etrade.gov.et Telegram Channel

ይህ ቻናል በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና በክልል ንግድ ቢሮዎች ተጠቃሚ ደንበኞች ስለ ኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች መረጃ ለመለዋወጥ ይረዳ ዘንድ የተፈጠረ ነው:: This channel was created to help users of the Ministry of Trade & Regional Integration and Trade Bureaus exchange info about OTRS.

View in Telegram

Recent Posts

‼️ ማስታወቂያ‼️
የንድ ፈቃዳችሁን ያላደሱ የአማራ ክልል የሚገኙ ነጋዴዎች በሙሉ፣ የንግድ ፈቃድ ማደሻ ጊዜ እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም የተራዘመ ስለሆነ የሚጠበቅባችሁን የግብር ክሊራንስ በማቅረብ ያለቅጣት የንግድ ፈቃዳችሁን ማደስ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
+++++++++++++++++++++++++
‼️ NOTICE‼️
To all traders in the Amhara region who have not renewed your business license, we would like to inform you that you can renew your business license without penalty by providing the required tax clearance as the business license renewal period has been extended until SENE 30/2016 E.C.
============================
መጀመሪያው ወር የቅጣት እድሳት ሊያበቃ 6 ቀን ብቻ እንደቀረው ያውቃሉ?
ለተጨማሪ ቅጣት ከመዳረጎ በፊት የንግድ ፍቃድዎን እንዲያድሱ እናሳስባለን።
ለተጨማሪ መረጃ፡- https://t.me/EthioEoDB/9
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል።
====================
አዲስ አበባ 27/07/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ መጋቢት ወር ሲሸጥ በነበረበት ዋጋ የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ከመጋቢት 28/07/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በስራ ላይ በነበረበት ዋጋ እንዲቀጥል ተወስኗል።
ተጨማሪ መረጃዎችን:-- https://t.me/EthioEoDB
የሸማቾች መብትና የነጋዴው ግዴታ
ለተጨማሪ መረጃ፡- https://t.me/EthioEoDB
!! ማስታወቅያ !!
አዲስ አበባ 22/06/2016ዓ.ም (የንቀትሚ)

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በገብያ ቦታ በመገኝት በሰራው የገብያ ክትትልና ቁጥጥር ስራ ምንጩ የማይታወቅ እንዲሁም የጥራት ደረጃቸውን ያላሟሉ አስር ምርቶችን በገብያ ውስጥ ያገኝ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው አሳሰበ፡፡

በመሆኑም እነዚህን ምርቶች በገበያ ቦታ ማንኛውም ነጋዴ ሆነ ግለሰብ ሲሸጥ ከተገኙ ለክልሎችና ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮዎች እንዲሁም ለሚመለከታቸው የፍትህ አካላት ጥቆማ እንድታደረጉ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን:-https://t.me/EthioEoDB/34
‼️‼️-------------------
በዛሬው ይዘታችን ላይ የግል ድርጅትን(sole proprietorship) ማዋቀር ምን ጥቅም እና ጉዳት እንዳለው እንዳስሳለን።
‼️‼️-------------------
ተጨማሪ መረጃ :- https://t.me/EthioEoDB/32
የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ትግበራ ማፋጠን ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ ነው
==================
አዲስ አበባ 12/06/2016 (ንቀትሚ)የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ትግበራን ማፋጠን እና የአፍሪካ የንግድ እና የኢኮኖሚ ትስስርን ማሳደግ በሚል መሪ ሃሳብ ለአምባሳደሮች እና ለዲፕሎማቶች ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ እየተሰጠ ባለው ስልጠና አምባሳደሮች፣ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ ዛዲግ አብርሃ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ስልጠናው በአፍሪካ ሀገራት መካከል የሚደረገውን የግብይት መጠን እና የንግድ ትስስር ለማሳደግ ያለመ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት እንደሚሰጥ ተመላክቷል ሲል ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ :https://t.me/EthioEoDB
ኦን ላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ሽፋን 89.8 በመቶ ደርሷል።
===================
አዲስ አበባ 05/06/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) ባለፉት ስድስት ወራት የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና ተደራሽ ለማድረግ በልዩ ትኩረት በተሰራው ስራ ኦን ላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ሽፋን 89.8 በመቶ መድረሱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ተናግረዋል፡፡

በሀገራችን የንግድ ስራን ለመጀመር የነበረውን አስቸጋሪነት ለመፍታት የተጀመረው ኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግት ሽፋን ባለፈው በጀት ዓመት ከነበረበት 57 በመቶ ባለፉት 6 ወራት ወደ 89.8 በመቶ ማድረስ መቻሉን ያስረዱት ሚኒስትሩ ይህም የንግድ ማህበረሰቡ የነበረበትን እንግልት፣ ወጪ እና የጊዜ ብክነት በማስቀረት  የደንበኛ እርካታን ማሳደጉን ገልጸዋል፡፡

በሌላ መልኩ የድህረ ፈቃድ ክትትለና ቁጥጥር ስራው የተሟላ ባለመሆኑና የሚወሰደው እርምጃ የተጠናከረ ባለመሆኑ ፈቃድ ሳይኖራቸው የሚነግዱ፣ ፈቃድ ሳያሳድሱ እንዲሁም  ከዘርፍ ውጪ የሚነግዱ በመኖራቸው በቀጣይ ክትትልና ቁጥጥሩን በማጠናከር አስተማሪ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

በግማሽ በጀት ዓመቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ 1,381,938 አገልግለቶች በኦንላይ የተሰጡ ሲሆን ይህ አፈፃጸም ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት አፈፃጸም ጋር ሲነፃጸር የ69 በመቶ ብልጫ አለው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን:-

https://t.me/EthioEoDB
https://t.me/EthioEoDB/28

Telegram
EoDB (Ease of Doing Business)
‼️‼️-------------------
በንግድ ስም እና በድርጅት ስም ምሃከል ያለውን ልዩነት ያውቃሉ?
‼️‼️-------------------
ድርጅቶ የሚጠሩበት ስም ለድርጅትዎ ስኬት ወይም ውድቀት ምክያት ሊሆን ይችላል። እርግጥ ነው፣ ድርጅትዎ ስኬታም እንዲሆን ሚና የሚጫወቱ ብዙ ነገሮች አሉ ከነሱም ውስጥ አንዱና ዋነኛው ግን የንግድዎ ስም ነው። የንግድ/የድርጅት ስምዎት የአገልግሎቶት/የምርቶት ተጠቃሚዎች ስለ ድርጅቶት ከሚያስተውሏቸው የመጀመሪያ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው።
በንግድ ስም እና በንግድ ምልክት መሃከል ያለውን ልዩነት ያውቃሉ?

ለተጨማሪ መረጃ፡- https://t.me/EthioEoDB/9
የመጀመሪያው ወር የቅጣት እድሳት ሊያበቃ 1 ቀን ብቻ እንደቀረው ያውቃሉ? 
ለተጨማሪ ቅጣት ከመዳረጎ በፊት የንግድ ፍቃድዎን እንዲያድሱ እናሳስባለን።
ለተጨማሪ መረጃ፡- https://t.me/EthioEoDB/9
+++==================================================== +++
This is a polite reminder that only 1 day remain till the first month of penalty renewal for the Ethiopian fiscal year expires. If you haven't done, we strongly advise you to renew your business license today to prevent incurring excessive fines and penalties.
for more Info :- https://t.me/EthioEoDB/9
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል።
=====================
አዲስ አበባ 27/05/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር ሲሸጥ በነበረበት ዋጋ የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ከጥር 28/05/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በስራ ላይ በነበረበት ዋጋ እንዲቀጥል ተወስኗል።
ተጨማሪ መረጃዎችን:-

For more info:- https://t.me/EthioEoDB
የመጀመሪያው ወር የቅጣት እድሳት ሊያበቃ 6 ቀን ብቻ እንደቀረው ያውቃሉ?
ለተጨማሪ ቅጣት ከመዳረጎ በፊት የንግድ ፍቃድዎን እንዲያድሱ እናሳስባለን።
ለተጨማሪ መረጃ፡- https://t.me/EthioEoDB/9
+++==================================================== +++
This is a polite reminder that only 6 days remain till the first month of penalty renewal for the Ethiopian fiscal year expires. If you haven't done, we strongly advise you to renew your business license today to prevent incurring excessive fines and penalties.
for more Info :- https://t.me/EthioEoDB/9
የመጀመሪያው ወር የቅጣት እድሳት ሊያበቃ 7 ቀን ብቻ እንደቀረው ያውቃሉ?
ለተጨማሪ ቅጣት ከመዳረጎ በፊት የንግድ ፍቃድዎን እንዲያድሱ እናሳስባለን።
ለተጨማሪ መረጃ፡- https://t.me/EthioEoDB/9
+++==================================================== +++
This is a polite reminder that only 7 days remain till the first month of penalty renewal for the Ethiopian fiscal year expires. If you haven't done, we strongly advise you to renew your business license today to prevent incurring excessive fines and penalties.
for more Info :- https://t.me/EthioEoDB/9
እስካሁን እድሳት ላላደሳችሁ የኢትዮጵያ በጀት ዓመት ተጠቃሚ ደንበኞቻችን ፤ የመጀመሪያው ወር የቅጣት እድሳት ሊያበቃ 8 ቀን ብቻ እንደቀረው ያውቃሉ?
ለተጨማሪ ቅጣት ከመዳረጎ በፊት የንግድ ፍቃድዎን እንዲያድሱ እናሳስባለን።
ለተጨማሪ መረጃ፡- https://t.me/EthioEoDB/9
+++==================================================== +++
This is a polite reminder that only 8 days remain till the first month of penalty renewal for the Ethiopian fiscal year expires. If you haven't done, we strongly advise you to renew your business license today to prevent incurring excessive fines and penalties.
for more Info :- https://t.me/EthioEoDB/9
ውድ ደንበኞቻችን የክፍያ ሥርዓታችን ላይ አሁን የቴክኒካል ችግር ተፈትቶልናል። ስለሆነም ክፍያ የተቸገራችሁ ደንበኞቻችን አሁን አገልግሎት በቴሌብር ወይም በንግድ ባንክ ባሉት አማራጮች መጠቀም የምትችሉ መሂኑን እንገልጻልን።
እናመሰግናለን።
+++ =================================== +++
‼️ Short Notice‼️
Dear customers, we were experiencing a technical problem with our payment system. But the problem is solved.

Thank You!
+++ ================================ +++
ለድጋፍ (for support) @motriHelpBot
ወይም
ለጠቅላላ መረጃ :- https://t.me/+XJLYynaaOrk3ZGI8
‼️ ማስታወቂያ‼️

ውድ ደንበኞቻችን የክፍያ ሥርዓታችን ላይ አሁን የቴክኒካል ችግር ገጥሞናል። ስለሆነም የሚመለከታቸው መ/ቤቶች እስከ ነገ ጠዋት ድረስ መፍትሔ እንደሚሰጡን በመተማመን በትዕግስት እንድትጠብቁኝ እንጠይቃለን።
እናመሰግናለን።
+++ =================================== +++
‼️ Short Notice‼️
Dear customers, we are currently experiencing a technical problem with our payment system. Therefore, we ask you to wait patiently, trusting that the concerned organization will give us a solution up to tomorrow morning.

Thank You!
+++ ================================ +++
ለድጋፍ (for support) @motriHelpBot
ወይም
ለጠቅላላ መረጃ :- https://t.me/+XJLYynaaOrk3ZGI8
See more posts

View in Telegram

Telegram Channel
TeleSearch Telegram Search