Ethiopian Public Health Institute | የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት Telegram Channel

EPHI one of the oldest and known public health institutes in Africa. It is open 24/7 for public health emergency management through Emergency Operation Center.

For any information and help call 8335 or send us a message through ephieoc@gmail.com

View in Telegram

Recent Posts

ኢንስቲትዩቱ ከአፍሪካ የላብራቶሪ ሕክምና ማህበር (African Society for Laboratory Medicine [ASLM]) ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የአደገኛ ኬሚካል ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ላይ ያተኮረ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ፡፡
------------------------
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከአፍሪካ የላቦራቶሪ ሕክምና ማህበር (ASLM) ጋር በመተባበር ከሞሎኪውላር ላቦራቶሪዎች የሚመነጨው አደገኛ የኬሚካል ቆሻሻ (Guanidinium Thiocyanate [GTC]) አያያዝና አወጋገድ ላይ ያተኮረ ስልጠና ከኢትዮጵያና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ባለሙያዎች ለአራት ቀናት (ከግንቦት 20 እስከ 23/2016 ዓ/ም) የሚቆይ ስልጠና በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ስልጠና ማእከል መሰጠት ተጀመሯል፡፡
በዚህ ስልጠና መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሳሮ አብደላህ ስልጠናው እጅግ በጣም አሰፈላጊና ወቅታዊ መሆኑን ሲገልጹ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትም ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ገልጸዋል፡፡ እንዲሁም የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቱዩት በአሁኑ ወቅት የጤናው ዘርፍ ብቁ በሆነ የሰው ሀይል ማደራጀት አስፈላጊ በመሆኑ የኢንስቲቱዩቱ የስልጠና ማእከል በማደራጀት ከሀገር ባሻገር በምሰራቅ አፍሪካ ተመራጭ የስልጠና ማእከል ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻ ይህንን ስልጠና ከኢንስቲትዩታችን ጋር በመተባበር ያዘጋጁትን US-CDCን እና ASLMን ያመሰገኑ ሲሆን, እዲሁም በዚህ የስልጠና ተሳታፊ ለሆኑት የላቦራቶሪ ባለሞያዎች በዚህ ስልጠና የምታገኙትን እውቀትና ክህሎት ተጠቅማቹህ ጠንካራ የሆነ የአደገኛ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርዓት ወደ መጣችሁበት ስትመለሱ ተግባራዊ እንድታደርጉ በማለት አሳስበዋል፡፡
በኢንስቲትዩቱ NIPN-ኢትዮጵያና በሲዳማ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ፣ የስርዓተ ምግብ ተግባራትን የማከናወን ስራን ያጠናክራል
------------------------------
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (ኢሕጤኢ) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ ህብረተሰቡ በአገር አቀፍ ደረጃ ተገቢውን የተመጣጠነ ምግብ ተጠቃሚ ለማድረግ የሁሉም የሚመለከታቸው ሴክተሮች በትብብር መስራታቸው አስፈላጊ መሆኑን አስገነዘቡ። ዶ/ር መሳይ ይህንን የገለፁት ዛሬ በኢሕጤኢ ብሔራዊ መረጃ ፕላትፎርም ለሥነ-ምግብ ((National Information Platform for Nutrition) (NIPN-Ethiopia)) እና በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (ሲሕጤኢ) መካከል ትስስር ለመፍጠር እንዲሁም ስራዎችን ወደ ክልሉ ለማውረድ (ካስኬድ) የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ በተፈራረሙበት የምክክር አውደ ጥናት ላይ ነው።
ዋና ዳይሬክተሩ የመግባቢያ ሰነዱን ከተፈራረሙ በኋላ እንደተናገሩት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚደርሱ የጤና ችግሮችን ለመቅረፍ ብዙ እንደሚጠበቅብን እና ፖሊሲ ለመቅረፅ የሚቅርቡ መረጃዎችን ምንጮችን አስተማማኝነት ለማረጋገጥ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መሰብሰብና መተንተን እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
"NIPN-ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ስር ከሥነ-ምግብ ጋር የተገናኙ የፖሊሲ ጥያቄዎችን በማጠናከርና በመተንተን ጉልህ ሚና እየተጫወተ ሲሆን እንዲሀገር የተቀየሱ የስነ-ምግብ ስትራቴጂዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ለማጠናከር ይረዳል። ስለዚህ የመግባቢያ ሰነዱ በሥነ-ምግብ ላይ ፖሊሲውን እና ስትራቴጂውን የመተግበር አስፈላጊነትን ያጠናክርዋል፣” ብለዋል ዶ/ር መሳይ።
ዋና ዳይሬክተሩ የጤና እና የስነ-ምግብ ፕሮጀክቶችን ወደ ህብረተሰቡ ለማድረስ የክልል ጤና ቢሮዎች እና የህዝብ ጤና ተቋማት ወሳኝ ሚናን አጽንኦት ሰጥተውታል። ለማንኛውም ተመሳሳይ ፕሮጀክት ስኬት የእነዚህ ዘርፎች ተሳትፎ ወሳኝ ነው፣” ሲሉም ጨምረው ተናግረዋል።
"የጤና ፕሮጀክቶችን ስኬት ለማጎልበት NIPN/EPHI ከክልል ጤና ቢሮዎች እና የህዝብ ጤና ተቋማት ጋር በትብብር መስራት አስፈላጊ ነው። ከእነዚህ አካላት ጋር በቅርበት መስራት የአመጋገብ እና የጤና ውጥኖች የታለመላቸው ተጠቃሚዎችን በብቃት እንዲደርሱ ለማድረግ ወሳኝ ነው። በየክልሉ ያሉ የህዝብ ጤና ተቋማትን አቅም በማጎልበት ስራቸውን በጥራትና በብቃት እንዲወጡ ማስቻል የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ኃላፊነት ነው ብለዋል ዶ/ር መሳይ።
የ EPHI ዋና ዳይሬክተር ከሲህጤኢ ጋር የተፈረመው ሁለተኛው የካሳዲንግ ስምምነት ፍሬያማ እንደሚሆን ያላቸውን እምነትና በክልሎች ደረጃ እየተከናወኑ ያሉትን ተግባራት የኢትዮዽያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መደገፉን ይቀጥላል፣" ብለዋል.
የሲሕጤኢ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት ኢንስቲትዩታቸው በካስኬዲንጉ የተቀመጡትን ዓላማዎች ለማሳካት በትጋት እንደሚሰራ ነው።
"በክልላችን ውስጥ የ NIPNን ተግባራት ለማከናወን ሲሕጤኢ ከብዙ ተወዳዳሪዎች መካከል መመረጡ ለኛ ትልቅ ዕድል ነው። ሲሕጤኢ የሚጠበቀውን ያህል ለመስራት ዝግጁ መሆኑን በድጋሚ ማረጋገጥ እፈልጋለሁ፣” ብለዋል፣ ዶ/ር ዳመነ።
የምክክር አውደ ጥናቱን የከፈቱት ኢሕጤኢ የምግብ ሳይንስና ስነ-ምግብ ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ማስረሻ ተሰማ የNIPN/EPHI ውጥኖችን በመላ ክልሎች ማስፋፋትና ያለውን መተግበር ያለውን ጠቀሜታ ያብራሩ ሲሆን ዶ/ር አረጋሽ ሳሙኤል የ NIPN-ኢትዮጵያ አስተባባሪ ደግሞ የNIPN-ኢትዮጵያን ሚና እና አላማ ገልፀው ፕሮጀክቱ ከሚንቀሳቀሰባቸው ዘጠኝ ሀገሪት ውስጥ በአፈፃፀም ኢትዮዽያ ከመጀመሪያዎች ሦስቱ ውስጥ መሆኗን አስረድተዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘም ዶ/ር ታደሰ ዘርፉ ስለ ፕሮጀክቱ ካስኬዲንጉ ለምን እንዳስፈለገ ጠቅልል ያለ ፅሑፍ አቅርበዋል።
NIPN/EPHI ከዚህ ቀደም ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር ተመሳሳይ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ስራውን በሚጠበቀው መልክ እንዲተገበር ማድረጉ የሚታወስ ነው።
EPHI and Ethiopian Artificial Intelligence Institute signed MoU to foster impactful partnership
A Memorandum of Understanding (MoU) was signed between the Ethiopian Artificial Intelligence Institute (EAII) and the Ethiopian Public Health Institute (EPHI), marking a remarkable step towards fostering collaboration and innovation. The MOU aimed at creating cooperation between EAII and EPHI on infrastructure development, joint research, surveillance, and intelligence on health and nutritional problems, and devising joint AI-based solutions for health care programs and facilitations to generate evidence that can inform policy and decision-making.
Dr. Messay Hailu, the Director General of EPHI, expressed his optimism that the collaboration between EPHI and EAII will propel significant advancements in digitalizing disease and health event surveillance systems. This partnership is poised to leverage predictive and prescriptive big data analytics, along with fostering decision science endeavors, paving the way for transformation in public health functions. The Director General also underscored the profound impact this collaboration will have on bolstering healthcare systems, and the partnership represents a significant step forward in the realm of public health, heralding collaboration and innovation in the fight against emerging health challenges. By generating evidence through advanced analytics, both institutes aim to enable early detection and swift responses to health threats. Crucially, the Director General also emphasized the commitment of both institutes to stringent data protection protocols, leveraging AI-driven solutions to ensure the privacy and accuracy of critical health information.
 Dr. Taye Girma, Deputy Director General of EAII, said, "This partnership marks the beginning of a collaborative effort to leverage AI technology in optimizing healthcare services, health information management systems, surveillance, evidence generation, and use." He also emphasized the commitment to carrying out the Memorandum of Understanding efficiently and expressed optimism that it would provide positive results. " He disclosed plans to quickly form a technical team to operationalize the objectives stated in the Memorandum of Understanding and guarantee timely action to achieve the objectives. "The establishment of a dedicated technical team will expedite the implementation process and bring the envisioned benefits to fruition at the earliest," he said.
 Dr. Masresha Tessema, director of EPHI's Food Science and Nutrition Research Directorate, outlined the Institution’s historical development, emphasizing its critical role in advancing research projects, strengthening the capacity of sub-national public health institutions, and delivering trustworthy, evidence-based data to decision-makers. He presented an overview of the institute's activities, which include public health emergency management, research, the laboratory systems and existing collaborations between regional and international institutes. Dr. Masresha also emphasized the institution's remarkable achievements in this domain, citing its instrumental role in promptly detecting and responding to emerging health threats.
Deputy Director Generals, Dr. Getachew Tollera and Dr. Saro Abdella, directors, and team leaders underscored the significance of the collaborative endeavor, signaling a collective commitment to leveraging innovation and expertise to address pressing challenges in public health.
በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲካሄድ የነበረዉ በአፈር ንክኪ የሚተላለፉ የአንጀት ጥገኛ ትላትሎች እና የብልሃርዚያ በሽታዎች የዳሰሳ ጥናት ዉጤት ይፋ ሆነ
----------------------------
በየኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የባክቴሪያል፣ፓራሲቲክ እና ዞኖቲክ በሽታዎች ምርምር ዳይሬክቶሬት ከጤና ሚኒስቴር እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲካሄድ የነበረው በአፈር እና በውሃ ንክኪ የሚተላለፉ የአንጀት ጥገኛ ትላትል /STH/ እና የብልሃርዚያ /SCH/ በሽታዎች ላይ ሲካሄድ የነበረው የዳሰሳ ጥናት ውጤት /national reassessment result dissemination / ከግንቦት 14 እስከ 16/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ጎልድን ቱልፕ ሆቴል በተካሄደው አዉደ ጥናት ይፋ ተደረገ።
በአዉደ ጥናቱ ማስጀመሪያ ስነ ስርአት ላይ የጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶ/ር ሕይወት ሰለሞን ለአወደ ጥናቱ ተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ሲያስተላልፉ፣ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ አዉደ ጥናቱን በይፋ ከፍተዋል።
አዉደ ጥናቱ የተካሄደዉ የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ፣ ከጤና ሚኒስቴር የተለያዩ የትኩረት የሚሹ የሐሩራማ በሽታዎች ባለድረሻ አካላት፣ ከThe END Fund፣ ከUnlimit Health፣ ከ ለንደን ስኩል ኦፋ ሀይጅን ና ትሮፒካል ሕክምና ትምህርት ቤት፣ ከሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደር ተወካዮችና የተለያዩ የባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት ነበር።
በዚህ አውደ ጥናት ላይ በበሽታዎቹ ዙሪያ በየክልሎች የተደረገዉ ዝርዘር ጥናታዊ ጽሁፍ በየኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ቀርቦ በሽታዎቹን ለመከላከልና መቆጣጠር ወደፊት መወሰድ ያለበት የህክምና ስትራቴጂ ሁሉም የክልል ጤና ቢሮዎች እንዲተገብሩ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም፣ በክልሎችና በጤና ሚኒስቴር ሲሰራ የነበረዉ በሽታዎቹን የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ አበረታች መሆኑን ከአዉደጥናቱ ዉጤትና ከተሳታፊዎች አስተያየት ለመረዳት ተችሏል፡፡
በአዉደ ጥናቱ ማጠቃለያ ላይ በየኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የባክቴሪያል ፣ፓራሲቲክ እና ዞኖቲክ በሽታዎች ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይርክቴር የሆኑት ዶ/ር ገረመዉ ጣሰዉ እንደተናገሩት በአፈር ንክኪ የሚተላለፍ የአንጀት ጥገኛ ትላትል /STH/ እና የብልሃርዚያ /SCH/ በሽታዎችን ለመከላከል ለመቆጣጠርና ብሎም ለማጥፋት ለጤና ሴክቴር ብቻ የሚተዉ ሥራ ሳይሆን የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍና ማህብረሰቡ የራሱን ጤና እራሱ እንዲጠብቅና እንዲንከባከብ በማስተማርና በማስተባበርም ጭምር ነዉ ብለዋል። በማከልም በሽታዉን ለማጥፋት በሚደረገዉ ጥረት ዉስጥም የተሻለ የመመርመሪያ ዘዴ እንዲኖር በማድረግ በመረጃ ልዉዉጥ አጠቃቀምና አያያዝ ላይም የክልሎችን አቅም ማጎልበት አይተኬ ሚና ስላለዉ አጋር ድርጅቶች በዚህ ዙሪያም ድጋፋቸዉን መቀጠል እንዳለባቸዉ አሳስበዉ ለዚህ አዉደ ጥናት መሳካት አሰተዋጾ ያደረጉትን አጋር ድርጅቶች The End Fund, Unlimit Health, WHO, የጤና ሚኒስቴር አመራሮችና የስራ ክፍሎች የክልል ጤና ቢሮዎች የአወደ ጥናቱ ተሳታፊዎችና አሰተባበሪዎችን በማመስገን አወደ ጥናቱ ከሶስት ቀን ቆይታ በኃላ መጠናቀቁን አብስረዋል፡፡
See more posts

View in Telegram

Telegram Channel
TeleSearch Telegram Search