Addis Maleda – አዲስ ማለዳ Telegram Channel

ዜና ከምንጩ

View in Telegram

Recent Posts

መደበኛ ፓስፖርት ለማግኘት እየተንገላታን ነው ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ

ዓርብ የካቲት 29 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ለሁለት ዓመታት በጦርነት ውስጥ የቆየው ትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ እስካሁን አገልግሎቱ ያልተጀመረ ሲሆን አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው ከአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ሐዋሳ፣ ጅማ፣ ድሬዳዋ፣ ጅግጂጋ፣ አሶሳ፣ ሆሳዕና እና ሌሎችም ከተሞች ፓስፖርት የፈለጉ ዜጎች እየተቸገርን ነው ብለዋል።

ደላሎች በኢሚግሬሽን አካባቢ ለሚገኙ የፌደራል ፖሊስ አባላት የተወሰነ ብር እንዲሰጥና ቅድሚያ ማግኘት እንዲቻል ያመቻቻሉ የሚለው ቅሬታ አቅራቢ... https://addismaleda.com/archives/36279
———
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት እንዲሁም ሃሳብ፣ አስተያየት እና የሚዲያ ሽፋን ጥቆማ ለማድረስ
የአዲስ ማለዳ ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይቀላቀሉ፤ ለሌሎችም ያጋሩ!

Telegram | Facebook | YouTube | X | www.addismaleda.com | 0961414141

“መሬታችን በመንግስት እየተወሰደብን ነው” የምዕራብ ሸዋ ዞን ናኑ ወረዳ ነዋሪዎች

ዓርብ የካቲት 29 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ናኑ ወረዳ ልዩ ስሙ ናኑ ጉዲና ቀበሌ 01 ‘መዳሎ’ አካባቢ “ግብር የምንከፍልበት እና ሕጋዊ ካርታ ያለውን ንብረታችንን ከ2 ሄክታር መሬት በላይ መያዝ አትችሉም በማለት የተቀረውን ሰብስበው ላመጧቸው ወጣቶች እየሰጡ መሆኑን” ጠቁመዋል።

እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ፤ የአካባቢው ሚሊሻዎች ከባድ መሳሪያ በመታጠቅ አጅበው ያመጧቸው ወጣቶች ደግሞ “ስለት እና መሰል መሳሪያዎችን በማስያዝ ማህበረሰቡን እያስፈራሩና ባስ ሲል... https://addismaleda.com/archives/36275

ኢትዮጵያ ለአገር ውስጥ መጓጓዣነት የሚያገለግሉ ሁለት ጀልባዎችን ገዛች

ዓርብ የካቲት 29 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ መንግስት ለአገር ውስጥ የውሃ መጓጓዣ የሚሆኑ ሁለት ጀልባዎችን መግዛቱን የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አስታወቀ።

ከአንድ ዓመት በፊት ድርጅቱ 'ጣናነሽ 2' እና 'መደመር' የተሰኙ ሁለት ጀልባዎች ግዢ እየተፈጸመ እንደነበር ተገልጾ ነበር። የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሁለት ጀባዎች መጫናቸውን ቢገልጽም የ'ጣናነሽ 2' ስም ተጠቅሶ አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

ከሦስት ሳምንታት በኋላ ጅቡቲ ወደብ እንደሚደርሱ ከተገለጹት ሁለት መርከቦች አንዱ 'ጣናነሽ 2' 38 ሜትር ርዝመት ሲኖረው በአንድ ጊዜ 188 ሰዎችን የመጫን አቅም እንዳለው የተገለጸ ሲሆን በ'አሶሳ መርከብ' ተጭና ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ መጀመሯን አዲስ ማለዳ ከድርጅቱ ያገኘችው መረጃ ያሳያል።

በ1942 ዓ.ም ጣሊያናዊያንና ኢትዮጵያዊያን ግለሰቦች ተሰባስበው ጣና ላይ መሰረታቸውን አድርገው የፈጠሩት 'ናቪጋ ጣና' የባህር ትራንስፖርት ድርጅት፤ በሕዳር ወር 2015 ከኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ጋር ከጣና ሐይቅ በመጀመር በአገር ውስጥ የውሃ ጉዞ አገልግሎት ለመስጠት ተዋህደዋል።

የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር "የንጹሀን ሶማሌዎች ደም እየፈሰሰ ነው፤ የእኛ ጊዜም ይመጣል" አለ

ዓርብ የካቲት 29 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) በኦጋዴን መሬት የንጹሀን ሶማሌዎች ደም እየፈሰሰ ነው በማለት አጭር ማሳሰቢያ አወጣ።

ኦብነግ ትላንት ምሽት በኤክስ ገጹ እንዳስታወቀው "በኦጋዴን በሚፈሰው የሶማሌዎች ደም የሚደሰቱ አካላት ይኖራሉ" ብሎ፤ "የእኛ ጊዜም እንደሚመጣ ያስታውሱ" ሲል ማንነታቸውን ያለጠቀሳቸውን አካላት አሳስቧል።

"ይቅርታ ወደ እኛ ቢመጣ እንኳን በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሕዝባችን ላይ ጉዳት ያደረሱትን ፈጽሞ አንረሳውም" ሲልም የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር ገልጿል።

ኦብነግ በወታደራዊ ክንፉ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለ24 ዓመታት ገደማ በትጥቅ ውጊያ ሲፋለም ከቆየ በኋላ በጥቅምት ወር 2011 ግንባሩ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት በመፈራረም ውጊያ አቁመዋል።

በቅርቡ ከአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሃላፊዎች ጋር የመከረው ኦብነግ፤ ከሰሞኑን በሶማሌ ክልል እየተካሄደ ያለው "የእቃና የእንስሳት ወረራ፣ በሲቪል ሰዎችና ተሽከርካሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት በጽኑ አወግዛለው" በማለት አስታውቆ ነበር።

ድርጊቶቹ ኢኮኖሚያዊ መረጋጋትን በእጅጉ የሚጎዱ እና ሰብዓዊ እና ሕጋዊ መብቶችን የሚጥሱ በመሆናቸው በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እና ጭንቀት አስከትለዋል ያለው ኦብነግ፤ የፌደራል ባለስልጣናት የህግ የበላይነትን እንዲያከብሩ እና የሶማሌ ክልል ህዝቦችን ፍትሃዊ የሕግ አያያዝ እና ጥበቃ እንዲያረጋግጡ ጥሪ አቅርቦ ነበር።
———
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት እንዲሁም ሃሳብ፣ አስተያየት እና የሚዲያ ሽፋን ጥቆማ ለማድረስ
የአዲስ ማለዳ ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይቀላቀሉ፤ ለሌሎችም ያጋሩ!

Telegram | Facebook | YouTube | X | www.addismaleda.com | 0961414141
#ተጨማሪ#updates
ኃይል የተቋረጠባቸው የሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ ከተሞች መብራት አግኝተዋል

ዓርብ የካቲት 29 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የደብረ ብርሃን-ሸዋ ሮቢት-ኮምቦልቻ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተጠግኖ ሥራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገለጸ።

በዚህም በሸዋ ሮቢት አቅራቢያ ጉዳት ደርሶበት የነበረው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በመጠገኑ፤ ካለፈው እሁድ ጀምሮ ኃይል ተቋርጦባቸው የነበሩ የአፋር መዲና ሠመራን ጨምሮ በሰሜን ምሥራቅ የሚገኙ ከተሞች ዳግም የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸው ተገልጿል።

ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከባህር ዳር-በደብረታቦር-ንፋስ መውጫ-ጋሸና- አላማጣ የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር "ተበጥሷል" ብሎ ነበር።

ይሁን እንጂ አዲስ ማለዳ ትላንት የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽን ዋቢ አድርጋ "በጽንፈኛ ኃይል በጦር መሳሪያ ተመቶ ነው" ብላ የዘገበች ሲሆን 'የጎጃም ፋኖ' ብለው ራሳቸውን የጠሩ አካላት ኃይል ማስተላለፊያው "በመንግስት ኃይል" እንደተመታ መግለጫ ማውጣታቸውን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

ለአካል ጉዳተኞችና አረጋውያን የፍትሕ ተደራሽነት ክፍተት መኖሩን የመብቶች ኮሚሽኑ ገለጸ

ሐሙስ የካቲት 28 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ፍርድ ቤቶች እና የፍትሕ ጽሕፈት ቤቶች አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያንን ከማካተት አንጻር የተለየ የበጀት ዕቅድ፣ ፖሊሲዎች ወይም መመሪያዎች የላቸውም ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ።

ኢሰመኮ በዛሬው ዕለት ባለ 31 ገጽ የፍርድ ቤቶች እና ፍትሕ ጽሕፈት ቤቶች ለአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን የተደራሽነት ሁኔታ ላይ ያወጣውን ሪፖርት አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

በተመረጡ የአፋር፣ አማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሌ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች የፍትሕ ተቋማት ኮሚሽኑ ክትትል አድርጓል።

በሪፖርቱም የአካል ጉዳተኞችና አረጋውያንን ፍላጎቶች መሠረት ያደረገ የአሠራር ሥርዓት ያልተዘረጋ መሆኑን፣ ለሴት አካል ጉዳተኞች ተደራራቢ የመብት ጥሰት ተጋላጭነት ያገናዘበ የአሠራር ሥርዓት አለመኖሩን ገልጿል።

ለመብት ጥሰት ተጋላጭ ለሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚደረጉ ድጋፎች የተቀመጠ የአሠራር ሥርዓት ቢኖርም ክትትሉ በተደረገባቸው ቦታዎች በወረዳ ደረጃ ወደሚገኙ ፍርድ ቤቶች እና ፍትሕ ጽሕፈት ቤቶች አሠራሩ ባለመውረዱ የፍትሕ ተደራሽነት ክፍተቶች መኖራቸውን አመላክቷል።

እንዲሁም ክትትል በተደረገባቸው ሁሉም የፍትሕ ተቋማት የሚሠሩ ሠራተኞችና ኃላፊዎች በተደራጀ መንገድ ስለአካል ጉዳተኞችና አረጋውያን ሰብአዊ መብቶች በተለይም የፍትሕ ተደራሽነት ላይ ያተኮረ ስልጠና ወይም የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት አለማግኘታቸውንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ስለሆነም በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ፍርድ ቤቶች እና ፍትሕ ጽሕፈት ቤቶች አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን የሚገጥማቸውን ተቋማዊ መሰናክሎች በማስወገድ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚረዱ አዳዲስ ሕጎችን፣ ፖሊሲዎችን መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል።

እንዲሁም የአሠራር ሥርዓቶችን እንዲያወጡ እና ክፍተት በታየባቸው ነባር ሕጎች፣ ፖሊሲዎች እና የአሠራር ሥርዓቶች ላይ ተገቢውን ማሻሻያዎች እንዲያደርጉ ኢሰመኮ ምክረ ሐሳብ አቅርቧል።

የአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ፍትሕ የማግኘት መብት ኢትዮጵያ ፈርማ የአገሪቱ የሕግ አካል ባደረገቻቸው የዓለም አቀፍ ስምምነቶች፣ አህጉራዊ እንዲሁም ብሔራዊ የሕግ ማዕቀፎች እና መርሖዎች ዕውቅና የተሰጠው ነው።
———
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት እንዲሁም ሃሳብ፣ አስተያየት እና የሚዲያ ሽፋን ጥቆማ ለማድረስ
የአዲስ ማለዳ ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይቀላቀሉ፤ ለሌሎችም ያጋሩ!

Telegram | Facebook | YouTube | X | www.addismaleda.com | 0961414141
180 ሺህ ህገ ወጥ ፍልሰተኛ ኢትዮጵያውያን በአንድ ዓመት ተኩል ውስጥ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል- የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር

ሐሙስ የካቲት 28 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) መደበኛ ባልሆነ ፍልሰት ከሀገር ወጥተው የነበሩ 180 ሺህ ዜጎች በአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ገለጹ።

ሚኒስትር ዴኤታዋ ይኼንን የተናገሩት፤ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከልና የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ለመቀነስ የሚያስችል የንቅናቄ መድረክ በመቀሌ ከተማ መጀመሩን ተከትሎ ነው።

በዚህም የንቅናቄ መድረክ  መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከልና ተመላሾችን መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል ህብረት ለመፍጠር ታልሟል ተብሏል።

እንዲሁም በሌሎች አገሮች በችግር ላይ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልጸዋል።

በተመሳሳይም በመድረኩ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የማህበራዊ ጉዳይና የመልሶ ማቋቋም ክላስተር ሴክሬታሪያት ሃላፊ ጄነራል ተክላይ አሸብር፤ በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና የወጣቶች ፍልሰት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አንስተዋል።

በሱዳንና በሊቢያ አድርገው ወደ አውሮፓ እንዲሁም፤ የጂቡቲንና የየመንን በረሃዎችና ባህር በማቋረጥ ወደ ሳዑዲ አረቢያና ሌሎች የአረብ አገራት በሚያደርጉት ጉዞ ለተለያዩ ችግሮች እየተጋለጡ መሆኑም ተጠቁሟል።

የተበጠሰው የባህር ዳር-ጋሸና-አላማጣ መስመር ተጠገነ

ረቡዕ የካቲት 27 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ)ትላንት የተበጠሰው የባህር ዳር-ጋሸና-አላማጣ መስመር ተጠገነ "በእልህ አስጨራሽ ርብርብ ተጠግኗል" ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
    
በትላንትናው ዕለት አብዛኛው የሰሜን ምስራቅ የኢትዮጵያ ክፍል የኤሌክትሪክ ኃይል እንደተቋረጠበት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስታወቁን አዲስ ማለዳ ዘግባ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፤ ተቋሙ ከባህር ዳር-በደብረታቦር-ንፋስ መውጫ-ጋሸና-አላማጣ የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር “መበጠሱን” ብቻ ነበር ያስታወቀው።

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በክልሉ በርካታ አካባቢዎች ከትላንት እኩለ ቀን ጀምሮ ለተቋረጠው የኤሌክትሪክ ኃይል፤ ምክንያቱ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር “ጽንፈኛ ኃይሎች" በጦር መሳሪያ ተመቶ ነው ማለቱ አይዘነጋም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በክልሉ ያለውን የትጥቅ እንቅስቃሴ የሚደግፉ የብዙኀን መገናኛ ለከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያው መመታት መንግስትን ተጠያቂ እያደረጉ ነው።
———
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት እንዲሁም ሃሳብ፣ አስተያየት እና የሚዲያ ሽፋን ጥቆማ ለማድረስ
የአዲስ ማለዳ ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይቀላቀሉ፤ ለሌሎችም ያጋሩ!

Telegram | Facebook | YouTube | X | www.addismaleda.com | 0961414141
ከምዕራብ ወለጋ ዞን ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች እየተመለሱ መሆኑን መንግስት ገለጸ

ረቡዕ የካቲት 27 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ከምዕራብ ወለጋ ዞን በታጣቂው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና የመንግስት ኃይል መካከል በነበረ ግጭት ከመኖሪአይ ቀያቸው ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች እየተመለሱ ነው ተባለ።

የብሔራዊ ዜና አገልግሎት ድርጅቱ የዞኑን ቡሳ ጎኖፋ ጽፈት ቤት ኃላፊ ዋቢ አድርጎ ባወጣው ዘገባ በአንደኛ ዙር 601 አባ ወራዎች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ነው መባሉን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች። በዚህም ከዞኑ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ የተፈናቀሉ 313 አባ ወራዎች ወደ መኖሪያቸው ተመልሰዋል ተብሏል።

በመንግስት በኩልም ለተመላሾች ድጋፍ ይደረጋል የተባለ ሲሆን ዘገባው ተፈናቃዮቹ ከየት አካባቢ እንደተመለሱ የጠቀሰው ነገር የለም።

በጥር ወር መጨረሻ በምዕራብ ወለጋ በአካባኢው የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ኃይል በጠራው የእንቅስቃሴ ገደብ የትራንስፖርት አገልግሎት መስተጓጎሉ የሚታወስ ነው።

ይሁን እንጂ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮምኒኬሽን ቢሮ በወቅቱ በሰጠው መግለጫ "ሸኔ" ሊፈጥረው የነበረው መስተጓጎል "ከህዝቡ ጋር" ማክሸፍ ተችሏል ሲል መግለጹን አዲስ ማለዳ መዘግቧ አይዘጋም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የካቲት 11 ቀን 2016 ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ባሰራጨው መረጃ በደብረብርሃን ከተማ በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች ከተጠለሉ ተፈናቃዮች መካከል "ኦሮሚያ ክልል" መሬት ያላቸው የአማራ ተወላጆች ብቻ ወደ ተፈናቀሉበት ወለጋ አካባቢ በግዴታ እንዲመለሱ መደረጉን ገልጾ ነበር። ተፈናቃዮቹ “ስማችሁ ከወለጋ የተላከ ነው“ ተብለዋል ማለቱንም አዲስ ማለዳ ዘግባ ነበር።
———
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት እንዲሁም ሃሳብ፣ አስተያየት እና የሚዲያ ሽፋን ጥቆማ ለማድረስ
የአዲስ ማለዳ ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይቀላቀሉ፤ ለሌሎችም ያጋሩ!

Telegram | Facebook | YouTube | X | www.addismaleda.com | 0961414141
See more posts

View in Telegram

Telegram Channel