ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና – Zehabesha News Telegram Channel

@Zehabeshanewsbot
Contact us – @@EthiopiaI
ዘ-ሐበሻ የኢትዮጲያና ኢትዮጲያዊነትን ሁለንተና የሚቃኝ፣ የሀገርንና የህዝብን ጉዳዮች በብዙ መንገዶች ተደራሽ የሚያደርግ፣ በርካታ ዝግጅቶችና አቀራረቦች ያሉት የሚድያ ተቋም ነው።

View in Telegram

Recent Posts

በጣም ይቅርታ ከበራችሁ ላይ ቆሜ ስላቆምኮት🙏.
እኔ ዳንኤል እባላለሁ እዚህ እናንተ ፋብሪካ ብትቀጥሩኝ በታታሪነት እሰራለሁ ደሞ ቴክኒካል ስራ ጎበዝ ነኝ አልታክትም አልኩ ወ/ሮ ዛፍ ትንሽ ለነፋስ ዝቅ ባደረገችው የመኪናዋ መስታወት:: እጅግ ጠባብ ክፍተት ስለነበረ ስራ የማግኘቴ እድልም የዛኑ ያህል ጠባብ እንደሆነ እያወኩ::
መስታወቱን ዝቅ አድርጋ እይ...እኔም ብትቀጠር ደስ ይለኝ ነበር ነገር ግን ቀጥረን ጨርሰናል እንደውም ተጠባባቂ ብዙ ሰው ተመዝግቡአል:: እባክዎ የመጨረሻ ተጠባባቂ ሆኜ ልመዝገብ?? 🙏🙏 እሺ ትችላለህ:: አስገቡትና ከፀጋዬ ጋር ይገንኝ ብላ ገባች::
ለinterview ፋርማሲስት ፀጋዬ ቢሮ እንደ ገባሁ
እሺ እንኳን ደህና መጣህ ማን ልበል? አለኝ
ዳንኤል ሃይሉ እንዳለ እስከ አያት ካልጠራሁ የሚጥለኝ ስለመሰለኝ:: የት ትሰራ ነበር? የስራ ልምድ? እስኪ ስለ ራስህ ተናገር....
እኔ የስራ ልምድ የለኝም ተቀጥሬ መስራትም አልፈልግም ነበር ግን እዳሰብኩት አልሆን አልሳካ አልሞላልህ ስላለኝ በቃ ለመቀጠር ወሰንኩ ስለው አግብተሃል? ሲል አይ አላገባሁም አንተስ አግብተሃል? ብዬ ስጠይቀው እየሳቀ የጠየኩህን ብቻ መልስ ሲለኝ አይ እኔም የቀጣሪዬን ማንነት ማወቅ ስላለብኝ ነው አልኩት::
ወይ ጉድ ለመሆኑ ስንት አይነት welding ታውቃለህ? እኔ ከ30 በላይ ናችው ልዘርዝርልህ? ስለለው እንዴ... ከዚህ በፊት የተቀጠሩት በሙሉ 7 ወይም 8 አይነት ነው ያለው ያሉት አለና በፋብሪካው ውስጥ የነበሩትን ቻይናውያን ኢንጂነሮች በአሰተርጏሚ ሰፋ ያሉ ጥያቄዎች እንዲጠይቁኝ አስደርጎ የዛኑ እለት ተቀጥሬ ማምሻውን ከሌሎች ሰራተኞች ጋር በሰርቪስ ተመለስኩ:: ማንበብ መዘጋጀት መጣጣር መሞከር ከተጠባባቂዎቹ ብቻ ሳይሆን ቀድመውኝ ከተቀጠሩትም በተሻለ ደሞዝ እና የስራ ሃላፊነት እንዲኖረኝ አድርገውኛል::
ለ1 አመት ከ6 ወር ሳልቀር ሳይደክመኝ ሳልሰለች ከራሴ እና ከቻይናውያን ጋር እየተወዳደርኩ እየተፎካከርኩ ሰራሁ:: በራሴ ፈቃድ እረፍት ለራሴ ከለከልኩት::
የስራ ቦታው ገላን የምኖረው ኮተቤ ስለነበር በሰርቪስ ስጏዝ ጠዋትም ማታም እያነበብኩ በወር 2 እና 3 መፅሃፍት እጨርስ ለበር::
SINO እየሰራሁ ለመጨረሻ ጊዜ ያነበብኩት መፅሃፍ እንብቤ እንደጨረስኩ ከSINO-ETHIOPIA PHARMACEUTICAL እንድለቅና የራስ የሆነውን እራስን የሚያስችለውን ቀድሞም የነበረኝን የተዳፈነ ብርቱ ፍላጎት አቀጣጥሎታል:: /The Burden of Freedom Dr Myles Monroe/.
የመፅሃፋ የመጨረሻ ገፆች ላይ ነኝ
የ ሳይኖ-ኢትዮጵያም እንዲሁ:: በጠዋት ደርሰን ሁሉም ሰራተኞች ወደ ፋብሪካው ሲሄዱ የመፅሃፋን የመጨረሻ ገፅ ወደ ወ/ሮ ዛፍ ቢሮ እየሄድኩ ለ3ኛ ጊዜ በምናቤ አነበብኩ:: ከቢሮዋ እስፈቅጄ ግባሁ:: ሰላም እዴት ነህ? ምነው በጠዋት? አለችኝ
ውስጤ " በርታ አዎ ወስን ሳይመሽብህ በጠዋት ጉልበትህም ሳይዝል በወጣትነትህ ዛሬ ወስን ዛሬ ከወሰንክ ነገ የተሻለ ቀን ይሆንልሃል አትፍራ" ሲለኝ
ውጩ " ምን አለህ? በምን ልትኖር ነው? መናጢ ደሃ እንደሆንክ አትርሳ ዘመድ የለህ ገንዘብ እላስቀመጥክ ያሳለፍከውን ችግር እንዴት ትደግመዋለህ" ቢለኝም
በቃ ውስጤን ሰማሁት
ላደረግሽልኝ ነገር ሁሉ አመሰግናለሁ:: ከዛሬ ጀምሮ ስራ አቁሚያለሁ:: የራሴን ስራ ለመስራት ወስኛለሁ ሌላ ቦታ ልቀጠር አይደለም:: በነበረኝ ጊዜ ሁሉ ደስተኛ ነበርኩ:: እግዜር ያክብርሽ ብዬ በንግግር እና በድርድር ሃሳቤን እንዳታስቀይርኝ በማለት በቶሎ ከቢሮዋ ወጣሁ::
የስራ ባልደረቦቼም በውሳኔዬ ግራ ተጋብተዋል ክሊራንስ አዙሬ ደሞዜ ተቀናንሶ ታስቦ 2 ብር ከ 70 ሳንቲም በፖስታ ታሽጎ ከድርጅቱ Casher አበባ እጅ ትቀብዬ እነ ኢንጂነር አለማየሁ : እነ ቤዛ :ዬሴፍ : እነ ሚ/ር ዋንግን በሉ ቻው ብዬ ትሰናበትኩ::
ወ/ሮ ዛፍ የተከበረች ብርቱና ታታሪ ስትሆን አንቺ ብለን እንደ እናት ስለምንጠራት እንቺ እያልኩ ፅፌያለሁ:: በዚሁ አጋጣሚ ምስጋናዬም ይድረስልኝ:: ያኔ በወጉ ሳላመሰግን እንዳለፍኩ አሁን እድሜዬ ሲገፋ ታውቆኛል::
ወጣቶች ከውጩ ይልቅ ውስጣችሁን ስሙ ሳይመሽ አሁን ወስኑ::
ይቅናችሁ🙏🙏🙏
የህዝብን የጋራ ትውስታ (collective memory) ማጥፋት

ከሰሞኑ እድሜ ጠገቡ እና የብዙ እኩያዎቻችን እና ታላላቆቻችን የጋራ ትውስታ ስፍራ የነበረው እንዲሁም በቅርስነት ተመዝግቦ የቆየው ሎምባርዲያ መፍረሱ መነጋገርያ ሆኗል። ታላቁ ነጋዴ፣ ዲፕሎማትና ኢትዮጵያን ወዳጅ የነበሩት ሼክ አሕመድ ሷሊህ ህንጻውን ያስገነቡት በ1926 ዓ.ም እንደነበር ታሪክ ይነግረናል።

ሼክ አሕመድ ሷሊህ አልዛሕሪ በ1873 በየመን የተወለዱ በ1903 ኢትዮጵያ በመምጣት በንግድ ሥራና በሀገር ልማት ክብርና ሞገስ ያገኙ ሰው ነበሩ፡፡ ጣሊያን አገራችንን በወረረበት ዘመን ተቃውሟቸውን በማሰማት በተሌግራምና የተለያዩ ጽሑፎችን አባዝተው በመበተን ለኢትዮጵያ ታግለዋል፡፡ ለአርበኞች በድብቅ መሣሪያ በማቀበል የሕቡዕ አርበኛ ሆነውም ነበር፡፡

በሥራቸው የተበሳጨው ጣሊያን በወቅቱ ንብረታቸውን በሙሉ ወርሶባቸዋል፡፡ ንጉሡ ወደ ሀገር ከተመለሱ በኋላ በአዲስ አበባ ፒያሳ ፣እሪ በከንቱ፣ በአዋሽ ፣በአዳማ ፣በድሬዳዋ በአጠቃላይ ሁሉም ንብረቶቻቸው እንዲመለሱ አድርገውላቸዋል፡፡

ሆኖም በደርግ ዘመን 99 የሚደርሱ መጋዘንና ሕንፃዎቻቸው ብሎም ሌሎች ንብረቶቻቸው በሙሉ ተወርሰው ሸበሌ አካባቢ ያለው ቤታቸውና ሎምባርዲያ የሚገኝበት ሕንፃቸው እንዲመለስላቸው ተደርጎ ነበር፡፡

ከሰሞኑ አፍራሾቹ ከሕንጻው አጠገብ ወደ ሸበሌ የሚያልፈውን የእግረኛ መንገድ የሚያሰፉ መስለው ሲነሱ በህጋዊ ማህተም ነበር ከነንግድ እንቅስቃሴው ያሸጉት። ከዛ ከአንድ ወር በኋላ ባለፈው አርብ ማታ የፀሃይን መጥለቅ ተገን በማድረግ ተከራዮችን ሆን ብለው በድንገት በስልክ ''ኑ እቃ አውጡ፤ ቤቱ ሊፈርስ ነው'' አሏቸው።

በቀን ከሆነ ግርግር ሊነሳ ስለሚችል ነው ተብሎ ሊታሰብ ይችላል፣ ባለሱቅ በሙሉ ከያለበት ተጠዳድፎ ከምሽቱ 1:00 አካባቢ መጥቶ ከፋፍቶ ሲገባ መብራት ቆረጡባቸው። በእጅ ባትሪ እንደምንም ያላቸውን ዋና ዋና እቃ ለማስወጣት ሲሞክሩ ደግሞ ህንጻውን በላያቸው ማፍረስ ጀመሩ። በዚህም 4 ሰዎች ከባድ አደጋ የደረሰባቸው ሲሆን አንደኛው ሆስፒታል ሲደርስ ህይወቱ አልፏል። የሰዎቹ የአካል ጉዳትም ሆነ ሞት ግን ተደብቋል።

ይህ ነው የሰሞኑ የአዲስ አበባ የመንገድ ዳር 'ልማት' ውጤት። ለአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ተብሎ በከተማዋ እንግዶች በሚያልፉበት አቅጣጫ ሁሉ የ ''ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ'' አይነት ስራ እየተሰራ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ የብዙ ሰው እንጀራ እና ሕይወት ተመሰቃቅሏል።

ሌላው እዛው ሸበሌ ፊትለፊት የሚገኘው የአ/አ ዩኒቨርስቲ የንግድ ሥራ ት/ቤት (ኮሜርስ) ከነዛ ውብ ሕንፃዎቹ ጋር ፈርሶ ለአንድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ መገንቢያ ሊሰጥ አሁን ዙሪያው በግንባታ ማስጀመሪያ አጥር መከለሉ ታውቋል።

እንደ ኒውዮርክ፣ ለንደን፣ ቶክዮ ያሉ ከተሞች እንኳን ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎቻቸው ስር ህዝባቸው collective memory ያለባቸውን ቅርሶች ጠብቀው አቆይተዋል፣ አሁን ድረስ የህዝቡን ታሪካዊ እሴት ለመጪው ትውልድ ያስተላልፋሉ፣ እናት እና አባቶቻቸው ያሳለፉባቸውን ግዜያት እያስታወሱ ይኖራሉ።

"እና ልማት አይኑር ነው የምትለው?" አይነት ጉንጭ አልፊ ጥያቄ አይጠፋም። እርግጥ ነው ልማት ያስፈልጋል፣ በዚህ ወቅትም የሚፈርስ እና ቦታ የሚለቅ ይኖራል። ነገር ግን የህዝብ የጋራ ትውስታ ቦታውችን በማጥፋት የሚመጣ ልማት ምን ሊጠቅም? በቅርቡ እያቀረብኳቸው እንዳሉት አይነት መሬት በህገወጥ ወረራ መያዝ በተስፋፋበት ግዜ በቅርስነት የተመዘገበ ሀብትን ማፍረስ አይጋጭም?

የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣንስ ስራው ምን ይሆን?
via EliasMeseret
በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ከወሰዱ 845 ሺህ ገደማ ተማሪዎች መካከል፤ ወደ ዩኒቨርስቲ የማለፊያ ነጥብ ያመጡት ተፈታኞች ብዛት 27,267 ተማሪዎች አሊያም 3.2 በመቶዎቹ ብቻ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ካስፈተኑ 3,106 ትምህርት ቤቶች መካከል፤ 1,328ቱ አሊያም 42.8 በመቶ የሚሆኑት አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ይፋ አድርገዋል።
ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በመግለጫቸው " 5 ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸው ተማሪዎች ሙሉ ለሙሉ አሳልፈዋል፡፡ " ብለዋል።

ሌሎች 5 ትምህርት ቤቶች ድግሞ ካስፈተኗቸው ውስጥ 95 ከመቶ ተማሪዎቻቸውን እንዳሳለፉ ገልጸዋል።

ከፍተኛ አፈጻጻም ያሳዩ አስር ትምህርት ቤቶች (በደረጃ)፦

1. አዲስ አለማየሁ አዳሪ ትምህርት ቤት (ደብረማርቆስ)
2. ደሴ አዳሪ ትምህርት ቤት
3. ባህርዳር ስቴም ትምህርት ቤት
4. ሀይራንዚ አዳሪ ትምህርት ቤት (ስልጤ ዞን)
5. ሊች ጎጎ አዳሪ ትምህርት ቤት (ሀድያ)
6. ኦዳ አዳሪ ትምህርት ቤት (አዳማ)
7. ኮተቤ ሼርድ ካምፓስ
8. የኔታ አካዳሚ
9. ወላይታሊቃ አዳሪ ትምህርት ቤት
10. ቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት
አማራ ክልል ዛሬ የተሰጠው ሹመት
     👇
1.አቶ አብዱ ሁሴን የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር
2.ዶክተር አህመዲን መሐመድ  በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ ኅላፊ 
3.ዶክተር ድረስ ሳህሉ  በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኅላፊ
4.ዶክተር ሙሉነሽ ደሴ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማእረግ የማሕበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኅላፊ
5.አቶ ደሳለኝ ጣሰው በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአስተዳደር ጉዳዮች አስተባባሪ እና የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኅላፊ
6.ዶክተር ጋሻው አወቀ የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ ኅላፊ
7.አቶ ብርሃኑ ጎሽም የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ኅላፊ
8.ዶክተር መንገሻ ፈንታው የአማራ ክልል ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኅላፊ
9.ዶክተር ስቡህ ገበያው የአማራ ክልል ሥራ እና ስልጠና ቢሮ ኅላፊ
10.አቶ ክብረት አህመድ የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኅላፊ
11.አቶ አብዱልከሪም መንግሥቱ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኅላፊ
12.ዶክተር ደመቀ ቦሩ የአማራ ክልል ፕላን እና ልማት ቢሮ ኅላፊ

ከላይ የተጠቀሱት ተሿሚዎች በእጩነት የቀረቡ ሲሆን ሌሎቹ ተቋማት ባሉበት እንደሚቀጥሉ ርእሰ መሥተዳድሩ ገልጸዋል፡፡

የምክር ቤት አባላቱ በእጩ ተሿሚዎች ላይ ሰፊ ውይይት እና ምክክር ካደረጉ በኋላ ሹመታቸውን አጽድቀዋል፡፡
          አሚኮ
                
ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News pinned «የአማራ ክልል ምክር ቤት - ሹመት አፀደቀ 1. ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ ተሹመዋል። የኢንተርፕራይዞች ሃላፊ የነበሩ ሲሆን የርዐሰ መስተዳደር ይልቃል ከፋለን ቦታ ተረክበዋል። 2. ደሳለኝ ጣሳው የአስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ ሲሾሙ የሰማ ጥሩነህን ቦታ ተክተዋል። ሲሰሩ የነበሩበት የክልሉ ጸጥታ ሃላፊ በመሆን ነበር። 3. ዶ/ር ድረስ ሳህሉ የባህርዳር…»
የአማራ ክልል ምክር ቤት - ሹመት አፀደቀ


1. ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ ተሹመዋል። የኢንተርፕራይዞች ሃላፊ የነበሩ ሲሆን የርዐሰ መስተዳደር ይልቃል ከፋለን ቦታ ተረክበዋል።
2. ደሳለኝ ጣሳው የአስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ ሲሾሙ የሰማ ጥሩነህን ቦታ ተክተዋል። ሲሰሩ የነበሩበት የክልሉ ጸጥታ ሃላፊ በመሆን ነበር።
3. ዶ/ር ድረስ ሳህሉ የባህርዳር ከተማ ከንቲባ የነበሩ ሲሆን የስዩም መኮነንን ቦታ በመረከብ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ሆነዋል።
4. ዶ/ር ጋሻው አወቀ የብልጽግና የፓለቲካ ዘርፍ ሃላፊ የነበሩ ሲሆን የዶ/ር ጌታቸው ጀምበርን የምክትል ርዕሰ መስተዳደር ቦታ ተረክበዋል።
5. አቶ ይርጋ ሲሳይ የብልፅግና ፓርቲ በነበሩበት እንዲቀጥሉ ተደርገዋል።
6. ዶ/ር አብዱ ሁሴን በነበሩበት የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ ሆነው እንዲቀጥሉ ተብሏል።
የቀድሞ ባለስልጣናቱ በወጡበት አዲስ አበባ ቀርተዋል። ኮማንድ ፖስቱ መግለጫ ለመስጠት ዛሬ ወይ ነገ ዝግጅቱን ጨርሷል።
ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News pinned a photo
በቁጥጥር ስር ዋሉ

የአማራ ክልል የምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ዮሃንስ ቧያለው ዛሬ ረፋዱን በባህርዳር ከተማ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰምቷል።አቶ ዮሃንስ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት እንደሆነ ተጠቁሟል።
‹‹ በአማራ ክልል በጎንደርና ሸዋ ሮቢት ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጪ ሰላማዊ ሰዎች በፀጥታ ሐይሎች ሰለመገደላቸው ተዓማኒነት ያላቸው መረጃዎች ደርሰውኛል ›› - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ‹‹ በአማራ ክልል፣ ጎንደርና ሸዋሮቢት በርካታ አካባቢዎች ከፍርድ ቤት ትዕዛዘው ውጪ ሰላማዊ ሰዎች በፀጥታ ሀይሎች መገደላቸውን የሚያመላክቱ ተዓማሚነት ያላቸው መረጃዎች ደርሰውኛል ›› ብሏል፡፡ኮሚሽኑ ይህን ያለው ነሐሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም በአማራ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ በላከው ባለአራት ገፅ መግለጫ ላይ ነው፡፡

ኢሰመኮ ተፋላሚ ሀይላት ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ግጭቶችን እንዲያቆሙ፣ ለሰላማዊ ንግግር ስፍራ እንዲያመቻቹና ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡በአማራ ክልል ያለው ግጭት በሰብዓዊ መብቶች ላይ እያሳደረ ያለውን ተፅዕኖ እየተከታተለ መሆኑን የገለፀው ኮሚሽኑ ‹‹ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከመደንገጉ በፊትና በኋላ ከአዲስ አበባና ከሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መረጃዎች እየተቀበልሁ ነው ›› ብሏል፡፡

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ‹‹ ከባድ የመድፍ ተኩስ ጭምር ጥቅም ላይ የዋለባቸው ከፍተኛ ውግያዎች እየተካሄደ መሆናቸውን አረጋግጬያለሁ ›› ያለው ኮሚሽኑ በዚህም ሞት ሰላማዊ ሰዎች እና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን በመግለጫው አመልክቷል፡፡

መግለጫው ሲቀጥል ‹‹ መንገድ ለመዝጋት የሞከሩ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ጭምር መገደላቸውን ›› ይፋ አድርጓል፡፡ ‹‹እስር ቤቶችና ፖሊስ ጣቢያዎች ተሰብረዋል፤ የጦር መሣሪያዎችና ጥይቶች ተዘርፈዋል፤ ቅድመ ፍርድ ያሉ እና ታራሚዎች አመልጠዋል ›› ሲል አመልክቷል፡፡የአማራ ክልል መንግስት አመራሮች የጥቃት ዒላማ መሆናቸውንም በዚሁ መግለጫው ጠቁሟል፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች እንደ ኤሌክትሪክ ሐይል፣ ውሃ፣ ባንክ፣ ሆስፒታል፣ ትምህርት ቤቶች፣ ሰልክ፣ ኢነንተርኔት ያሉ መሠረታዊ አገልገሎቶች መሰተጓገላቸውንም አክሏል፡፡‹‹በደብረ ብርሃን ከተማ ለሁለት ቀናት፣ በአራት ብዙ ህዝብ በሚኖርባቸው አካባቢዎች በተካሄደ ከፍተኛ ውግያ በሆስፒታል፣ ቤተ ከርስቲያን፣ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በስራ ቦታዎች ያሉ ሰለማዊ ሰዎች በመድፍና ተኩስ ልውውጥ ተገድለዋል ›› ባይ ነው፡፡

ኢሰመኮ ‹‹ እንደ ደብረብርሃን፣ ፍኖተ ሰላምና ቡሬ ባሉ ከተሞች ‹ የአየር ድበደባዎች › በመፈፀሙ ሰላማዊ ሰዎች፣ በመኖሪያ ቤቶችና ሕዝብ በሚበዛበቸው ስፍራዎች ጉዳት መድረሱን ›› አመልክቷል፡፡ይህ የኮሚሽኑ መግለጫ ሲቀጥል ‹‹ በባህርዳር ከተማ በርካታ አካባቢዎች ሰላማዊ ሰዎች በየጎዳናውና ከቤታቸው ውጪ ተግደለዋል፤ አንዳንድ ወጣቶችን ደግሞ ለመደብደብና ለመግደል ፍለጋ ሲደረግ እንደነበረ የሚያመላክቱ ተዓማኒ መረጃዎች ደርሰውኛል ›› ሲል ይፋ አድርጓል፡፡

የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቱ በአማራ ክልል ብቻ የተገደበ አለመሆኑን የሚጠቅሰው ኮሚሽኑ ‹‹ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአማራ ተወላጆችን እያሰረ መሆኑን ›› ገልፆል፡፡በርካታ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ያተተው የኮሚሽኑ መግለጫ አምስት ያህል ምክረ ሀሳቦችን ቢደረጉ ሲል በመግለጫው አስቀምጧል፡፡

ከእነዚህም መካከል ‹‹ የፌደራሉ መንግስት የጅምላ እስሩን እንዲያቆም፣ ክህግ አግባብ ውጪ የታሰሩት ሁሉም እንዲፈቱ፣ ኮሚሽኑን ጨምሮ ሌሎች ተቋማት በየእስር ቤቶቹ ጉብኝት ለማድረግ ያልተገደበ መንገድ እንዲመቻችላቸው ›› የጠየቀበት ይገኝበታል፡፡የመንግስት ባለስጣናትን ጨምሮ ተሰመኒነት ያላቸው ግለሰቦች ሰላማዊ መንገዶችን ከመጠቆም ይልቅ ግጭቱን ከሚያጋግሙ መግለጫዎች እንዲቀቆጠቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡ በመጨረሻም በኢትዮጵያ ያሉ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ)፣ የአፍሪካ ህብረት፣ የተባባሩት መንግስታትና ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ግጭቶቹ እንዲቆሙ ድጋፍ እንዲያደርጉ፣ የመነጋገሪያ ስፋራዎችን እንዲያመቻቹ ጠይቋል፡፡
Via: Asham
የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ እና ሰብአዊ መብቶች

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. በሚኒስትሮች ምክር ቤት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 ላይ ያዘጋጀውን ባለ 26 ገጽ የሰብአዊ መብቶች ትንታኔ እና ዝርዝር ምክረ ሐሳቦች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መላኩን አስታወቀ፡፡

በመጪው ሰኞ ነሐሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዋጁ ላይ ለመምከርና ለመወሰን አስቸኳይ ስብሰባ የጠራው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኮሚሽኑን ምክረ ሐሳቦች በጥንቃቄ አጢኖ ተግባራዊ እንዲያደርጋቸው ኮሚሽኑ ጠይቋል፡፡

ኮሚሽኑ ለምክር ቤቱ በላከው የትንታኔ ሰነድ ላይ እንደተመለከተው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ፣ በተለይም በአዋጁ የተመለከቱ ክልከላዎችና ግዴታዎች፣ ለመንግሥት የተሰጠው የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣን፣ የአዋጁ ከባቢያዊና የጊዜ ተፈጻሚነት ወሰን፣ የሕዝብ ተወካዮች እና ዳኞችን ያለምክር ቤቱ ውሳኔ አለመያዝና መከሰስ ልዩ መብት (Immunity) ጨምሮ ሌሎችም ሊገደቡ ስለማይችሉ መብቶች ጥበቃ፤ በአጠቃላይ የአዋጁ እያንዳንዱ አንቀጾች ከጥብቅ አስፈላጊነት (necessity)፣ ተመጣጣኝነት (proportionality) እና ሕጋዊነት (legality) አንጻር አንዲመረመሩ ይጠይቃል፡፡

በተጨማሪም አዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በነበሩት ተከታታይ ቀኖች በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ተከስቶ የነበረው የሰላምና ደህንነት ልዩ አደጋ በአሁኑ ወቅት ተወግዶና መደበኛ እንቅስቃሴዎች ወደ ነበሩበት ሁኔታ መመለስ መጀመራቸው በመንግሥት በይፋ የተገለጸ በመሆኑ፤ ምክር ቤቱ በአሁኑ ወቅት የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣን አስፈላጊነት፣ ከባቢያዊና የጊዜ ተፈጻሚነት ወሰንን በተለይ በጥንቃቄ በማጤን ምክር ቤቱ አዋጁን የሚያጸድቀው ቢሆን የጊዜ ተፈጻሚነቱ ከአንድ ወር ወይም የተወሰኑ ሳምንታት የበለጠ እንዳይሆንና ከባቢያዊ ተፈጻሚነቱም ልዩ አደጋው ተከስቷል በተባለበት ቦታ ብቻ የተገደበ እንጂ በጠቅላላ ሀገሪቱ እንዳይደረግ ኮሚሽኑ ምክረ ሐሳብ አቅርቧል፡፡

ኮሚሽኑ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጁን አስመልክቶ አዋጁ በተነገረበት ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም፣ ባወጣው መግለጫ፣ በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ውስጥም ቢሆን ሰብአዊ መብቶች ሊከበሩ እንደሚገባ አሳስቦ፤ በተለይም ከሚያዝያ ወር 2015 ዓ.ም. በአማራ ክልል እየተባባሰ ለመጣው የትጥቅ ግጭት እና የጸጥታ ችግር ዘላቂ እና ሰላማዊ መፍትሔ የማፈላለግ ጥረት እንዲቀድም ጥሪ ማቅረቡ የሚታወስ ነው። ኮሚሽኑ ከሚያደርገው መደበኛ የሰብአዊ መብቶች ክትትል በተጨማሪም በተለይ በአስቸኳይ ጊዜ ወቅት የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን ክትትል እንዲያደርግ በማቋቋሚያ አዋጁ ሥልጣንና ኃላፊነት የተሰጠው በመሆኑ የአዋጁን አፈጻጸም በሕገ መንግሥቱና ኢትዮጵያ ተቀብላ ባጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶችና በተለይም የጥብቅ አስፈላጊነት፣ በማናቸውም ሁኔታ የማይገደቡ መብቶችን የመጠበቅ፣ የተመጣጣኝነት እና ከመድልዎ ነጻ መሆን መርሖችን ባከበረ መልኩ መተግበራቸውን በመከታተል ላይ ነው።

ኢሰመኮ በተለያዩ ወቅቶች በሀገሪቱ በከፊልም ሆነ በሀገር አቀፍ የተጣሉ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታዎች ክትትል እና ምርመራ አድርጎ፣ ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለሕዝብ ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው። በአዋጅ ቁጥር 6/2015 ላይ የቀረቡ ምክረ ሐሳቦችም በዋነኝነት በእነዚህ የክትትል እና የምርመራ ግኝቶቹ ላይ የተመሠረቱ ሲሆን፣ በተለይም ከእዚህ ቀደም በነበሩ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታዎች ወቅት የተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መድረሳቸውንና ከእነዚህም ውስጥ አሳሳቢ ከነበሩ ጉዳዮች ውስጥ ኢሰብአዊ አያያዞች፣ በተለይም በጥቆማ ላይ የተመሠረቱ እስሮችን በተመለከተ የጥቆማዎቹ መነሻ የሰዎቹ የብሔር ማንነት አለመሆኑን ለማረጋገጥ እና ምክንያታዊ ጥርጣሬ ስለመኖሩ ለማጣራት በቂ ጥረት ያልተደረገባቸው በርካታ እስሮች እንደነበሩ፣ ሴቶች፣ አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች እና በመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ላይ የደረሱ ጥሰቶችን እንደሚጨምር አመላክቷል።

ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትና በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶችና የሰብአዊ መብቶች መርሖች ላይ በመመሥረት ባቀረበው ትንታኔ ላይ ምክር ቤቱ አዋጁን የሚያጸድቀው ቢሆን ለትርጉም አሻሚ የሆኑና ተለጥጠው በመተግበር ተገቢ ላልሆነ አፈጻጸምና የሰብአዊ መብቶች አደጋ ሊሆኑ የሚችሉ ድንጋጌዎች ላይ ሊደረጉ የሚገባቸውን ማሻሻያዎች በዝርዝር በማቅረብ ምክረ ሐሳብ ሰጥቷል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አወጁ ጋር የሚቃረኑ የፍሬ ነገር እና የሥነ ሥርዓት ሕጎች በጅምላ መታገዳቸው እና የዲፕሎማቲክ ልዩ መብቶችን ብቻ ሲቀር ሌሎች ከልዩ ሥራና ኃላፊነት ነጻነትን ከመጠበቅ አስፈላጊነት የሚመነጩ ልዩ መብቶቸንና ጥበቃዎችን (Functional Immunity) ሊታገዱ መቻላቸው ከሚያስከትላቸው ውጤቶች መካከል አንዱ ለምሳሌ የፓርላማ አባላትና የዳኞችን ያለ ምክር ቤቱ ውሳኔ ያለመያዝና ያለመከሰስ መብቶችን ጭምር አላግባብ ለማገድ በር የሚከፍት በመሆኑ ይህም በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ውስጥም ቢሆን ሊታገድ የማይችለውን የዳኝነት ዋስትና እና በነጻነት ላይ የተመሠረተ የፍትሕ አስተዳደርን የሚያግድ፣ እንዲሁም በተለይም በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ውስጥ ሊደረግ የሚገባውን የፓርላማ ክትትል (Parliamentary Oversight) መርሕ ተፈጻሚነት ሊያደናቅፍ የሚችል ነው፡፡

በማናቸውም ጊዜ ብቁ ነጻ እና ገለልተኛ የዳኝነት አካላት እና የፍትሕ ሥርዓት መኖር ለሕጋዊነት እና ለሕግ የበላይነት መርሖች መተግበር የግድ የሚል ነው፡፡ በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታም የዳኝነት ተቋሙ ተግባርና ኃላፊነት በሙሉ ነጻነት ሊቀጥል የሚገባው ሲሆን በተለይም የመንግሥት ኃላፊዎች እና የሕግ አስፈጻሚ አካላት የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣን አጠቃቀም ከአስቸኳይ ጊዜ ሕጉ ጋር የሚስማማ መሆኑንና አለመሆኑን፤ እንዲሁም የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣን አተገባበር አላስፈላጊና ተመጣጣኝ ባልሆነ ሁኔታ በሕገ መንግሥቱና በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሕግጋት የተረጋገጡ መብቶችን የሚጥሱ መሆናቸውን ወይም አለመሆናቸውን በነጻነት መወሰን መቻል ስላለበት፣ እንዲሁም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ ወቅት ክትትል (Parliamentary Oversight) እና የኮሚሽኑ የሰብአዊ መብቶች ክትትል በነጻነት መቀጠል ስላለበት፤ የዳኞችና የምክር ቤት አባሎችን ልዩ መብት ጥበቃ ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ አሳስበዋል፡፡
የዋጋ ንረትን ለማርገብ የሚያስችል የገንዘብ ፖሊሲ ማሻሻያ ሊደረግ ነው
#EBC

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዋጋ ንረትን ለማርገብ የሚያስችል የገንዘብ ፖሊሲ ማሻሻያ ለማድረግ መወሰኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ፡፡

የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የገንዘብ ፖሊሲ ማሻሻያዎችን በተመለከተ የባንኩ ገዥ ማሞ ምህረቱ በሰጡት መግለጫ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እያየለ የመጣውን የዋጋ ንረት ትርጉም ባለው መልኩ ለመቆጣጠር የብሔራዊ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔ ማሳለፉን ተናግረዋል።

የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንና ውሳኔዎቹም ቅንጅታዊ ስራውን እንደሚያግዙ ገልጸው፤ ከውሳኔዎቹ መካከል ለመንግስት የሚሰጠው የቀጥታ ብድር ባለፈው አመት ከተሰጠው ከ1/3ኛ እንዳይበልጥ እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

መንግስት ቅድሚያ የግምጃ ቤት ሰነድ አማራጭን አሟጦ እንዲጠቀምና አማራጭ ሳይኖር ሲቀር ብቻ የቀጥታ ብድር እንደሚጠቀም ተጠቁሟል።

በ2016 ዓ/ም በጀት ዓመት ሰኔ መጨረሻ የሃገር ውስጥ ብድር ዕድገት በ14 በመቶ ጣሪያ እንደሚገደብ ተነግሯል።

በመሆኑም ሁሉም ንግድ ባንኮች የብድር ዕድገት ዕቅዳቸውን በዚህ የብድር ጣሪያ መሰረት እንዲያስተካክሉ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

ባንኮች የገንዘብ እጥረት ሲገጥማቸው ከብሄራዊ ባንክ ከሚወስዱት ብድር የብድር ፋሲሊቲ ላይ የሚከፍሉት ወለድ ከ16 በመቶ ወደ 18 በመቶ ከፍ እንዲል እንደሚደረግም ተነስቷል፡፡

ቁልፍ የሆኑ የወጪ ንግድ ላይ የተሰማሩ ዘርፎች በተለይም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ላኪዎችን ለማበረታታት ከዚህ ቀደም የነበረው የውጭ ምንዛሬ የማስተላለፍ ግዴታ ከ70/30 ወደ 50/50 እንዲሻሻል ይደረጋል ተብሏል።

ላኪዎቹ 50 በመቶውን ለብሄራዊ ባንክ እንዲያስገቡ፣ 10 በመቶውን አብረው ለሚሰሩት ባንክ እንዲሰጡ እና 40 በመቶውን ለራሳቸው እንዲጠቀሙ ተወስኗል።

የዋጋ ንረቱን በመቆጣጠር ረገድም፤ በ2016 በጀት ዓመት መጨረሻ የዋጋ ንረቱ ከ20 በመቶ በታች እንዲሆንና በ2017 በጀት ዓመት ደግሞ ከ10 በመቶ በታች ለማውረድ ይሰራል ብለዋል የብሄራዊ ባንክ ገዥው ማሞ ምህረቱ።

ህብረተሰቡ ውሳኔውን በመደገፍ የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር የሚደረገውን እርምጃ እንዲደግፍም ጥሪ አቅርበዋል።
ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News pinned a GIF
Breaking: Exclusive video shows ENDF special forces entering Gondar city.
በአማራ ክልል ለቀናት በቀጠለው ግጭት በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የሆስፒታል ምንጮች እና ነዋሪዎች ነግረውኛል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

የባሕር ዳር ፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል ሐኪም የሆኑ ግለሰብ ግጭቱ ከጀመረ አንስቶ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች በጥይት ተመትተው ወደ ሆስፒታሉ እንደገቡ ተናግረዋል።

“አሁን በቁጥር ደረጃ የደረሰውን ጉዳት ለመግለጽ ይቸግራል። በርከት ያለ አስክሬን ነው ወደ ሆስፒታሉ እየገባ ያለው” በማለት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የሆስፒታሉ ዶክተር ተናግረዋል።

በርካታ ሰላማዊ ሰዎች የግጭቱ ሰለባ እየሆኑ ነው ያሉት እኝህ ሐኪም፣ ከሆስፒታሉ ውጭ፣ ትናንት አባይ ማዶ አካባቢ በሚገኝ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ሲያስቀድሱ የነበሩ ግለሰብ በተባራሪ ጥይት ተመትተው መመልከታቸውንም ገልጸዋል።

ሌላኛው ለደኅንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ ሌላ የሆስፒታሉ ሐኪም፣ በከተማዋ ግጭቱ ከተከሰተብት ጊዜ ጀምሮ በጥይት ተመትተው ወደ ሆስፒታል የመጡት ሰላማዊ ሰዎች መሆናቸውን ገልጸው፣ ከእነዚህ መካከል በሕክምና ላይ እያሉ ሕይወታቸው ያለፈ እና ሕይወታቸው አልፎ የመጡ እንዳሉ ተናግረዋል።

በከተማዋ የትራንስፖርትም ሆነ የአምቡላንስ አገልግሎት ባለመኖሩ የተጎዱ ሰዎች ወደ ሆስፒታሉ የሚገቡት በቃሬዛ እንደሆነም የሕክምና ባለሙያቹ ጨምረው ተናግረዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በፀጥታው ችግር ምክንያት ደም ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎችም ደም ማጓጓዝ አዳጋች መሁኑ ገልጸዋል ሲል ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል።
ከአማራ ክልል አሁን የተሰሙ ወሳኝ መረጃዎች
  
ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታን በተመለከተ ከሀረሪ ክልል መንግስት የተሰጠ መግለጫ

እንደሚታወቀው በአማራ ክልል በታጠቁ ጽንፈኛ ቡድኖች አማካኝነት እየደረሰ የሚገኘው ጥቃት በክልሉ ሰብዓዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

በክልሉ የታጠቁ ጽንፈኛ ቡድኖች አማካኝነት እየተደረገ የሚገኘው እንቅስቃሴም የሀገር እና ህዝብ ደህንነት ስጋት ከመሆኑም በተጨማሪ በህገመንግስቱ እና በህገመንግስታዊ ስርዓቱ ላይ አደጋ የደቀነ መሆኑን የክልላችን መንግስት በፅኑ ያምናል።

የአማራ ክልል መንግስትና ህዝብ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት ከደረሰው ጉዳት ሳያገግም ለሌላ ጦርነት እና ችግር በመዳረጉ የክልላችን መንግስት ማዘኑን በዚህ አጋጣሚ ይገልጻል።

በአሁኗ ኢትዮጵያ ሁኔታ በትጥቅ ትግል የሚመለስ ጥያቄ አለመኖሩን በመገንዘብ ችግሮችን በነፍጥ ሳይሆን በሰለጠነ መንገድ በመነጋገር መፍታት አስፈላጊ መሆኑን መገንዘብ ይገባል።

የአማራ ሕዝብ መብቶችና ጥቅሞች ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጥቅሞች ጋር የተያያዙ መሆናቸውን በመገንዘብ በሰላማዊ መንገድ ከመታገል ይልቅ የሀይል አማራጭን ለጥያቄዎች መፍቻ መሳሪያ አድርጎ መንቀሳቀስ ህዝቡን ለከፍተኛ ችግር መዳረግ በመሆኑ ፍፁም ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው።

ጽንፈኛው ቡድን ከሰላም ይልቅ ነፍጥ በማንገብ የአንድነታችን አርማ የሆነውን ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት በመተንኩስ እና የሰራዊቱን ስም ማጥፋት ዘመቻ እያካሄደ ይገኛል።

በመሆኑም የክልላችን መንግስት መከላከያ ሰራዊቱን መንካት ሉአላዊነታችንን መዳፈር መሆኑን በጽኑ ያምናል።

የክልላችን ህዝብ እና መንግሥት ከአማራ ክልል ህዝብ ጋር በመሆን የአንድነታችን አርማ የሆነው ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የፀጥታ ሀይሎች እየዳረጉ ከሚገኙ ፅንፈኛ ቡድኖች ነፃ ለማውጣት እየተከናወኑ ባሉ ስራዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ያረጋግጣል።

መላው የክልላችን ህዝብም ይህንን ሀገር አፍራሽ እንቅስቃሴ ለመግታት በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሁሉ የበኩሉ እንዲወጣ በዚህ አጋጣሚ ጥሪውን ያቀርባል።

የሀረሪ ክልላዊ መንግሥት
ነሀሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም
ሐረር
ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ ከሶማሌ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ

የሶማሌ ክልል ህዝብና መንግሥት በተለያዩ ጊዜያት በሀገራችን ህዝቦችና በብሔራዊ ሉዓላዊነታችን ላይ ያጋጠሙትን የጸጥታ መደፍረስ ችግሮች እንዲሁም በሀገር ነጻነት ላይ በውጭ ወራሪዎችና በሀገር ውስጥ ጸረ-ሰላም ኃይሎች የሚሸረቡ የጠላት ሴራዎች ከሀገር ደጀን የሆነውን ከጀግናው መከላከያ ሰራዊትና ከሌሎች ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ደሙንና አጥንቱን የከሰከሰና በብሔራዊ ጥቅማችን የማይደራደር ህዝብ መሆኑን ከማንም ያልተሰወረ ሀቅ ነው።

ይሁን እንጂ ሰሞኑን በአንዳንድ የሀገራችን ክፍሎች ላይ በጸረ-ሰላምና ፅንፈኛ ቡድኖች በተፈጠረው የጸጥታ ችግር በውይይትና በሰለጠነ መንገድ ከመፍታት ይልቅ በማይሳካ ቅዠት ሴረኞች በሸረቡት ሴራ አማካኝነት በዴሞክራሲያዊና በህዝቦች ምርጫ የመጣውን መንግሥት በአፈሙዝ በሁከት እረከባለሁ የሚሉት አካላት በተፈጠረው ችግርና የዜጎች የሰላም እጦት የሶማሊ ክልል መንግስት በጽኑ ያወግዛል።

ከዚህ በተጨማሪም የሶማሌ ክልል ህዝብና መንግሥት የሀገር ደጀን የሆነው መከላከያችን መንካት የሀገርን ሉዓላዊነት መንካት መሆኑንና በሴረኞች የሚሸርበውን እኩይ ተግባር ለአፍታ እንደማይታገስ ከወዲሁ ያሳውቃል።

የሶማሌ ክልል መንግሥት በማንኛውም ሁኔታና ማንኛውም ጊዜ ላይ የኢትዮጵያውያን አንድነት አርማ ከሆነው ከጀግናው መከላከያችን ጎን እንደሚሆን ያምናል።

በሌላ በኩል የአማራ ክልል ህዝብ መብቶችና ጥቅሞች ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጥቅም ጋር የተሳሰረና በአንድነት በመቻቻል ፤በፍቅርና በመከባበር ላይ የተመሰረተ መሆኑን የሶማሌ ክልል ህዝብ ያምናል።

በዚህም በቅርቡ በሰላም የተቋጨው የሰሜኑ ጦርነት ገና ሳናገግም፣ መርህ አልባ በሆነ አካሔድ ላይ በሚገኘው ፅንፈኛ ቡድን ፣ የአማራ ህዝብ ላይ በተሸረበ ሴራ የሰላም መደፍረስና የህይወት ዋጋ ባስከፈለ መልኩ እየሆነ ያለውን ተግባር የሶማሌ ክልላዊ መንግሥትና ህዝብ በፅኑ ያወግዛል።

በመጨረሻም ህዝቡ የሚያነሳው ጥያቄዎች በጋራ በውይይት በመነጋገርና በጠረጴዛ ላይ መፍታት እንጂ ዘመኑን የማይመጥን እሳቤን በነፍጥ የሚመለስ ጥያቄ አለመኖሩንም የክልላችን ህዝብና መንግሥት ያምናል።

የሶማሌ ክልል መንግሥት
ነሀሴ 1/2015 ዓ.ም
ጅግጅጋ
See more posts

View in Telegram

Telegram Channel
TeleSearch Telegram Search