Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች Telegram Channel

The interest of this Channel is giving continuous information about housing projects (40/60&20/80) & other Real Estates Updates.

View in Telegram

Recent Posts

#እንድታውቁት#AddisAbaba

በመንገድ ኮሪደር ልማትና በአስፓልት የማንጠፍ  ስራ ምክንያት  ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ የሚወስደው ዋናው መንገድ በከፊል ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

መዚህ መሰረት ፡-

- ከለገሐር በመስቀል አደባባይ  ወደ ቦሌ አየር መንገድ

- ከእስጢፋኖስ በቀጥታ ወደ ቦሌ  አየር መንገድ

- ከኡራኤል በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ

እንዲሁም #በውስጥ_ለውስጥ ወደ ዋናው ቦሌ አየር  መንገድ የሚወስዱ መንገዶች ከዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ #በየዕለቱ  ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ከቀኑ 8:00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12:30 ሰዓት ለተሽከርካሪ በከፊል ዝግ ይሆናሉ።

አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥማቸው ሌሎች  አማራጭ መንገዶችን መጠቀም እንዳለባቸው  አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
Downloaded via:
@downloader_tiktok_bot
የመጀመሪያ ዙር የማህበር ቤት ተጠባባቂዎች ዳግም ምዝገባ እስከሚቀጥለው ሰኞ መራዘሙ ተገለፀ

የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በከተማዋ የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመፍታት ከሚከተላቸው አማራጮች መካከል የማህበር ቤት ግንባታ አንዱ ነዉ።

በዚህም መሰረት ቢሮዉ ፍላጎት እና አቅሙ ያላቸውን  የ20/80 እና የ40/60 የቤት ልማት ተመዝጋቢዎችን በህብረት ሥራ ማህበር ማደራጀቱ የሚታወቅ ነዉ።

በመሆኑም ከዚህ ቀደም ሲደረጁ ተጠባባቂ የነበሩ የመጀመሪያ ዙር ተመዝጋቢዎች ለማደራጀት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎችን እና ዶክመንቶችን አሟልተው ለቀረቡ ተጠባባቂ ግለሰቦች ለተከታታይ አምስት ቀናት ዳግም ምዝገባ ሲያካሂድ የቆየ ሲሆንና ትላንት ቢጠናቀቅም ነገር ግን መረጃ ሳይደርሳቸው ቆይተው  ተንጠባጥበው እየመጡ ያሉ ተመዝጋቢዎች በመኖራቸው እስከ ቀጣይ ሰኞ ማለት አስከ 26/09/16 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን የቢሮው የማህበር ቤት ዳይሬክቶሬት ገልጿል።

ለሁለተኛ ዙር ተጠባባቂዎችንም በቀጣይ ምዝገባ እንደሚካሄድ ቢሮው ገልጿል።
ከመገናኛ አዲሱ ገበያ በሚኒባስ ታክሲ ሲስጥ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በብዙሀን ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ ተደረገ። (ኢትዮ ኤፍኤም)

ቀደም ብሎ በትራንስፖርት አሰጣጡ ላይ ሲታይ የነበረው ችግር ለመቀረፍ የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ ምላሽ መስጠቱን ገልጿል።

በየካ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስር አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ከመገናኛ - አዲሱ ገበያ የጉዞ መስመር በሚኒባስ ታክሲ ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በብዙሀን ትራንስፖርት አገልግሎቱ እንዲሰጥ መደረጉን ነው የተገለጸው።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ዳዊት ዘለቀ ህብረተሰቡ ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር በተገናኘ በዋናነትም ከማቆራረጥና ከታሪፍ በላይ ማስከፈል ጋር ተያይዞ በመስመሩ የሚስተዋለውን ችግር ተለይቶ መፍትሔ ተሰቶታል ብለዋል።

ኃላፊው አክለውም አገልግሎቱ በብዙሀን ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ በሆኑት የአደይ አበባ አውቶብስ፣ ቅጥቅጥ አውቶብሶች እንዲሁም የከተማ አውቶብሶችን ጨምሮ በድምሩ 32 የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችን መድቦ ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል ብለዋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ኢትዮ ኤፍኤም
#Addis_Ababa_City_Bus
#AddisAbaba

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ በግንባታ ላይ ከነበረ ህንጻ አጠገብ ያለ ቤት ውሃልክ እና አፈር ተደርምሶ የአንድ ወጣት ህይዎት አልፏል።

አደጋው የደረሰው ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 በተለምዶ " የረር ጉሊት " ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ነው።

በግንባታ ስራ ላይ የነበሩ ሰራተኞች ከአጠገቡ ዳገት ላይ የነበረ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ውሃ ልክ እና አፈር ተደርምሶ የ28 ዓመት ወጣት ህይወት አልፏል።

አደጋው መፈጠሩ ከተሰማ ጀምሮ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ሰራተኞችን ህይዎት ለመታደግ ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸው ተነግሯል።

በቅርቡ የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፤ ከተማዋ ውስጥ በአደጋ የሚከሰት ሞት ከባለፈው ዓመት ሲታይ ዘንድሮ መጨመሩን ፤ በብዛት የሞት አደጋ እየደረሰባቸው ያሉት ደግሞ የቀን ሠራተኞች መሆናቸውን ጠቁሞ እንደነበር አይዘነጋም።

በትናንትናው እለት በተከፈተው የሊዝ ጨረታ በቅርቡ በፈረሰችው ፒያሳ ሰፈር አካባቢ ለአንድ ካሬ ሜትር ቦታ 350ሺህ ብር በማቅረብ አዋሽ ባንክ ቦታውን ተረከበ። አዋሽ ባንክ በአራዳ ዲስትሪክት 977 ካሬ ሜትር ቦታ 311,000 ብር በማቅረብ ሙሉ ክፍያ ፈፅሟል።

A plot of land received a 350,000 Br for a square metre during a lease auction held yesterday for plots surrounding the recently demolished Piassa neighborhood. Awash Bank emerged highest bidder, eyeing a 977Sqm plot in the Arada District for 311,000 Br, committing to full upfront payment.

Read more https://ow.ly/7OW050RS8J1
             ማስታወቂያ

በጋራ መኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር ለመደራጀት ተመዝግባችሁ በቀን 4/8/2016ዓ.ም  በተደረገላችሁ ጥሪ  መሰረት የባንክ ስቴትመንት ያቀረባችሁ በሙሉ ባምቢስ ከግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ከጋራ መኖሪያ ቤት ማህበራት ዳይሬክቶሬት 6ኛ ፎቅ ቅጽ 01 በመውሰድ በምትኖሩበት ወረዳ እንድታስሞሉ እና በሶስት የስራ ቀናት ውስጥ /ከ14 - 16/09/2016 ዓ.ም/ መረጃ እንድታሟሉ እናሳውቃለን።
የመኖሪያ እና የንግድ ቤት ጨረታ የውል ማዋዋያ ጊዜ የማስተካከያ መርሀ ግብር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ እና የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የመኖሪያና ንግድ ቤት ጨረታ በማውጣት የአሸናፊዎችን ስም ዝርዝር በጋዜጣ የአሳወቀ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም አንደኛ ደረጃ አሸናፊዎች በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ግሪክ ስኩል ፊት ለፊት ወይም ባንቢስ በሚገኘው አዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የውል አገልግሎት መስጫ ማዕከል ግራውንድ ወለል ላይ በመገኘት ከዚህ በታች በቀረበው የውል ድርጊት መርሀ ግብር መሰረት ከግንቦት 14/2016 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00-11፡00 ሰዓት የምትዋዋሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች ለውል ሲመጡ ሊያሟላቸው የሚገባ ቅድመ ሁኔታዎች

✓ የጨረታ አሸናፊው በአካል መቅረብ ✓ የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ዋና እና 2 ኮፒ ✓ የጋብቻ የምስክር ወረቀት ዋና እና 2 ኮፒ ✓ ያላገባ ከሆነ

6 ወር ያላለፈው የምስክር ወረቀት

✓ ያገባ ከሆነ

የትዳር አጋር የታደሰ የምስክር ወረቀት 2 ኮፒ ✓ ውክልና ከሆነ

• የወካይ መታወቂያ 2 ኮፒ

• የተወካይ መታወቂያ ዋና እና 2 ኮፒ

• የውክልና ማስረጃ ዋና እና 2 ኮፒ

✓ ወቅታዊ 4x4 የሆነ 4 ጉርድ ፎቶ ግራፍ

ፒያሳ_ሰባ_ደረጃና አካባቢዋ
ፒያሳ_ሰባ_ደረጃና አካባቢዋ
See more posts

View in Telegram

Telegram Channel
TeleSearch Telegram Search