Fasilo HD ታማኝ የመረጃ ምንጭ!
Recent Posts
ምዕራብ ወለጋ ገዳዮች ቤት ለቤት እየዞሩ የፈፀሙበት ጭፍጨፋ የሚያሳይ ቪዲዬ ለቀዋል
ይሄው እውነታው !
በደባርቅ ከተማ ተከስቶ የነበረዉ መጠነኛ የጸጥታ ችግር ወደነበረበት ሰላምና መረጋጋት ተመልሷል።
ረፋድ 2፡50 ገደማ በከተማዉ ቀበሌ 01 በምትገኘዉ የጎጢት ማርያም ቤተክርስቲያን የተከሰተዉን የእሳት ቃጠሎ ተከትሎ የተፈጠረዉ መጠነኛ የፀጥታ ችግር በአካባቢዉ ወጣቶች፣ በሃገር መከላከያ ሰራዊት፣ በአማራ ልዩ ሃይል፣ በአካባቢዉ ሚሊሻና መላዉ የአካባቢዉ ማህበረሰብ ባደረገዉ ብርቱ ጥረት ወደነበረበት ሰላምና መረጋጋት ተመልሷል፡፡ እሳቱም የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሏል፡፡
የመንግስት የጸጥታ መዋቅር ከአካባቢዉ ህዝብ ጋር በመቀናጀት አጥፊዎችን ለማሳዎቅና በቁጥጥር ስር ለማዋል ስምሪት ተሰጥቶ እየተሰራ ሲሆን፤ የጸጥታ ምክር ቤቱ የችግሩን ምንጭ፣ የደረሰበትን ዉጤት አስመልክቶ የሚሰጠዉን መግለጫ ተከታትለን የምናሳዉቅ ይሆናል፡፡
ይሁን እንጅ አካባቢዉ ጠላት በቅርብ ርቀት የሚገኝበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለጠላት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር በመሆኑ፤ ህዝባችን አብሮ የመኖር እሴቱን ለማጠናከር አጥፊዎች በህግ እንዲጠየቁ ከጸጥታ ሃይሉ ጋር በመቀናጀት ለአካባቢዉ ሰላምና መረጋጋት የበኩሉን እንዲዎጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
የሰሜን ጎንደር ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን
ሚያዚያ 20/2014 ዓ.ም
ደባርቅ።

የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ሁለት የቀድሞው መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ከእስር እንደለቀቀ የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የሽግግር መንግሥቱ የቀድሞው የካቢኔ ጉዳዮች ሚንስትር ካሊድ ኦማር እና የቀድሞው የሉዓላዊ ምክር ቤት አባል ሞሐመድ ሱሌማን ከእስር የተለቀቁት፣ የአገሪቱን ፖለቲካዊ ቀውስ ለማርገብ ሲባል እንደሆነ ተገልጧል። ኦማር እና ሱሌማን ከሌሎች ባለሥልጣናት ጋር የታሰሩት በኅዳሩ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ወቅት ነበር።
ዋዜማ ራዲዮ
ዋዜማ ራዲዮ
ፋኖማ አሸንፏል!
ፋኖ ሕዝቡን ከአደጋ ሲከላከል የከረመ ኃይል ነው። የትህነግን ወረራ ሲመክት ዛሬ በፋኖ ላይ ጥላቻ ሲነዙ የዋሉት ተደብቀው ነበር።
ከሳምንታት በፊት አንድ የፋኖ አባልን ሙስሊሞች የሚኖሩበት አዲስ ዓለም የተባለ ቦታ ቀጥቅጠው ገድለው ጣሉ። አላማቸው ፋኖ በስሜት ሄዶ በንፁሁ ሙስሊም ላይ ጥይት እንዲያዘንብና ግጭት እንዲነሳ ነው። ፋኖ አላደረገውም። ስሜታዊ አልሆነም። ሴራው ከሸፈባቸው።
ትናንት ያ ችግር ሲፈጠር ፋኖ አልወጣም። ግጭት ያባብሳል ሲሉ የፀጥታ ማስከበሩን ልዩ ኃይልና መከላከያ ሲወስድ ፋኖ የጦር ግንባርና ቤቱ ነበር። ለሁለተኛ ጊዜ ከሸፈባቸው።
ሁለት ሶስት ጊዜ ፋኖ የግጭት አካል እንዲሆን ፈልገው ሲከሽፍባቸው በስም ማጠልሸት ፈለጉ። ምን ያድርጉ አሸንፏቸዋላ።
ባለፈው ትህነግ ቤንሻንጉል ላይ የተፈፀመውን አማራ ክልል ላይ ነው ብሎ ዋሸ። ፋኖን ዋና ተጠያቂ አደረገ። ይሁንና አማራ ክልል አለመሆኑ ተገለፀ። ሳያፍሩ ቤንሻንጉል ውስጥም የአማራ ፋኖ አለ ብለው ሲቀባጥሩ ሰነበቱ። ወንጀሉን የፈፀሙት የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል አባላት መሆናቸው ታወቀ። ትህነግና አክራሪዎቹ በፋኖ ላይ፣ በአማራም ላይ ተመሳሳይ አቋም አላቸው። ለዛም ነው የአማራ ሙስሊም ሲጨፈጨፍ፣ ወሎ ውስጥ ቁርዓን ሲቃጠል፣ መስጊድ ሲነድ፣ ደረሳዎች ሲገደሉ ከእነዚህ ንፁሃንና ቅርሶች ይልቅ ትህነግ በልጦባቸው ዝም ያሉት። ዛሬም በአንድ ላይ የዘመቱት የጋራ አጀንዳ ስላላቸው ነው።
ፋኖ ግን ትህነግን በጦርነት፣ አክራሪዎችን በእርጋታው አሸነፋቸው። ጎትተው የሴራ አካል ለማድረግ ሊጥሩ ሲሞክሩ ሰተት ብሎ አልገባላቸውም። ቢያቅታቸው በሀሰት ከሰሱት። አሁንም በዝምታው አሸንፏቸዋል።
ቀን አክራሪዎቹ ስሙን ሲያነሱት ዋሉ። ምሽቱ ደግሞ የትህነግ ፈንታ ነው። በቀጥታ ስርጭት ፋኖን ስሙን ሊያጠፋ ነው። በነገራችን ላይ ከአዲስ አበባ ጎንደር መጥተው የባንክ ደብተር የከፈቱት ጎንደር በሚኖረው ጂሃር ሙሃመድ ሀጎስ ስም ነው። የእነ ጋሽ ሀጎስ ስጅ በኩል ጎንደር ላይ የሚፈጠርን ብጥብጥ እነ አሉላ ሰለሞን ሲያቦኩት ቢያመሹ ምን ይገርማል። የጋራ አጀንዳቸው ነው። ጎንደር ከተማ ውስጥ በሰላም እየኖረ የከተማውን ሰላም የሚነሳ በርካታ ትህነግና የፅንፈኞቹ አባል ሞልቷል።
ያም ሆኖ ግን ፋኖ አሸንፏል። በእነ ሞሃመድ ሀጎስ የወጣ የገንዘብ መሰባሰቢያና ሴራም ሆነ አዲስ አበባና ዋሽንግተን ሆነው ስሙን በሚያጠፉት የሚደረገው ቅንጅት በዝምታው ብቻ እየተሰባበረ ነው። በቅርቡ ደግሞ ብዙ መረጃዎች ይወጡ ይሆናል።
ፋኖ አባሉን ገድለው አዲስ ዓለም ላይ ሲጥሉ ባለመተኮሱ አሸንፏል። ትናንት ባለመተኮሱ አሸንፏል። ነገም ያሸንፋቸዋል።
አዲስ አበባ ላይ በፋኖ ሲጮህ የዋለውንና ምሽቱን በፋኖ የሚጮኸውን ጎንደር ላይ ሲያስተባብር የነበረው የጁሃር ሙሃመድ ሀጎስ አጎትን መልዕክት ይመልከቱ

በኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳለህ የተመራ ልኡክ በሩሲያ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛል።
በጉብኝቱ ላይም ከውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ በተጨማሪ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አማካሪ የማነ ገብረአብ ተገኝተዋል።
በጉብኝቱ ወቅትም የኤርትራ ልኡክ ከሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው ተነግሯል። በዚህም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ፤ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያደረገችው ባለው ጦርነት ዙሪያ ገለጻ ያደረጉላቸው ሲሆን፤ በዚህም የጦርነቱ መነሻ፣ የሩሲያ አቋም እና አሁን ያለበት ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከዚህ ቀደም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ሩሲያን ከሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ለማገድ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ኤርትራ ሩሲያን በመደግፍ ድምጽ መስጠቷ ይታወሳል። በተጨማሪም ኤርትራ በተለያ መንገዶች ለሩሲያ ያላትን አጋርነት ስንተልጽ መቆየቷ ይታወሳል።
(አል ዓይን)

Update‼️
በጎንደር ከተማ ትናንት የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር አስመልክቶ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
በጎንደር ከተማ ትናንት የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር በተመለከተ የክርስትና እና የእስልምና ሃይማኖት ተወካዮች እና ነዋሪዎች የተገኙበት ውይይት እየተካሄደ ነው። ውይይቱ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት ነው እየካሄደ የሚገኘው።

"ጥፋተኞች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው!"‼️
በጎንደር ከተማ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር በህይወትና አካል ጉዳት እንዲሁም በዘረፋ የተሰማሩት አካላት በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ የጸጥታ ምክር ቤት ገልጿል፡፡
ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ ግጭቱ በምንም ሁኔታ የሁለቱን እምነት ተከታይ ማኅበረሰብን የማይወክል ጥፋት መፈጸሙን አስታውቋል። ጥፋቱ የተፈፀመው በጥቂት ጽንፈኛና አክራሪ ግለሰቦች መሆኑን የጠቆመው መግለጫው የሁለቱን እምነት ተከታዮች ወደ ለየለት ግጭት ለማስገባት ሆን ተብሎ የተቀነባበረና የተመራ ሴራ መሆኑንም ጠቁሟል።
በዚህ እኩይ ተግባር ከሁለቱም የእምነት ተከታዮች የህይወትና አካል መጉደል እንዲሁም የንብረት መቃጠልና ዘረፋ ያጋጠመ ሲሆን በደረሰው ጉዳት የከተማ አስተዳደሩ ጥልቅ ሐዘን የተሰማው መሆኑንም ገልጿል፡፡
ጎንደርን ማቃጠል፣ መዝረፍና ማዋረድን ተልዕኮ ያደረገው ይህ እኩይ ተግባር በፀጥታ መዋቅሩ፣ በሁለቱም የእምነት አባቶችና ወጣቶች እንዲሁም በሀገር ሽማግሌዎች ጥረት የፈለጉት ጥፋት ሳይደርስ መቆጣጠር መቻሉንም አንስቷል።
በተፈጠረው ችግር ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተጠለሉ ሙስሊሞች እንዲሁም በመስጂድ ውስጥ የተጠለሉ የክርስትና አማኞች እንደነበሩና ከጥቃት የዳኑ መሆኑ ተረጋግጧል ብሏል መግለጫው።
የተፈጠረውን ቃጠሎም ሕዝቡ በነቂስ በመውጣት በከፍተኛ ርብርብ መቆጣጠር የቻለ ሲሆን አሁን አካባቢው ሙሉ በሙሉ ከፀጥታ መዋቅርና ከአካባቢው ነዋሪ ጋር በመተባበር የተረጋጋ ሰላም ለመፍጠር በሁሉም አካባቢ ስምሪትና ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።
እስካሁን ባለው ሁኔታ ከ9 በላይ ሰዎች መሞታቸው ፤ በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውን ፣ መስጂዶች እና ቤቶች ላይ ጥቃት መድረሱንም ምንጮች ጠቁመዋል።

ደራሲ ይስማከ ወርቁ የመኪና መገልበጥ አደጋ ደረሰበት‼️
ትናንት ሌሊት ሊነጋጋ አቅራቢያ 10:50 ላይ ደራሲ ይስማከ ወርቁ ከመገናኛ ወደ ላምበረት በሚወስደው መንገድ ወደ ቤቱ እያሽከረከረ ዲያስፖራ አደባባይ ላይ በምስሎቹ ላይ በሚታየው መልኩ የመኪና መገልበጥ አደጋ ደርሶበታል ። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን የሚዲያ ሀላፊና የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው ኮማንደር ማርቆስ ታደሰም የአደጋውን መድረስ ትክክለኛነት አረጋግጠውልኛል ።
ኮማንደር ማርቆስ አያይዘውም በደራሲው ላይ የደረሰው አደጋ ቀላል የሚባል እንደሆነና የካ ወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ተወስዶ ህክምና ከተደረገለት በኋላ ለተሻለ ህክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዱን ነግረውኛል ። በሌላ ምንጭ በይስማከ ላይ የደረሰው አደጋ በእጁ ፣ በደረቱና በጭንቅላቱ ላይ ሲሆን የተወሰደውም ወደ ዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል መሆኑ ተገልጾልኛል ። ይሁንና ደራሲው በአሁኑ ወቅት ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገለት ይገኛል ። ይህ የመኪና አደጋ ሲደርስበት ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

ለአርበኛ ዘመነ ካሴ ድንቅ መልስ ስንት ላይክና ሼር ልጠብቅ?
የቢቢሲ ጋዜጠኛው ስንት ፋኖ ምን ያህል ትጥቅ አላችሁ አላለም🤣አርበኛ ዘመነ ካሴ ለቢቢሲ የሰጠውና እንዲጠፋ የተደረገው ቃለ ምልልስ ሙሉውን ያድምጡት👇
https://youtu.be/4t7Anhv99gA

እኛው ነን!
--------------
© ዘመነ ካሴ
ጎንደሬነት አማራነት!
ጎንደሬነት ክርስቲያንነት፣ ሙስሊምነት፣ ይሁዲነት!
ጎንደሬነት አብሮነት፣ ረቂቅነት!
ጎንደሬነት አንድነት፣ ኢትዮጲያዊነት!!
*******
የአብይ ጅኒ በክብር ተቀምጦ ከቆየበት ክፍሉ አንድ ባንድ መለቀቅ ጀምሯል እንጅ ትናንትም ዛሬም ነገም እኛው ነን። የሞትንም፣ የዳንም፣ ያዘንም እኛው ነን። ...አንድ ቀን ሁሉንም መሰናክል በንቀት ዘለነው በድል፣ በኩራት እንቆማለን!!
ድል ለአማራ ህዝብ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
[ክፋት ለማንም፣ በጎነት ለሁሉም]
/አዲስ ትውልድ፥አዲስ አስተሳሰብ፥አዲስ ተስፋ!/
@ዘመነ ካሴ

የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር በምሽግ ሰባሪው ሻምበል አዛዥ ፋኖ ጌጡ ይግዛው (ኮማንዶ ) ድንገተኛ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለጸ፤ መላው የአማራ ፋኖ አባላት በሙሉ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በአፅንኦት አሳስቧል።
የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የሰጠው መግለጫ:_
በምሽግ ሰባሪው ሻምበል አዛዥ ፋኖ ጌጡ ይግዛው (ኮማንዶ ) ድንገተኛና ነውረኛ ሞት የተሰማን ሃዘን መሪር ነው።
ፋኖ ጌጡ (ኮማንዶ ) ማነው?
እንዴትስ ተሰዋ ?
ፋኖ ጌጡ ይግዛው የአማራ ፋኖ ካፈራቸው ሰራዊቶች መካከል እንቁና ቁርጠኛ የፋኖ አባላት መካከል አንዱ ነበር።
ይህ የፋኖ ሰራዊት የህወሓት ወራሪ ቡድን ጦርነት በከፈታቸው የአማራ ክልል ግንባሮች ሁሉ ታላቅ ጀብድ የፈፀመ ከሁለት እስከ ሶስት ግዜ በላይ በጠላት ጥይት የቆሰለ።
በታጋይ ጓዶቹ እጅግ ተወዳጅና ተስፋ የተጣለበት ወጣት የፋኖ ሰራዊት አባል ነበር።
ፋኖ ጌጡ ይግዛው (ኮማንዶ ) በቀን 16/08/2014 በጎንደር ከተማ ከምሸቱ ሁለት ሰዓት ገደማ ተሰዋ። እንዴት? በማን ተሰዋ?
የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር አመራሮች ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ጋር ባደረጉት የጋራ የሆነ አገራዊ ውይይት መካከል አንዱ በጎንደር ከተማ የፋኖ አባላት የጦር መሳሪያ ይዘው መንቀሳቀስ ባይችሉ ከተማዋ የኢኮኖሚ እድገት ከፍ ሊል ይችላል የሚለው ሃሳብ ገዥ ስለነበረ የፋኖ አመራሮች በደረሱት ስምምነት መሰረት አባላት የጦር መሳሪያ ይዘው መንቀሳቀስ እንደሌለባቸው በተሰጣቸው መመሪያ መሰረት ህግና ስርዓት ካከበሩ የፋኖ አባላት መካከል ፋኖ ጌጡ አንዱ ነበር።
ሆኖም ግን የደህንነት ስጋት ያለባቸውን ፋኖች በስም ዝርዝር ተዘርዝሮ ለጎንደር ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች መምሪያ ህጋዊ በሆነ መልኩ የጦር መሳሪያ ይዘው የሚንቀሳቀሱበትን መንገድ ከተጠየቀላቸው የፋኖ አባላት መካከል ፋኖ ጌጡ አንዱ ነበር።
ሆኖም ግን ተቋሙ ምንም ዓይነት ሚሊሻ አልሰጠም።
ፋኖ ጌጡ ባዶውን እያለ ነው የተገደለው፤ የተገደለውም በጎንደር ከተማ የሚሊሻ ጽህፈት ቤት የሚሊሻ አባል ነው። የጦር መሳሪያውም የመንግስት ነው።
ሌላው የሚገርመው ነገር ችግሩ እንደተፈጠረው ወዲያው በከተማዋ ምንም ዓይነት የፀጥታ ሃይል አልነበረም። ለምን? ችግር ሲፈጠር ችግሩን ማረጋጋት ያለበት ማነው? ፍርዱን ለህዝብ!!
ከዚህ ጋር ተያይዞ ከነበረው ስሜት አንፃር አንዳንድ የፋኖ አባላት የሚታገሉለትን ህዝብ በጥይት ተኩስ መረበሻቸው ይቅርታ እንጠይቃለን?
የጀግናውን የቀብር ስነ-ስርዓት ላደማቃቹህና ሃዘናችን ለተጋራቹህን የህብረተሰብ ክፍሎች በሙሉ ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው።
ለመላው የአማራ ፋኖ አባላት በሙሉ ጥንቃቄ እንድታደርጉ በአፅንኦት እናሳስባለን!
ለቤተሰቦቹና ለወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን እንመኛለን!
ከአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ስራ-አስፈፃሚ
አርበኛ ይሞታል
የሞተበት ዓላማ ይቀጥላል!

ሰበር መረጃ❗️
አማራ የሆንክ ሁሉ በአስቸኳይ ላይክና ሼር አድርግ❗️
ቢቢሲ ከቀናት በፊት አርበኛ ዘመነ ካሴን ኢንተርቪው አድርጎ ነበር።ነገር ግን የሚፈልገውን ነጥብ ለማስጣል ባለመቻሉ ኢንተርቪውን ሳያስተላልፍ ሰርዞታል።የመረጃ አነፍናፊያችን ይህንን የ25 ደቂቃ ቃለ ምልልስ የድምፅ ቅጂ ካለበት አምጥተው ልከውልናል።አርበኛ ዘመነ ካሴ ያደረገውን ሙሉ ቃለ ምልልስ በዚህ ሊንክ ታገኙታላችሁ👇

የመግቢያ ውጤቱ እስኪፈተሽ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜ እንዲራዘም የአማራ ትምህርት ቢሮ ጠየቀ
በ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው ወደዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ውጤት ተፈትሾ መተማመኛ ላይ እስኪደረስ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ጊዜው እንዲራዘም ተጠየቀ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ለትምህርት ሚኒስቴር በፃፈው ደብዳቤ ጠይቋል።
የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ እጅግ በጣም ሰፊ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎቻችን ውጤታቸው እንደገና እንዲፈተሸላቸው እያመለከቱ መሁኑን የገለፀው የክልሉ ትምህርት ቢሮ በተጨማሪ በትምህርት አመራሩና በትምህርት ማህበረሰቡ ዘንድም በርካታ ጥያቄዎች እየተነሱ መሆኑን ቢሮው አትቷል። የተማሪዎች ውጤት በአግባቡ ተፈትሾላቸው ተገቢው መተማመን እስኪፈጠር ድረስ የተማሪዎች መግቢያ ቀን ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ቢሮው በደብዳቤ ትምህርት ሚኒስትርን ጠይቋል፡፡
ለፈጣንና ለሀቀኛ መረጃዎች ቤተሰባችን ይሁኑ!
የቴሌግራም ገፃችንን ይጎብኙ👇
https://t.me/FasilAmhara
የፌስቡክ ገፃችንን ይከታተሉ👇
https://www.facebook.com/110194134211057/posts/421046496459151/?substory_index=0&app=fbl
ዝርዝር መረጃዎችን በዩቲዩብ ቻናላችን ይከታተሉ👇
https://www.youtube.com/channel/UC5uxO6rNeYuNCcGXgM2gQHA