FBC (Fana Broadcasting Corporate) Telegram Channel

This is FBC’s official Telegram channel.

For more updates please visit www.fanabc.com

View in Telegram

Recent Posts

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአረጋዊያን እና ለአቅመ ደካሞች ማዕድ አጋርተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለአረጋዊያን እና ለአቅመ ደካሞች የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ ማጋራታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ማስታወቂያ!
እንኳን አደረሳችሁ!
የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 482/2013 የተቋቋመ ሲሆን፣ ዓላማውም ለገንዘብ አስቀማጮች የመድን ዋስትና ወይም ኢንሹራንስ ሽፋን በመስጠት ለፋይናንስ ዘርፉ ጤናማነት አስተዋጽኦ ማበርከት ነው፡፡ በዚህም መሠረት አይበለውና አንድ ባንክ ወይም ማይክሮፋይናንስ ተቋም ኪሳራ አጋጥሞት ለገንዘብ አስቀማጮች ገንዘባቸውን መመለስ ቢያቅተው፣ ፈንዱ ኪሳራ ያጋጠመውን እና የወደቀውን ባንክ ወይም ማይክሮፋይናንስ በመተካት ለእያንዳንዱ አስቀማጭ እስከ መቶ ሺህ ብር በፍጥነት የመመለስ ሃላፊነት አለው፡፡ ለገንዘብ አስቀማጮች የሚመለሰው ገንዘብም ከፋይናንስ ተቋማት የሚሰበሰብ ሲሆን፣ ለዚህም ሲባል እስካሁን ባለው ሁኔታ ከብር 4.6 ቢሊዮን በላይ አረቦን (premium) ተሰብስቧል፡፡

ፈንዱ የራሱን የፋይናንስ አቅም ለማሳደግና ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት፣ በየጊዜው የሚሰበስበውን አረቦን በሕግ አግባቡ መሠረት በመንግስት ግመጃ ቤት ሰነድ ላይ ኢንቨስት እያደረገ ይገኛል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251115571597 እና +251115578534 መደወል ይቻላል፡
በየአካባቢያችን አቅም ያጠራቸውን ወገኖቻችን ልናስባቸው ይገባል -አለሙ ስሜ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ልብስ ለብሰው ግን ደግሞ ሆዳቸው ባዶ የሆኑ አቅም ያጠራቸውን ወገኖቻችን በየአካባቢያችን ልናስባቸው ይገባል ሲሉ ተናገሩ፡፡ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ቁጥር 4 በመገኘትለአቅመ…

https://www.fanabc.com/archives/244882
የትንሳኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትንሳኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል። ባዕሉን በማስመልከት የሃይማኖት አባቶች ባስተላለፉት መልዕክት በዓለ ትንሳኤ የእግዚአብሄር ፍቅር መገለጫና የተስፋችን ማሳያ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል ብለዋል። በዓለ ትንሳኤውን ስናከብርም ለእግዚአብሄር ክብርና ለሰው ልጆች ደኀንነት በአንድነት በመቆም መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል። የትንሣኤ በዓል የክርስቶስን መነሣት ያስተማረን የምሥራች መሆኑንም…

https://www.fanabc.com/archives/244876
83ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ድል በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) -ኢትዮጵያውያን አርበኞች የጣልያንን ወራሪ ኃይል ድል ያደረጉበት 83ኛው የአርበኞች ድል በዓል አራት ኪሎ በሚገኘው የአርበኞች ድል መታሰቢያ ኃውልት በመከበር ላይ ይገኛል። በበዓሉ ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፣ አባት አርበኞች፣ እናት አርበኞች፣ የአርበኛ ቤተሰቦች፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።…

https://www.fanabc.com/archives/244877
መልካም የፋሲካ በዓል

#PMOEthiopia
በአዲስ አበባ በጎርፍ የተከበቡ 25 ሰዎችን መታደግ ተቻለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የጣለው ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ፍየል ቤት አካባቢ በተሽከርካሪ ውስጥ እንዳሉ በጎርፍ ተከብበው የነበሩ 25 ወገኖችን ጉዳት ሳይደርስባቸው መታደግ ተቻለ፡፡

በሌላ በኩል ከቀኑ 7 ሠዓት ተኩል ላይ በአዲስ ከተማ ወረዳ 8 መሳለሚያ የካቲት 23 ትምሕርት ቤት አካባቢ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ የነበረ ዕድሜው 35 የሚገመት ግለሰብን በሕይወት ማትረፍ መቻሉን የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ፋሲል ከነማ ሀድያ ሆሳዕናን 2 ለ1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሣምንት ፋሲል ከነማ ሀድያ ሆሳዕናን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

ምሽት 12 ሠዓት ላይ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው የፋሲል ከነማን ጎሎች ዣቪየር ሙሉ እና ምኞት ደበበ አስቆጥረዋል፡፡

እንዲሁም የሀድያ ሆሳዕናን ብቸኛ ጎል ደግሞ ዳዋ ሆጤሳ ከመረብ አሳርፏል፡፡

See more posts

View in Telegram

Telegram Channel
TeleSearch Telegram Search