳ ትምህርት አመራሮች፤ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ጋር ከግንቦት 5-6/2016ዓ.ም ድረስ በጎንደር ከተማ ግምገማ አካሂዷል፡፡
በግምገማ መድረኩ የቢሮው የ9 ወር ሪፖርት፣ የሱፐርቪዥን ቡድኑ የመስክ ድጋፍ ግብረመልስ እንዲሁም የስራና ተግባር ትምህርት የተመለከተ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በውይይቱ ተገኝተው ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት የትምህርት ቢሮ ም/ሃላፊ ወ/ሮ እየሩስ መንግስቱ እንደተናገሩት 6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማዘጋጀት ወርክ ሽቶችን በማዘጋጀት፣ ቤተመጽሐፍት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ክፍት በማድረግ ተማሪዎች እንዲያነቡና የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ እየሰሩ ያሉ ወረዳዎችንና ትምህርት ቤቶችን አመስግነዋል፡፡ በ2016ዓ.ም 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የአዳር ፕሮግራም ዘርግተው ተማሪዎች እንዲዘጋጁ እያደረጉ ያሉ ትምህርት ቤቶች ተሞክሮ በሁሉም አካባቢዎች መስፋት ያለበት እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ ከቀጣይ የትምህርት ስራ አኳያም ተማሪዎችን ለፈተና የማዘጋጀት ስራ እንደተጠበቀ ሆኖ ፈተናውን ያለምንም ችግር ለማጠናቀቅ ከማህበረሰቡ ጋር መግባባት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
በግምገማ መድረኩ ማጠቃለያ የሰጡት የትምህርት ቢሮ ም/ሃላፊ አቶ መኳንንት አደመ እንደተናገሩት አመቱን በሙሉ የምንሰራው የትምህርት ስራ የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል ላይ ትኩረት ያደረገ መሆን አለበት ብለዋል፡፡ የትምህርት ስራ ብቁና ተወዳዳሪ ትውልድ መፍጠር ላይ ትኩረት ማድረግ ነው ያሉት ሃላፊው ይህንንም ለማሳካት 6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን በልዩ ሁኔታ ድጋፍ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡
የትምህርት አመራሩ ትምህርትን በአደጋ ጊዜ ለማስቀጠል የሚያስችል አቅምና ተነሳሽነት ያለው፤ ነባራዊ ሁኔታን የሚረዳ መሆን አለበት ያሉት አቶ መኳንንት በቀጣይ ወራት በትኩረት መፈፀም ያለባቸውን ተግባራትም በዝርዝር አቅርበዋል፡፡


ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
በጎንደር ከተማ አስተዳደር የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም በይፋ ተጀምሯል።

በምገባ ማስጀመሪያ ፕሮግራሙ የተገኙት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ባዩህ አቡሃይ እንደገለፁት የምገባ ፕሮግራሙ ዛሬ ተጀምሮ የሚቀር ሳይሆን የበለጠ እየተጠናከረ የሚሄድ ፕሮግራም ነው።

የአንድ ሀገር እድገት ዋነው ትምህርት ላይ የሚሰራ ሰራ መሆኑን ያስታወሱት ከንቲባው ትውልድን በመቅረፅ መምህራን ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልጸዋል ።

የተጀመረው የምገባ ፕሮግራም ተጠናክሮ እንዲቀጥል መምህራን ፣ወላጆች የማይተካ ድርሻ እንዳላቸው ገልጸዋል ።

ህፃናት በአእምሮአዊና በአካላዊ ዳብረው ሀገረ ተረካቢ ትውልድ ለመገንባት የምገባ ፕሮግራሙ ፋይደው ከፍተኛ ነው ብለዋል ።
በምገባ ፕሮግራሙ የተገኙት ከንቲባው ተማሪዎች በትምህርታቸው ጎበዝ እንዲሆኑ አበረታትተዋል ።
አያይዘውም ተማሪዎች መምህራንና ወላጆቻቸውን እንዲያከብሩ አቶ ባዩህ አስገንዝበዋል ።

ፕሮግራሙ እንዲሳካ ላስተባበሩ አካላትና አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለሀብቶች ከንቲባው ምስጋና አቅርበዋል ።
በፕሮግራሙ ዘላቂነት እንዲኖረው ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ከንቲባ ባዩህ አሳስበዋል ።

የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ነፃነት መንግስቴ በበኩላቸው በ11ትምህርት ቤቶች 2ሽህ 954 ቅደመ መደበኛ ተማሪዎች በምገባ ፕሮግራሙ ተሳታፊ መሆናቸውን ገልጸዋል ።

የምገባ ፕሮግራሙ ከተማ አስተዳደሩ ከተለያዩ ባለሀብቶች ሀብት በማፈላለግ የተጀመረው መሆኑን ገልጸዋል ።

ምገባው እስከ በጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ የሚቀጥል ሲሆን በቀጣይ ዓመት ግን በተጠናከረ መንገድ እንደሚሰራ ገልጸዋል ።
የቅደም መደበኛ ተማሪዎችን የእቅድ አካል አድርጎ በቁርጠኝነት መሰራት እንደሚገባ አቶ ነፃነት ተናግረዋል ።
የምገባ ፕሮግራሙ ኮሜቴ ተዋቅሮ ሀብት የሚያመነጭና የምገባ ሂደቱን የሚከታተል መኖሩን አንስተዋል ።
ምገባ አንዱ የተማሪዎች መሰረታዊ ጉዳይ በመሆኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል ።

መቀንጨር ለትምህርት አሉታዊ ተፅዕኖ መኖሩን የገለፁት ምክትል ኃላፊው በተመጣጠነ ምግብ ችግር ምክንያት የሚመጣ በሽታ ነው።
የአእምሮ ዕድገታቸው የሚወሰነው በአመጋገብ ስርዓታቸው ስለሆነ ቁርስ ሳይበሉ የሚመጡ ተማሪዎች ስላሉ ምገባው አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል ።

የምገባ ፕሮግራሙ መካሄድ ለተማሪዎች ለትምህርት መሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ መኖሩን አቶ ነፃነት ገልጸዋል ።

ለቀጣይ ዓመት በ43 ቅደመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ላይ ምገባ ለማካሄድ ባለሀብቶች እንዲሁም በየደረጃው ያሉ አካላት የየድርሻቸውን ኃላፊነት በመውሰድ የዜግነት ግዴታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አቶ ነፃነት አሳስበዋል ።
ዘገባው የጎንደር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ነው
በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሙሉነሽ ደሴ የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉት መልዕክት
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሠላም አደረሳችሁ!
እንደ ሀገር በስነምግባሩ ምስጉን፣ ስራ ፈጣሪ ፣ቴክኖሎጅ አፍላቂ እና ተጠቃሚ፣ ሀገር በቀል እውቀትን ወደ ላቀ ከፍታ የሚያሳድግ ዜጋን ለማፍራት አዲስ ስርዓተ ትምህርት ቀርጸን ወደ ትግበራ ገብተናል። ለውጤታማነቱም ግብዓት ለማሟላት ጥረት እያደረግን ነው።
ለምሳሌ ቢሮአችን የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ለማሻሻል እና ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ነው። በክልሉ መንግስት፣ በትምህርት ሚኒስቴርና በአማራ ክልል በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ መቋቋም እና ግንባታ ፈንድ ጽ/ቤት /3R/ አማካኝነት 80 የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ የተጠናቀቁ ሲሆን ቀሪ 15 ትምህርት ቤቶችን ግንባታ በዚህ በጀት አመት ቀሪ ወራቶች ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው። 12 ትምህርት ቤቶችን በአውሮፓ ህብረት እንዲሁም 13 ትምህርት ቤቶች ደግሞ በጃይካ ትብብር ለማስገንባት ጥረት እየተደረገ ነው።
አዳሪ ትምህርት ቤቶች ያላቸውን ጉልህ ፋይዳና ጠቀሜታ ግምት ውስጥ በማስገባት ከክልሉ መንግስት በተመደበ 4 ቢሊዬን ብር በሚጠጋ በጀት 3 አዳሪ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ተጀምሯል። የእነዚህ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ልዩ ትርጉም አለው። የነገ የሀገራችንን እጣ ፈንታ በቴክኖሎጅ፣ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ከፍ የሚያደርጉ ታዳጊዎች የሚፈሩባቸው ተቋማት ይሆናሉ።
ሌላው የትምህርት ቤት ግብዓትን በማሟላት በኩል ከ470 ሚሊዬን ብር በላይ በሆነ ወጭ 50 ሽህ የሚጠጉ የመምህራን እና የተማሪዎች መቀመጫ ወንበሮች ተሰርተዉ ወደ የትምህርት ተቋማት በመሰራጨት ላይ ናቸው። በተጨማሪም በአማራ ክልል በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ መቋቋም እና ግንባታ ፈንድ ጽ/ቤት /3R/ አማካኝነት ከ44 ሽህ በላይ ኮምባይንድ ዴስኮች ተሰራጭተዋል። ለ60 ትምህርት ቤቶች ለኢ ለርኒግ አገልግሎቶች የሚውሉ 2ሽህ አንድ መቶ ኮምፒውተሮች ተሰራጭተዋል።
ለቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ከታተመው 14 ነጥብ 3 ሚሊየን መጽሐፍ ውስጥ 10 ነጥብ 7 ሚሊዮን መጽሐፍ ተሰራጭቷል:: ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ደግሞ ከትምህርት ሚኒስቴር ከተላከልን አራት ነጥብ አምስት ሚሊዮን መጽሐፍ ውስጥ ከ3 ሚሊዮን በላይ አሰራጭተናል::
በመንግስት፣ በአለም ምግብ ድርጅትና በሌሎች አጋሮች የጋራ ርብርብ ከ221 ሽህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ ተጠቃሚ ሆነዋል።
ለአጋር አካላት መልዕክት
ትምህርት ቤቶቻችን በሰሜኑ ጦርነት እና አሁን ባለው የክልላችን ሰላም እጦት ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸዋል። በርካታ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎቻችን ከትምህርት ገበታ ውጭ ናቸው፡፡ በመሆኑም ባለድርሻ አካላት ሁሉ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ፣ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባትና ግብዓት ለማሟላት በምናደርገው ጥረት ሁሉ ከጎናችን ቆማችሁ እንድታግዙን ጥሪ አቀርባለሁ።
ትምህርት በጊዜ የተገደበ ስራ ነው። በመሆኑም የ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ቀሪ ጊዜያችሁን በአግባቡ በመጠቀም ለፈተና ተዘጋጁ። መምህራን እና ወላጆችም ለእነዚህ ተማሪዎች አስፈላጊውን እገዛ እንድታደርጉላቸው እጠይቃችኋለሁ።
ለተሻለ ትውልድ ግንባታ በምናደርገው ትጋት ሁሉ ሰላም እጅግ አስፈላጊ ነገር መሆኑን ማህበረሰቡ እንደሚገነዘብ አምናለሁ። በመሆኑም በክልላችን የሰላም እጦት ምክንያት ልጆቻችን ከትምህርት ገበታቸው ውጭ እንዳይሆኑ፣ የተጀመሩ የትምህርት ቤት ግንባታዎች እንዳይስተጓጎሉ እና ጥራታቸው እንዳይጓደል ማህበረሰቡ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
መልካም የትንሳኤ በአል
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ
**************
የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ወይም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ እንዲሁም ከሐምሌ 9 እስከ 11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (ኦን ላይን) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።
በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30 እና ሐምሌ 01/2016 ዓ.ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 6 እና 7/2016 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርስቲ እንደሚገቡ ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
በክልሉ የአዳሪ ትምህርት ቤቶች ግንባታ እየተካሄደ መኾኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
==========================
በክልሉ የአዳሪ ትምህርት ቤቶች ግንባታ እየተካሄደ መኾኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡ የአዳሪ ትምህርት ቤቶች ውጤታማነት ተጨማሪ የአዳሪ ትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ እያደረገ መኾኑ ተመላክቷል፡፡
በአማራ ክልል በሚገኙ የአዳሪ ትምህርት ቤቶች በተከታታይ ዓመታት በተሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡ ይታወሳል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የጽሕፈት ቤት ኀላፊ ደግሰው መለሰ የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት የማሥፋፋት እና ደረጃቸውን የማሻሻል ሥራ እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል፡፡ በሰሜኑ ጦርነት በርካታ ትምህርት ቤቶች መጎዳታቸውንም አንስተዋል፡፡ አሁን ባለው የክልሉ ወቅታዊ ጸጥታ በርካታ ትምህርት ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል ነው ያሉት፡፡
በክልሉ ትምህርት ቤቶችን ለማደስ ጥረት እየተደረገ መኾኑን አስታውቀዋል፡፡ በትምህርት ቢሮው፣ በአማራ ክልል በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ጽህፈት ቤት፣ በአማራ ልማት ማኅበር፣ በትምህርት ሚኒስቴር እና በሌሎች አጋር አካላት በርካታ ትምህርት ቤቶችን ለማደስ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ አዳዲስ ትምህርት ቤቶችም እየተገነቡ መኾናቸውን አስታውቀዋል፡፡
በክልሉ መንግሥት ሦስት አዳሪ ትምህርት ቤቶች በሦስት ከተሞች ላይ እየተገነቡ መኾናቸውንም ገልጸዋል፡፡ የአዳሪ ትምህርት ቤቶቹ ሰቆጣ፣ ፍኖተ ሰላም እና ደብረ ታቦር ላይ እየተገነቡ መኾናቸውን ነው የተናገሩት፡፡ በየአካባቢዎች የትምህርት ቤቶች እድሳት እና አዳዲስ ግንባታዎች እየተሠሩ እንደሚገኙም አመላክተዋል፡፡
ግንባታው በተያዘለት ጊዜ እና ጥራት እንዲጠናቀቅ ሁሉም ሰላሙን በማረጋገጥ እና በመደገፍ ውጤታማ እንዲኾኑ ማድረግ ይጠበቅበታል ነው ያሉት፡፡ እየተገነቡ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በጥሩ ደረጃ ላይ መኾናቸውንም አስታውቀዋል፡፡
አዳሪ ትምህርት ቤቶች ውጤታማ ናቸው ያሉት ኀላፊው የክልሉ መንግሥት የተምህርት ቤቶችን ውጤታማነት በመገንዘብ ግንባታዎችን እያከሄደ መኾኑን ነው የተናገሩት፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም የአዳሪ ትምህርት ቤቶችን ለማስገንባት እንቅስቃሴ እያደረጉ መኾናቸውን ገልጸዋል፡፡
ለአብነት ጎንደር ዪኒቨርሲቲ ከዳሽን ቢራ ፋብሪካ ጋር በጋራ በመኾን የአዳሪ ትምህርት ቤት ለመሥራት የመሠረተ ድንጋይ ማስቀመጣቸውን ተናግረዋል፡፡ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እና ባለሃብቶች ተሞክሮውችን በመውሰድ የአዳሪ ትምህርት ቤቶችን ለማስፋፋት እንዲሠሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በአዳሪ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች ክልሉም ሀገርም የሚኮራባቸው እየኾኑ መምጣታቸውንም ገልጸዋል፡፡
የተጀመሩ የአዳሪ ትምህርት ቤቶች እንዲጠናቀቁ እና አዳዲስ የአዳሪ ትምህርት ቤቶች እንዲገነቡ ተቋማት እና ግለሰቦች ርብርብ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል፡፡ በብዙ መልኩ የተገጎዱ ትምህርት ቤቶችን ለማደስም ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
See more posts

View in Telegram

Telegram Channel
TeleSearch Telegram Search