Ethio Fm 107.8 Canali Telegram

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

View in Telegram

Recent Posts

ፖሊስ ተማሪ ቃልኪዳን ባህሩ አለመደፈሯን አረጋግጦ መግለጫ ከማውጣቱ በፊት የህክምናው ሂደት ትክክል መሆኑን ማጣራት እና ማረጋገጥ ነበረበት ሲል የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር አስታወቀ፡፡

በወጣት ቃልኪዳን ባህሩ ላይ በተፈጸመው አስገድዶ መድፈር፣ ዕገታና ፆታዊ ጥቃት ዙሪያ የወጡ የፖሊስ፣ የህክምና እና የማህበራዊ ሚድያ መረጃዎች እንደገና እንዲጣሩና ትክክለኛው መረጃ ለህዝብ እንዲደርስ ሲልም የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር እና አጋሮቹ አስታውቀዋል፡፡

ቃልኪዳን ባህሩ የተባለች የ17 ዓመት ወጣት ላይ በቀን ጥቅምት 1/2014 ዓ/ም ከቤተሰቦቿ ጋር በምትኖርበት መኖሪያ ቤት፣ ተወስዳ መደፈሯ የተገለፀ ሲሆን፣
በድጋሚ ደግሞ በቀን መጋቢት 16/2016 ዓ.ም በማታውቃቸው ሰዎች ከምትኖርበት አካባቢ ወዳልታወቀ ቦታ ተወስዳ የአስገድዶ መድፈርና በባዕድ ነገር በማደንዘዝ እራሷን እንድትስት በማድረግ ጥቃት እንዳደረሱባት ተገልፆ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ቁጣን ያስነሳ ጉዳይ ሆነ ቆይቷል፡፡

ማህበራዊ ሚድያዎች የተበደለን ሰው በደል ከማውጣት እና አስፈላጊውን ምላሽ እንዲያገኝ ከማድረግ አኳያና ድምፁ ያልተሰማ ሰው አገልግሎት ለማግኘት የሚረዳ ቢሆንም የማይገባን ጥቅም ለማግኘት፣
አሉባልታዎችን በመፍጠርና ተጠቂ ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ሳያገናዝቡ የተዛቡ መረጃዎችን ማስተላለፍ አንዲት ጥቃት የደረሰባት ሴት መፍትሄ ወይም ፍትህ እንዳታገኝ እንቅፋት ይሆናል ሲል ማህበሩ ኮንኗል፡፡

ፖሊስ ተማሪ ቃልኪዳን ባህሩ አለመደፈሯን አረጋግጦ መግለጫ ከማውጣቱ በፊት የህክምናው ሂደት ትክክል መሆኑን ማጣራት እና ማረጋገጥ ነበረበት ሲልም የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር በመግለጫው ገልፃል፡፡

የፖሊስ ምርመራ መዝገቡ የተዘጋም ከሆነ ፋይሉ የተዘጋበትን ምክንያት፣ መዝገቡ የተዘጋው ለጊዜው ቢሆን እንኳን በቂ ማስረጃ ከተገኘ ሊከፈትና ምርመራው ሊካሄድ እንደሚችል ማስረዳት ሲገባው ይህንን ሳያደርግ በመቅረቱ በተጠቂዋ ላይ ተጨማሪ ጥቃት ሊፈጸም ችሏል ተብሏል፡፡

ፖሊስ መነሻውን የህክምና ሰነድ ብቻ በማድረግ በጉዳዩ ላይ በቂ ማስረጃ የለም ማለቱ፣ አጥቂዎችን ለመያዝ በቂ ክትትል አለማድረጉ እንዳሳዘነው ማህበሩ ገልፃል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር እና አጋር ድርጅቶቹ የሚመለከታቸው አካላት የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ሚኒሊክና ጴጥሮስ ሆስፒታሎች፣ማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች፣ሚዲያ አካላትና መላው ህብረተሰብ ክፍል በጉዳዩ ላይ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ፖሊስ ግንቦት 10/2016 ዓ.ም በማህበራዊ ሚዲያ በሰራጨው መግለጫው አንዲት ወጣት እንደተደፈረች ተደርጎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ ነው ማለቱ አይዘነጋም፡፡

በአቤል ደጀኔ

ግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ.ም
ከካሳ ክፍያ ጋር በተያያዘ የመንግስት አስተዳደሮች፣ ዳኞች እና ደላሎች የሚያገኙትን ያልተገባ ጥቅም ያስቀራል የተባለለት አዋጅ ሊወጣ ነው።

በካሳ ክፍያ ሂደት የመንግስት አስተዳደር ዳኞች እና ደላሎች የሚያገኙትን ያልተገባ ጥቅም በማስቀረት ዋናው የመሬት ባለይዞታውን ተጠቃሚ የሚያደርግ አዋጅ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

ይህ የተባለው መሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን፣ ካሳ የሚከፈልበትን እና ተነሽዎች መልሰው የሚቋቋበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ ለማሻሻል ውይይት በተደረገበት ወቅት ነው።

በውይይቱ የተሳተፉ አካላት እንደተናገሩት ለመሰረተ-ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ መዘግየት ዋናውና ትልቁ ማነቆ የልማት ተነሺዎች የሚጠይቁት የተጋነነ የካሳ ክፍያ መሆኑን ገልጸው፤ ንብረት የሚገምቱ እና ካሳ የሚከፍሉ ተቋማት ወደ አንድ ሊመጡ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በማህበረሰቡም ፕሮጀክቶች ተገንብተው ከሚሰጡት ጥቅም ይልቅ፤ ከካሳ ክፍያ የሚገኘውን ጥቅም አስበልጦ የማየት አስተሳሰብ በመኖሩ፤ ትክክለኛ እና ወቅቱን ያገናዘበ የካሳ ክፍያ ለመፈጸም የአዋጁ መሻሻል አስፈላጊነቱ የላቀ እንደሆነም ባለድርሻ አካላት አንስተዋል።

የፍትህ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በበኩላቸው የአዋጁ መሻሻል በካሳ ክፍያ ሂደቱ በታችኛው እርከን የመንግስት አስተዳደር፣ ዳኞች እና ደላሎች የሚያገኙትን ያልተገባ ጥቅም በማስቀረት ዋና የመሬት ባለይዞታውን ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል።

ማሻሻያ አዋጁ መሰረተ ልማቶች ሲገነቡ የንብረት ግመታው እና የካሳ ክፍያው በክልልና በወረዳ መዋቅሮች የሚፈጸም መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ዜጎች ቅሬታ ሲያነሱም በአቅራቢያቸው የፍትህ አገልገሎት እንዲያገኙ የሚረዳ መሆኑን ተናግረዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ.ም
ኮማንድ ፖስትና ብሔራዊ ደኅንነት ጣልቃ ቢገቡም የወርቅ ኮንትሮባንድ ሊቆም አልቻለም ተባለ፡፡

በመከላከያ ኮማንድ ፖስትና በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጭምር ክትትል ቢደረግም፣ በክልሎች እየጨመረ የመጣው የወርቅና የማዕድናት ኮንትሮባንድ ሊቆም እንዳልቻለ ተነግሯል፡፡

በማዕድናት ሕገወጥ ግብይት፣ ኮንትሮባንድና የፀጥታ ችግር ምክንያት በባለፉት ዘጠኝ ወራት ወደ ብሔራዊ ባንክ የገባው ወርቅ ሦስት ቶን ብቻ እንደሆነ፣ ይህም ከዕቅዱ 50 በመቶ ብቻ መሆኑ ታውቋል፡፡

የወርቅ ገቢም ከታቀደው 363 ሚሊዮን ዶላር 67 በመቶ ብቻ መሳካቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በመጋቢት ወር ብሔራዊ ባንክ የገባው ወርቅ 350 ኪሎ ግራም ሲሆን፣ ይህም በ2014 ዓ.ም. መጋቢት ወር ከተገኘው 800 ኪሎ ግራም በእጅጉ ያነሰ ነው ተብሏል፡፡


በአገሪቱ ያሉ ወርቅ አምራቾች የባህላዊና የኩባንያ ተብለው ሲከፈሉ፣ በተለይ በባህላዊ አምራቾች የሚወጣው ወርቅ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ወደ ብሔራዊ ባንክ መግባት ያቆመ መሆኑን፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከታቀደው 2‚306 ኪሎ ግራም ውስጥ 609 ኪሎ ብቻ (26 በመቶ) መቅረቡን መረዳት ተችሏል፡፡

እንደ ሪፖርተር ዘገባ በተለይ ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች ለብሔራዊ ባንክ ለማቅረብ ካቀዱት አንፃር የቀረበው እጅግ አናሳ መሆኑን፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የማዕድን ሚኒስቴር ሪፖርት ያሳያል፡፡

ይሁን እንጂ ፈጽሞ ወርቅ ካላቀረቡት የትግራይ፣ የአፋር፣ የደቡብ ኢትዮጵያና የሶማሌ ክልል አንፃር የበፊቶቹ እንደሚሻል ሪፖርቱ ያሳያል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ.ም
መንግስት የሰጠኝ ህጋዊ ቦታ እውቅና ሊሰጠው ይገባል ሲል አምባ ትምህርት ቤት ጠየቀ።

አምባ ትምህርት ት/ቤት ለተቸገሩ በጎ አድራጎት ማህበር ለትምህርት ቤት ግንባታ ከመንግስት መስሪያ ቦታ ቢሰጠኝም እስካሁን ህጋዊ ማረጋገጫ ስላልተሰጠኝ ስራዬን ለማከናወን ተቸግሬያለሁ ብሏል።

የአምባ ትምህርት ቤት መስራች እና ስራ አስኪያጅ ካሌብ ፀጋዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት፣ ይህ ሁኔታ ማህበሩ ያቀዳቸውን ግንባታዎች እንዳይከውን እና አጥጋቢ የሆነ ስራ ለመስራት እንዳንችል አደርጎናል ብለዋል፡፡

ማእከሉ የገጠሙት ችግሮች የሚቀረፍለት ከሆነ በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ አዳሪ ትምህርት ቤት ለመገንባት እቅድ እንዳለው ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ማህበሩ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም ነግረውናል።
ከዚህ በፊት ይበቃ የነበረው የተማሪዎች ምገባ አሁን ላይ እጥረት እያጋጠመው መሆኑ ነግረውናል፡፡

የትምህርት ቤቱ ዋናው የገቢ ምንጭ ከሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ባሉ ግለሰቦች የሚያደርጉት እርዳታ ስለመሆኑንም አንስተዋል።

አምባ ትምህርት ቤት ትምህርት መማር ለማይችሉ እና ለተቸገሩ ልጆች ደረጃውን የጠበቀ የቅድመ መደበኛ እና መደበኛ ትምህርት እንዲያገኙ የማድረግ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

እንደዚህ ያሉ የበጎ አድራጎት ማህበራትን መደገፍ እና ተቋማቶቹን ማበረታታት የመንግስት ሀላፊነት ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዱ ግለሰብ እና ማህበረሰብ ሀላፊነት ስለሆነ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተቋማቱን እንዲደግፍ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በሐመረ ፍሬው

ግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ.ም
መንግስት የሰጠኝ ህጋዊ ቦታ እውቅና ሊሰጠው ይገባል ሲል አምባ ትምህርት ቤት ጠየቀ።

አምባ ትምህርት ት/ቤት ለተቸገሩ በጎ አድራጎት ማህበር ለትምህርት ቤት ግንባታ ከመንግስት መስሪያ ቦታ ቢሰጠኝም እስካሁን ህጋዊ ማረጋገጫ ስላልተሰጠኝ ስራዬን ለማከናወን ተቸግሬያለሁ ብሏል።

የአምባ ትምህርት ቤት መስራች እና ስራ አስኪያጅ ካሌብ ፀጋዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት፣ ይህ ሁኔታ ማህበሩ ያቀዳቸውን ግንባታዎች እንዳይከውን እና አጥጋቢ የሆነ ስራ ለመስራት እንዳንችል አደርጎናል ብለዋል፡፡

ማእከሉ የገጠሙት ችግሮች የሚቀረፍለት ከሆነ በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ አዳሪ ትምህርት ቤት ለመገንባት እቅድ እንዳለው ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ማህበሩ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም ነግረውናል።
ከዚህ በፊት ይበቃ የነበረው የተማሪዎች ምገባ አሁን ላይ እጥረት እያጋጠመው መሆኑ ነግረውናል፡፡

የትምህርት ቤቱ ዋናው የገቢ ምንጭ ከሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ባሉ ግለሰቦች የሚያደርጉት እርዳታ ስለመሆኑንም አንስተዋል።

አምባ ትምህርት ቤት ትምህርት መማር ለማይችሉ እና ለተቸገሩ ልጆች ደረጃውን የጠበቀ የቅድመ መደበኛ እና መደበኛ ትምህርት እንዲያገኙ የማድረግ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

እንደዚህ ያሉ የበጎ አድራጎት ማህበራትን መደገፍ እና ተቋማቶቹን ማበረታታት የመንግስት ሀላፊነት ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዱ ግለሰብ እና ማህበረሰብ ሀላፊነት ስለሆነ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተቋማቱን እንዲደግፍ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በሐመረ ፍሬው

ግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ.ም
የግሪኩ ኦሎምፒያኮስ የኮንፈረንስ ሊግ አሸናፊ ህኖ አዲሰ ታሪክ ፀፈዋል!!!!!

የግሪኩ ክለብ ኦሎምፒያኮስ ከጣልያኑ ክለብ ፊዮሬንቲና ጋር ያደረገውን የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆነዋል።

የኦሎምፒያኮስን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አዮብ ኤል ካቢ በተጨማሪ ደቂቃ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ኦሎምፒያኮስ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓ መድረክ ውድድር ሻምፒዮን መሆን ችለዋል።

በተጨማሪም ኦሎምፒያኮስ የአውሮፓ መድረክ ውድድር ዋንጫን ማሸነፍ የቻለ የመጀመሪያው የግሪክ ክለብ በመሆን አዲስ ታሪክ ፅፈዋል።

በጋዲሳ መገርሳ

ግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ.ም
ባየር ሙኒክ በይፋ አሰልጣኝ ሾመ !

የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ ቤልጂየማዊውን አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ በአሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ምትክ በሀላፊነት መሾማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ ባየር ሙኒክን ለሶስት የውድድር አመታት ለማሰልጠን እስከ 2027 የሚያቆያቸውን ውል በይፋ ፈርመዋል።

ባየር ሙኒክ ለበርንሌይ ለአሰልጣኙ የካሳ ክፍያ የሚሆን 12 ሚልዮን ዩሮ የሚጠጋ ገንዘብ መክፈላቸው ተገልጿል።

በጋዲሳ መገርሳ

ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም
የነገ የግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን
የነገ የግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን
ጋዜጠኛ መሠለ ገ/ህይወት ከዜናው ዓለም ወደ መዝናኛው ዓለም ሊሸጋገር ነው።

በዜና አንባቢነት የሚታወቀው አንጋፋው ጋዜጠኛ መሠለ ገ/ህይወት በመዝናኛው ዘርፍ ሊመጣ ነው።

ላለፉት 18 ዓመታት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በዜና አንባቢነት ሲያገለግል የቆየው መሠለ በቅርቡ "መሴ ሾዉ" የተሠኘ የምሽት መዝናኛ ፕሮግራም በአባይ ቲቪ እንደሚጀምር ታውቋል።

መሴ ሾዉ የተሠኘው የምሽት የመዝናኛ ፕሮግራም (late night show) የሠርጌለታ፣ የሙዚቀኞች ብፌ፣ የእንግዳ ቆይታ እንዲሁም እግሬ ሲደርስ የተሰኙ አዝናኝ መሠናዶዎች የተካተቱበት ነው።

ፕሮግራሙ በየሣምንቱ ቅዳሜ ምሽት በአባይ ቲቪ ከመተላለፉ ባሻገር መሴ ሾው በሚል ስያሜ በተከፈተ በራሱ የዩቲዩብ ቻናል ለተመልካች የሚደርስ ይሆናል።

ጋዜጠኛ መሠለ ከሁለት ዓመታት በፊት የመልካሙ ተበጀንና የንዋይ ደበበን ዘፈኖች በመጫወት የመዝናኛ ተሥጥዖውን ማሣየቱና ተመልካቾችን ማሥደመሙ ይታወሳል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም
ኢትዮጵያ ምርጥ የመንገድ መሰረተ ልማት አላቸው ተብለው ደረጃ ውስጥ ከገቡ የአፍሪካ ሀገራት መካከል አልተካተተችም፡፡

በአፍሪካ ደረጃቸውን የጠበቁ የመንገድ መሰረተ ልማት ካላቸው ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ አለመካተቷ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

ቢዝነስ ኢንሳይደር የፈረንጆቹ 2023 አመት የአፍሪካ መሰረተ ልማት እድገት በተመለከተው ጥናቱ ላይ የመንገድ መሰረተ ልማት ዋነኛው ነበር፡፡

በዚህም የአፍሪካ ሀገራት የመንገድ ጥራት እና ደረጃ ያወጣ ሲሆን ሃገራችን ኢትዮጵያ ደረጃ ውስጥ ከገቡ 30 የአፍሪካ ሀገራት መካከል አልተካተተችም፡፡

በጥናቱ በአብዛኛው ደረጃ ውስጥ የገቡት የሰሜን አፍሪካ ሀገራት ሲሆኑ ጥቂት የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት በዚህ ዝርዝር ውስጥ ተቀምጠዋል፡፡

በዚህ ጥናት ውስጥ ደቡብ አፍሪካ ጥራቱን የጠበቀ የመንገድ መሰረተ ልማት ያላት ተብላም በአንደኝነት ተቀምጣለች፡፡

ናሚቢያ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ የሰሜን አፍሪካዊቷ ሃገር ሞሮኮ በሶስትኛ ደረጃ የተቀመጠች ሃገር ሆናለች፡፡

ጥራቱን የጠበቀ የመንገድ መሰረተ ልማት አላቸው ከተባሉ ሀገራት አራተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ቦትስዋና ናት፡፡

ሊቢያ አልጄርያ ዚምባብዌ ግብጽ ኮትዲቫር እና ቱኒዝያ በቅደም ተከተል ከአምስት እስከ አስረኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ ሀገራት ናቸው፡፡

ቢዝነስ ኢንሳይደር

ሔኖክ ወ/ገበርኤል

ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም
ባርሴሎና በይፋ አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክን ሾመ !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና በአሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ ምትክ ጀርመናዊውን አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ በሀላፊነት መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የቀድሞ የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ባርሴሎናን እስከ 2026 የውድድር ዘመን ለማሰልጠን የሁለት አመት ኮንትራት መፈረማቸው ተገልጿል።

በ ጋዲሳ መገርሳ

ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas
የማህጸን በር ካንሰር ቅድመ ልየታ ያከናወኑ ሴቶች ህክምናውን እያገኙ አይደለም ተባለ፡፡

የቅድመ ካንሰር ልየታ አከናውነው ምልክቱ የተገኘባቸው ሴቶች የህክምና አገልግቱን እያገኙ አለመሆኑን የነገሩን በጤና ሚኒስቴር በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፋጻሚ እና የማህጸን በር ካንሰር ፕሮግራም ተጠሪ ወ/ሮ ታከለች ሞገስ ናቸው፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ የቅድመ ካንሰር ልየታውን የሚያከናውኑ ሴቶች ቁጥር እየጨመረ እና ከዚህ ቀደም ከነበረው ጋር ሲነጻጸር መሻሻሎች መስተዋላቸው የተገለጸ ሲሆን በግንዛቤ እጥረት ምክንያት ግን የህክምና አገልግቱን እያገኙ አለመሆኑ ተገልጿል፡፡

የቅድመ ካንሰር ልየታ ግንዛቤ ቢኖርም ህክምናው ላይ ግን የግብዛቤ እጥረቶች መኖራቸው ተነግሯል፡፡

የቅድመ ካንሰር ምልክት ካንሰር ነው ማለት አይደለም ያሉ ሲሆን ምልክቱ ከታየበሚደረግ የህክምና ክትትል እንደሚዳን ህብረተሰቡ ሊገነዘብ ይገባል ተብሏል፡፡

የቅድመ ካንሰር ልየታ ህክምና የሚሆነው የተስተዋለውን የቅድመ ካንሰር ምልክትን ወደ ካንሰርነት እንዳይለወጥ ማድረግ መሆኑን ገለጹ ሲሆን ፤ የቅድመ ልየታ ከተከናወነ እና ክትባቶች ከተወሰዱ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰርን መከላከል እንደሚቻል ተነግሯል፡፡

በህክምናው እስከ አንድ ወር ድረስ ከግብረ ስጋ ግንኙነት የመታቀብ ሁኔታ አለ ተብሏል።

በህክምናው ላይ የወንዶች በተለይም የባሎች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ እገዛ ሊያደርጉ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

አንዲት ሴት በህይወት ዘመኗ 2 ጊዜ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ ካከናወነች 70 በመቶ ተጋላጭነቷን እንደሚቀንስ ተጠቁሟል።

ከ30 ዓመት በላይ የሆነች፣ የግብረስጋ ግንኙነት የጀመረች ሴት በ3 ዓመት አንዴ እንዲሁም ኤች አይቪ ኤድስ በደሟ ውስጥ ካለ በ2 ዓመት አንዴ የቅድመ ካንሰር ልየታ ልታከናውን ይገባል ተብሏል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም
የዛሬ የግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን
የዛሬ የግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን
See more posts

View in Telegram

Telegram Channel