Ministry of Education Ethiopia Telegram Channel

This is Ministry of Education’s Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe

View in Telegram

Recent Posts

የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር በ2015 ዓ.ም ባስተላለፈው ጥሪ መሰረት የእውቅና ጥያቄ አቅርበው መስፈርቱን ለአሟሉ የምርምር ጆርናሎች እውቅና ሰጥቷል። ዝርዝሩ በሚከተለው ደብዳቤ ተገልጿል።
በትምህርት ዘርፉ ውጤታማ ስራ ለመሥራት የተግባባ፣ የጋራ አስተሳሰብ ያለውና የወደፊቱን የተገናዘበ አመራር መስጠት እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለፁ።
--------------------------------------

የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የምክክር መድረክ የትምህርት ሚኒስቴርና የክልል የትምህርት ዘርፉ አመራሮች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

በምክክር መድረኩ የተገኙት ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሀገራችንን የትምህርት ሥርዓት የመምራት እድል እንደተሰጠው አመራር በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ያለውን ውስብስብ ችግር በመረዳት የተቀራረበ አመለካከት በመያዝ አመራር መስጠት ይገባል ብለዋል።

ከዚህ በፊት ትምህርትን እያየን ባለንበት መንገድ መሥራት አንችልም ያሉት ሚኒሰትሩ በረጅም ጊዜ አቅደን ብቁ ተወዳዳሪ እና በስነ-ምግባር የታነፁ ልጆች ለማፍራት የሚያስችል ትምህርት እየሰጠን ነው የሚለውን ማሰብና መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በትምህርት ዘርፍ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሆነ ያነሱት ሚኒስትሩ በዚህ ረገድ የጋራ አስተሳሰብ በአዲስ መልክና ማዕቀፍ መያዝ ይገባል ብለዋል።

አክለውም ከአጭር ጊዜ አስተሳሰብ ወጥተን የሚቀጥለውን ትውልድ በዓለም ተወዳዳሪ፣ ክህሎት ያለው፣ ግብረ ገብነትን የተላበሰ እንዲሆን ለማድረግ የጋራ አስተሳሰብ ይዞ መሄድ እንደሚገባም አሳስበዋል።

አሁን ዓለም ያለችበትን ሁኔታ በመረዳት የተሻለ ብቃትና ክህሎት ያላቸው እንዲሁም በስነ ምግባር የታነፁ ተማሪዎችን ለማፍራት ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል።

በመድረኩም የትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴን ጨምሮ፣ የህዝብ ተወካዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች፣ የሁሉም ክልልና ሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ አብዱራህማን ኢድ ጣሂር ጋር በመሆን ‘Top Gravity’ ከተባለ የህትመት ተቋም ጋር በጋራ ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት የሚከተሉትን ሊንኮች ይጫኑ። https://www.linkedin.com/posts/toppan-gravity-ethiopia_industrialprinting-collaboration-innovation-ugcPost-7185654197235683329-d7XZ?utm_source=share&utm_medium=member_android
እና
https://www.linkedin.com/posts/toppan-gravity_toppan-eih-innovation-activity-7188069238941638656-TVHw?utm_source=share&utm_medium=member_android

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ክቡር ሚኒስትሩ ጃፓን፣ ቶኪዮ በሚገኘው የ ‘Top Gravity ‘ዋና መስሪያ ቤት የስራ ጉብኝት በማድረግ ከተቋሙን ዋና ስራ አስፈጻሚ እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት የሚከተሉትን ሊንኮች ይጫኑ፤
https://www.linkedin.com/posts/ethiopian-investment-holdings_ethiopia-partnership-globalbusiness-ugcPost-7185619860398219264-O1h0?utm_source=share&utm_medium=member_android
እና
https://www.linkedin.com/posts/ethiopian-investment-holdings_commencing-their-networking-and-collaboration-ugcPost-7188069533868261376-IycV?utm_source=share&utm_medium=member_android
ለጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ውጤታማነት አጋር አካላት የድርሻቸውን እንዲውጡ ጥሪ ቀረበ።

ዲቪቪ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ በጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት የ30 ዓመታት ጉዞን የተመለከተ ኮንፈረንስ ተካሂዷል።
-----------------------//--------------------------
በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ ትምህርት ልማትር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሽቴ ሀገራችን መደበኛ ትምህርት ያላገኙ ዜጎችን የመማር መብት ለማረጋገጥና የተማሩ ዜጎችን ቁጥር ለማሳደግ ባለፉት ዓመታት የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ፕሮግራምን በመዘርጋት ውጤታማ ስራ ሰርታለች ብለዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0FxgzBbLxu3iLXRGFnDooGUNoaNN11JeBZGm7pYT5LLr1HaAfkpxQSKyCRssbnh2Ml&id=100064682287722&mibextid=Nif5oz

በድጋፍ የተገኙት የህክምና ቁሳቁሶች የህክምና ዘርፉን የመማር ማስተማር ተግባር ለማሻሻል ለሚደረገው ስራ የላቀ አስተዋፆ እንዳላቸው ተገለፀ፡፡
======================
ሚያዝያ 9/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) የባዮሜዲካል ቴክኒሻኖችንና መሐንዲሶችን ስልጠና ለማሳደግ እና በሆስፒታሎች ውስጥ ያለውን የህክምና አገልግሎት ለማሻሻል በጀርመን የፋይናንስ ትብብር፣ በጀርመን ልማት ባንክ KFW የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል፡፡ ሙሉ ዜናውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፣
https://www.facebook.com/share/p/4azpZTEjtnR4P3VZ/?mibextid=oFDknk

43ኛው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ህብረት መደበኛ ጉባኤ “ጠንካራ የተማሪዎች አደረጃጀት ለተሻለች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት ተካሄደ፡፡
===========================
መጋቢት 16/2016 ዓ.ም (ትሚ) 43ኛው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ህብረት መደበኛ ጉባኤ “ጠንካራ የተማሪዎች አደረጃጀት ለተሻለች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት ተካሂዷል፡፡

ሙሉ ዜናው👇
https://www.facebook.com/share/p/4CyUSuffFwVaKnzr/?mibextid=Nif5oz

የከፍተኛ ትምህርት ፕሬዝዳንቶች ፎረም ተጠናቀቀ

............................................
መጋቢት 8/2016 ዓ.ም (ትሚ) መሪ ቃሉን “ከፍተኛ ትምህርት ከፍ ላለ ተጽዕኖ” (Higher Education for Higher Impacts) ያረገው የከፍተኛ ትምህርት ፕሬዝዳንቶች ፎረም ትናንት ተጠናቀቀ፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሽኔ በፎረሙ ማጠቃለያ ከፍተኛ ትምህርት ላይ እየተተገበሩ ያሉት ቁልፍ የለውጥ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የዘርፉ ሃላፊዎች በትኩረት በመሰራት የድርሻቸውን መወጣት እንደሚገባቸውና የሁሉንም ባለድርሻዎች የላቀ ተሳትፎ እንደሚጠይቅ አሳስበዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ጨምሮ ከመላው የሃገራችን ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዚደንቶችና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች አንዲሁም ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት ፎረም በተጀመሩ የለውጥ መርሃ-ግብሮች አተገባበር፣የለውጥ ስኬቶችና ባጋጠሙ ተግዳሮቶች ዙሪያ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ጥልቅ ውይይት ሲያደርግ የቆየ ሲሆን የቀጣይ ስራ አቅጣጫዎች ላይ በመምከር ተጠናቋል፡፡

በዕለቱ በጅማ ዩኒቨርስቲ (@ Jimma University ) የተዘጋጀ አውደርዕይ፣ የዲጂታል ትምህርት ስቱዲዮና Ict መረጃ ማዕከል እንዲሁም ሌሎች ካምፓሶች በፎረሙ ተሳታፊዎች ተኀብኝተዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ!

See more posts

View in Telegram

Telegram Channel
TeleSearch Telegram Search