Feta Daily News Telegram Channel

View in Telegram

Recent Posts

የሩሲያ የድሮን ድብደባ❗️

ሩስያ በዩክሬይን የፖልተቫ ግዛት ባካሄደችው የድሮን ድብደባ አንድ ምንነቱ ያልተገለጸ ፋብሪካ ማውደሙን የዩክሬይ ባለሥልጣናት አስታወቁ። በጥቃቱ አንድ ሰው ላይ የመቁሰል አደጋ ደርሷል ነው የተባለው። የዩክሩይን የአየር መቃወሚያ ምድብተኞች ሌሊቱን ለዛሬ አጥቢያ በተለያዩ ዞኖች ለድብደባ ከተሰማሩ 27 የሩስያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ወይም ድሮኖች 22ቱን መትተው መጣላቸውን አስታውቀዋል። በደቡባዊ የዩክሬይን ግዛት ማይኮሊቭ የተመታች አንዲት ድሮን በመኖሪያ መንደር ውስጥ በመውደቋ ከ10 በላይ የግል መኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት አድርሳለች። ይሁንና በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ሮይተርስ ዘግቧል።
ሀማስ የተኩስ አቁም ቅድመ ሁኔታ አስቀመጠ❗️

ሀማስ እስራኤል ጦሯን ከጋዛ ለማስወጣት ቁርጠኛ ካልሆነች ምንም አይነት ስምምነት እንደማያደርግ ገልጿል። እስራኤል ዘላቂ ተኩስ ለማቆም በግልጽ ቁርጠኝነቷን ካላሳየች እና ጦሯን ሙሉ በሙሉ ከጋዛ ካላስወጣች ሀማስ ምንምአይነት ስምምነት እንደማይፈጽም የፍልስጤሙ ቡድን ከፍተኛ ባለስልጣን በትናትናው እለት ተናግረዋል። ከአሜሪካ እና ከግብጽ ጋር ሀማስ እና እስራኤልን እያደራደረች ያለችው ኳታር እስራኤል ስምምነት ለመድረስ የሚያስችል ሙሉ የመንግስት ድጋፍ ያለው አቋም ይዛ እንድትቀርብ አሳስባታለች። የሀማስ ባለስልጣን ኦሳማ ሀምዳን ባስተላለፉት የቴሌቪዥን መልእክት ለዘላቂ ተኩስ አቁም እና ለእስራኤል ከጋዛ ጠቅልሎ መውጣት ዋስትና የማይሰጥ ስምምነት ማድረግ አንፈልግም" ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ባይደን በስደተኞች ላይ ጥብቅ ውሳኔ ሰጡ❗️

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከሜክሲኮ የአሜሪካን ድንበር በማቋረጥ በአሜሪካ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ቁጥር ለመገደብ የሚያስችል ትዕዛዝ አስተላለፉ።
በሕገ-ወጥ መንገድ የአሜሪካን ድንበር እያቋረጡ ጥገኝነት የሚጠይቁ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች ጉዳይ የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደርን ሲያስተች ቆይቷል። በአዲሱ ፕሬዝዳንታዊ መመሪያ መሠረት ባለስልጣናት ድንበር አቋርጠው የገቡ ሰዎች የጥገኝነት ጥያቄያቸው ሳይታይ ከአሜሪካ በኃይል እንዲያስወጡ ይፈቅድላቸዋል። ዋይት ሃውስ በመግለጫ እንዳለው ጉዳያቸው የሚመዘገቡ ሰዎች ዕለታዊ ኮታ ከተሟላ የተቀሩት ከአሜሪካ እንዲወጡ ይደረጋሉ። የበርካታ የድንበር ከተሞች ከንቲባዎች በተገኙበት ስነ-ስርዓት ላይ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አዲሱን መመሪያ በተመለከት ባደረጉት ንግግር “ይህ እርምጃ በድንበራችን አካባቢ ነገሮችን መልስን እንድንቆጣጠር ያስችለናል ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የሀማስ ታጋቾች መሞታቸው ተሰማ❗️

ሀማስ መስከረም 26/2016 ዓ.ም. በእስራኤል ላይ ከፈጸመው ጥቃት ጋር ቴኣይዞ ከታገቱ እስራኤላውን መካከል ተጨማሪ አራት ሰዎች መሞታቸውን የአገሪቱ ሠራዊት አረጋግጫለሁ ብሏል። እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ ኻን ዩኒስ በተባለ ስፍራ ላይ ወታደራዊ ዘመቻ እያከነወነች በነበረበት ጊዜ አራቱ ታጋቾች በጋራ መገደላቸውን የገለጸው ጦሩ አስክሬናቸው እስካሁን በታጣቂዎቹ እጅ እንደሚገኝ ጠቅሷል። የእስራኤል እና የብሪታንያ ጥምር ዜግነት ያላቸው ታጋቾቹ የ51፣ የ79፣ የ80 እና የ85 ዓመት ዕድሜ ላይ የሚገኙ እንደነበሩ ተነግሯል። የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ሪር አድሚራል ዳንኤል ሀጋሪ ጦሩ በቅርቡ በስለላ ክፍሉ አማካኝነት ባደረገው አሰሳ ታጋቾቹ መገደላቸው መረጋገጡን ገልጸዋል።
ትራምፕ የተደረገላቸው ከፍተኛ ድጋፍ

የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ታሪካዊ ነው በተባለለት የፍርድ ሂደት በቀረቡባቸው ክሶች ጥፋተኛ መባላቸውን ተከትሎ እጅግ የናጠጡ የሪፐብሊካን ፓርቲ ለጋሾች ከኋላቸው መሰለፋቸው እየተነገረ ነው።
በመጪው ዓመት ኅዳር በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩ ይሆናሉ የሚባሉት ትራምፕ፤ ለቀድሞ የወሲብ ፊልም ተዋናይት ስቶርሚ ዳንኤልስ አፍ ማዘጊያ የተከፈለውን ገንዘብ ለመደበቅ መዝገቦችን በማጭበርበር ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል።
ከጆ ባይደን እና ከዲሞክራቶች የገንዘብ የማሰባሰብ እንቅስቃሴ አንጻር ወደኋላ የቀሩት ትራምፕ፤ የፍርድ ውሳኔው በምርጫ ቅስቀሳ ዙሪያ አዲስ ጉልበት እንደፈጠረላቸው ታውቋል። ከውሳኔው በኋላ ባሉት 24 ሰዓታት ውስጥ ወደ 53 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ማሰባሰብ መቻላቸውን ዘጋርዲያን ዘግቧል።
አሜሪካ በተኩስ አቁሙ የተመድን ድጋፍ ጠየቀች❗️

አሜሪካ በእስራኤል እና በሀማስ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቃለች። ለጋዛው ጦርነት ዘላቂ መፍትሄን ለማበጀት ያግዛል በሚል በአሜሪካ የተዘጋጀው የተኩስ አቁም ጥያቄ ረቂቅ ሰነድ በተባበበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት እንዲደገፍ ዋሽንግተን መጠየቋን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡  ለተኩስ አቁም ስምምነት ሀሳቡ ተቀባይነት ተፈጻሚነት እና ስኬታማነት የምክር ቤቱ ድጋፍ ያሻኛል ያለችው ሀገሪቱ በቀጣይ ሁለቱ ወገኖች ወደ ተኩስ አቁም በሂደትም ወደ ጦርነት ማቆም ይመጡ ዘንድ ተመድ ያግዘኝ ብላለች፡፡
የካንሰር ክትባት❗️

በእንግሊዝ የሚገኙ ተመራማሪዎች የካንሰር በሽታን ለማከም ያስችላል ያሉትን የካንሰር ክትባት አስተዋውቀዋል።  ይህ ክትባት በሰው ልጅ የምርምር ሂደት ውስጥ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት እንደሆነም ነው የተገለጸው። የክትባቱ ህክምና  በመጀመሪያ የሚያተኩረው የአንጀት፣ የጣፊያ፣ ቆዳ፣ ሳንባ፣ ፊኛ እና የኩላሊት ካንሰር ህመምተኞች ላይ ነው ተብሏል:: ለካንሰር  ህመም ፈውስ ይሆናል የተባለው አዲሱ ክትባት የሰውነት በሽታ የመከላከል ስርዓትን በማጎልበት ላይ የተመሰረተ ህክምና ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ሮይተርስ በዘገበው አመልክቷል።
በአየር ትርዒት የተጋጩት ጄቶች❗️

በፖርቹጋል የአየር ትርዒት ላይ በተፈጠረ ግጭት የስፔን ዜግነት ያለው ፓይለት ህይወቱ ማለፉን የፖርቹጋል አየር ሀይል አስታውቋል፡፡ እንደ አየር ሀይሉ መረጃ፤ ከፖርቹጋል መዲና ሊዝበን ከተማ በ178 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምተገኘው የቤጃ ከተማ ላይ እየተካሄደ በነበረው የአየር ትርዒት ላይ አውሮፕላኖች ተጋጭተው አደጋ ተከስቷል፡ በግጭቱ አንደኛው አውሮፕላን ከቤጃ አየር ማረፊያ ክልል ውጭ ሲከሰከስ ሌላኛው አውሮፕላን ደግሞ በአየር ማረፊያው አቅራቢያ መከስከሱ ተገልጿል፡፡በአደጋው አንድ ፓይለት ህይወቱ ሲያልፍ ሌላኛው ፖርቹጋላዊ ፓይለት ክፉኛ ተጎድቶ ወደ ቤጃ ሆስፒታል መግባቱ ነው የተገለፀው፡፡ የፖርቹጋል አየር ሀይል በተፈጠረው ክስተት ማዘኑን ገልፆ በአደጋው ሕይዎቱን ላጣው አብራሪ ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝቷል፡፡
ተኩስ አቁሙ የገጠመው ተቃውሞ ❗️

የእስራኤል ሚኒስትሮች አገራቸው የተኩስ አቁም ለማድረግ ከተስማማች ጥምር መንግሥቱን እናፈርሳለን ሲሉ አሳስበዋል። ሁለት ቀኝ ዘመም የእስራኤል ሚኒስትሮች አገራቸው የተኩስ አቁም ለማድረግ ከተስማማች ጥምር መንግሥቱን አፍርሰን ስልጣን እንለቃለን ሲሉ መዛታቸው ነው የተገለጸው። ሁለቱ ሚኒስትሮች ይህን ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በጋዛ ያለውን ጦርነት ለማስቆም አማራጭ ያሉትን መፍትሄ ማቅረባቸውን ተከትሎ ነው። የፋይናንስ ሚኒስትር ቤዛሌል ስሞትሪች እና የብሔራዊ ደኅንነት ሚኒስትር አታማር ቤን-ጋቪር ሐማስ ሙሉ በሙሉ ሳይወገድ እስራኤል ወታደራዊ እርምጃዋን የሚያስቆም የተኩስ አቁም ስምምነት መድረስ የለባትም ማለታቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል።
ትራምፕ ቲክቶክ ከፈቱ❗️

ትራምፕ በስልጣን ዘመናቸው እንዲታገድ የወሰኑበትን ቲክቶክ ተቀላቅለዋል። ትራምፕ ትናንት ምሽት የቻይናውን ባይትዳንስ ኩባንያ የቪዲዮ ማጋሪያ መቀላቀላቸውን የሚያበስር ቪዲዮ በአዲሱ አካውንታቸው ለቀዋል። ቪዲዮውን ከ30 ሚሊየን በላይ ሰዎች የተመለከቱት ሲሆን፥ አዲሱ አካውንት በስአታት ውስጥ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ተከታይ ማፍራት ችሏል። በህዳር ወር በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሪፐብሊካን ፓርቲን ወክለው የሚፎካከሩት ትራምፕ ቲክቶክን መቀላቀላቸው ወጣት መራጮችን ለማግኘት እንደሚያግዛቸው ሮይተርስ ዘግቧል።
በቀይ ባህር ከባድ ጥቃት❗️

የየመን ሀውቲ ታጣቂዎች ቡድን በቀይ ባህር እና በህንድ ወቅያኖስ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚን፣ ዩኤ ዲስትሮየርን እና ሶሰት እቃ ጫኝ መርከቦችን ኢላማ ያደረጉ ስድስት ጥቃቶች መፈጸማቸውን በኢራን የሚደገፈው ቡድን ቃል አቀባይ ያህያ ሳርኤ በትናንትናው እለት ተናግሯል። አብዛኛው ህዝብ የሚኖርበትን የየመን ክፍል የተቆጣጠረው እና በኢራን የሚደገፈው የሀውቲ ሚሊሻ በመርከቦች ላይ ጥቃት የሚያደርሰው ከእስራኤል ጋር እየተዋጋ ላለው ሀማስ አጋርቱን ለማሳየት እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል። ቡድኑ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ የሆነችውን ኢሰንሀወርን በቀይ ባህር ሰማናዊ ክፍል በበርካታ ሚሳይሎች እና ድሮኖች አድርገናል ያለው ሳርኤ ይህ ጥቃት በ24 ሰአታት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የተፈጸመ ነው ብሏል።
35 ሺ የዩክሬን ወታደሮች መሞታቸው ተሰማ❗️

በሩስያ እና ዩክሬን መካከል የሚደረገው ጦርነት በግንቦት ወር ብቻ 35 ሺህ የዩክሬን ወታደሮች መሞታቸውን ሩስያ አስታወቀች። ኦክስፋም አሜሪካ የተሰኝው ግብረ ሰናይ ድርጅት ባወጣው መረጃ፣ በጦርነቱ በአማካይ 42 ሰዎች በቀን ህይወታቸው እንደሚያልፍ የገለጸ ሲሆን አጠቃላይ የንጹሀን ሟቾች ቁጥር ደግሞ 10ሺህ 500 ነው ብሏል።
የሩስያ የመከላከያ ሚንስቴር በበኩሉ ባወጣው መግለጫ፤ በግንቦት ወር ብቻ 35ሺ የዩክሬን ወታደሮች መሞታቸውን አስታውቋል፡፡
ጄፍ ቤዞስ የዓለም ቁጥር አንድ ባለሃብትነትን ተረከቡ❗️

ጄፍ ቤዞስ የዓለማችን ቁጥር አንድ ቢሊየነር ሆነዋል፡፡ ላለፉት ወራት የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋነት ደረጃን ተቆጣጥረው የነበሩት ፈረንሳዊ የፋሺን ኩባንየ ባለቤት በርናርድ አርናውልት በጄፍ ቤዞፍ ተበልጠዋል፡፡ በርናርድ አርናውልት በኩባንያዎቻቸው የቦርድ አመራር ውስጥ ልጆቻቸውን ማስገባታቸውን ተከትሎ የድርጅቶቻቸው የአክስዮን ዋጋ ቀንሷል። በአርናውልት አዲስ ውሳኔ ምክንያት የ6 ነጥ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ያጡ ሲሆን በአጠቃላይ አዲሱ ዓመት ከገባ ጊዜ ጀምሮ ገቢያቸው እየቀነሰ መምጣቱን ኢውሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡ ጄፍ ቤዞስ የሀብታቸው መጠን 205 ቢሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን ፈረንሳዊ አርናልውት ደግሞ 203 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም ሌላኛው አሜሪካዊ እና የቴስላ ኩባንያ ባለቤት ኢለን መስክ በ202 ቢሊዮን ዶላር በሶተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
በባይደን የቀረበው የጦርነቱ መፍትሔ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ በሶስት ምእራፎች የተከፈለ አዲስ የተኩስ አቁም አቅድ በዛሬው እለት ይፋ አደርገዋል።ጦርነቱ ማብቂያ ጊዜ ደርሷል ያሉት ፕሬዝዳንት ባይደን አዲስ ያቀረቡት እቅድ በጋዛ ተኩስ ለማስቆም እና የእስራኤል ታጋጆችን ለማስመለስ የሚያስችል ነው ብለዋል። በመጀመሪያው ምዕራፍ ለ6 ሳምንታት የሚቆይ የተኩስ አቁም ይደረጋል፤ በሁለተኛው እስራኤል እና ሃማስ ጦርነቱን በዘላቂነት ማቆም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ይደራደራሉ እንዲሁም ሶስተኛው ምእራፍ ለጋዛ ትልቅ የመልሶ ግንባታ እቅድ ያካትታል ሲሉ ፕሬዝዳንት ባይደን ተናግረዋል።
ትረምፕ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ መባላቸውን አወገዙ❗️

በኒው ዮርክ ከሕዝብ በተውጣጣ ችሎት በ34 የክስ ዓይነቶች ትላንት ጥፋተኛ እንደሆኑ የተወሰነባቸው የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ውሳኔውን አሳፋሪ ሲሉ አውግዘዋል። ትረምፕ ከውሳኔው በኋላ ከፍርድ ቤት ሲወጡ እንደተናገሩት፣ የእርሳቸውን ዕጣ ፈንታ የሚወስኑት በምርጫ ቀን ድምፅ ሰጪዎች መሆናቸውን አስታውቀዋል። የተጭበረበረ፣ ክብር የሌለው የፍርድ ሂደት ነው። እውነተኛው ፍርድ በኅዳር 5 ቀን ይሰጣል ሲሉ ትረምፕ መጪውን የምርጫ ቀን ማመልከታቸውን ዘጋርዲያን ዘግቧል።
ባይደን ሩሲያ እንድትመታ ፈቀዱ❗️

ፕሬዚዳንት ባይደን ዩክሬን የሩሲያን ኢላማዎች በአሜሪካ የጦር መሳሪያ እንድትመታ ፍቃድ መስጠታቸው ተሰምቷል። የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዩክሬን በካርኪቭ ግዛት አቅራቢያ የሚገኙ የሩሲያን ኢላማዎች አሜሪካ ባቀረበችው የጦር መሳሪያ እንድትመታ ፍቃድ መስጠታቸውን የአሜሪካ ባለስልጣናት ገልጸዋል።የሩሲያ ጦር በቅርብ ሳምንታት ውስጥ በድንበር አቅራቢያ በሚገኘው አካባቢ ላይ ባደረገው ድንገተኛ የማጥቃት ዘመቻ በካርኪቭ ግዛት ከፍተኛ ድል ማስመዝገቡ በሮይተርስ ዘገባ ተመላክቷል።
ሀማስ ጦርነቱ ካልቆመ አልደራደርም አለ❗️

ሀማስ ጦርነቱ እየቀጠለ ባለበት ሁኔታ በተጨማሪ ድርድሮች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንደሌላው ለአደራዳሪዎቹ በትናንትናው እለት ገልጿል።
ነገርግን ሀማስ እንደገለጸው እስራኤል ጦርነቱን የምታቆም ከሆነ ግን ታጋቾችን በእስረኞች መለወጥን ጨምሮ "ሙሉ ስምምነት" ለማድረግ ዝግጁ ነው።  በግብጽ እና በኳታር አደራዳሪነት ሲካሄድ የነበረው የእስራኤል እና የሀማስ የተኩስ አቁም ድርድር እንዳቸው ሌላኛቸው ያቀረቡትን ቅድመ ሁኔታ ውድቅ በማድረጋቸው እስካሁን አልተሳካም ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ትራምፕ ጥፋተኛ ተባሉ❗️

የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ታሪካዊ በሆነ የክስ ሂደት በጠቅላላ ጥፋተኛ ተብለዋል። ፕሬዝዳንቱ ከንግድ መዝገቦች ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በቀረቡባቸው 34 ክሶች በሙሉ ጥፋተኛ ተብለዋል። በአሜሪካ ታሪክ በሥልጣን ላይ ያለም ይሁን ከሥልጣን የወረደ ፕሬዝዳንት በወንጀል ክስ ጥፋተኛ ሲባል ትራምፕ የመጀመሪያው ናቸው። የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈባቸው ትራምፕ ሐምሌ 11/2016 ዓ.ም. የቅጣት ፍርድ ይተላለፍባቸዋል ተብሏል። ፍርድ ቤቱ ስድስት ሳምንታት በዘለቀው ችሎት ላይ ከ22 ሰዎች ምስክርነትን ሰምቷል። ከእነዚህ መካከል የቀድሞ የልቅ ወሲብ ተዋናይት ስቶርሚ ዳንኤልስ ትገኝበታለች ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
አሜሪካ የእስራኤል ጦርነት በቅርቡ አይቋጭም አለች❗️

የእስራኤል ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ዛቺ ሃኔግቢ ጦርነቱ ከዓመቱ መጨረሻ በፊት እንደማይጠናቀቅ ገልጸዋል። የአሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማቱ ብሊንከን እስራኤል ጋዛን የማስተዳደርና የማቋቋም ስትራቴጂ ይዛ ካልቀረበች ሃማስ ከዚህ የከፋ ነገር ከጦርነት በኋላ እንደገና ይነሳል ብለዋል። ብሊንከን በሞልዶቫ ዋና ከተማ ቺሲናዉ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ እስራኤል የሃማስን ሽንፈት ለማረጋገጥ፣ የጋዛን ፀጥታ እና አስተዳደር ወደነበረበት ለመመለስ እቅድ ማውጣቷ አስፈላጊ ነው ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል ስጦታ❗️

ሰሜን ኮሪያ ለጎረቤቶቿ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ የባላስቲክ ሚሳዔል እና የቆሻሻ ስጦታዎችን ትናንትና እና ዛሬ ልካለች። ሰሜን ኮሪያ ለጎረቤቷ ደቡብ ኮሪያ ልባዊ ስጦታ በሚል በተገለጸው ስጦታ ቆሻሻ የያዙ ፊኛዎችን የላከች ሲሆን፤ የጃፓን የስጦታ ድርሻ ደግሞ የአጭር ርቀት ባላስቲክ ሚሳዔሎች ናቸው ተብሏል። የጃፓን መንግስት በዛሬው እለት እንዳስታወቀው፤ ሰሜን ኮሪያ በዛሬው እለት የባላስቲክ ሚሳዔል ይሆናል ተብሎ የተገመተ መሳሪያ እንደተኮሰች አስታውቋል።
See more posts

View in Telegram

Telegram Channel
TeleSearch Telegram Search