Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ Telegram Channel

አል-አይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው፡

View in Telegram

Recent Posts

የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ተከታይ “ኤጂአይ” ምንድን ነው?

ኦፕንኤአይ “ጂፒቲ - 4”ን የሚተካና የሰው ልጆች የሚከውኑትን ማንኛውም ስራ የሚሰራ ቴክኖሎጂ ማሰልጠን መጀመሩን አስታውቋል።

https://bit.ly/3URFxic
በሱዳን ኤል ፋሽር እየተከናወነ በሚገኝው ከፍተኛ ወግያ የሟቾች ቁጥር 134 መሻገሩ ተሰማ

በሁለቱ ጄነራሎች መካከል በሰሜናዊ ዳርፉር ዋና ከተማ ኤል ፋሽር ጠንከር ያለ ውግያ እየተደረገ ነው።
https://bit.ly/4e99tzs
በሰርጓ እለት ከስራ መሰናበቷን የሚገልጽ መልዕክት የደረሳት ብሪታንያዊቷ

ሙሽሪት በህይወቷ ትልቅ ቦታ የሰጠችውን እለት ወደሀዘን የለወጠ መልዕክት ከሃላፊዋ ተልኮላታል።

https://bit.ly/3VslNUd
በካንሰር ምክንያት ህይወታቸውን ከሚያጡ ሰዎች አንድ ሶስተኛው ሴቶች መሆናቸው ተገለጸ

በአፍሪካ ከ60-70 በመቶ ያሉ ሴቶች ምርመራ የሚያደርጉት ካንሰሩ በሰውነታቸው ውስጥ ከተሰራጨ በኋላ ነው ተብሏል።
https://bit.ly/3Kjxx4P
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ግብ በማስቆጠር ሁለት አዳዲስ ክብረወሰኖችን ሰበረ

ሮናልዶ በ4 ሊጎች ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን የዓለማችን የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል። የ39 ዓመቱ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግር ኳስ ዘመኑ ያስቆጠራቸው ግቦች 893 ደርሰዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4bCEBWg
ኢራን የኒዩክሌር መሳሪያ ለመስራት በተቃረበ ደረጃ ዩራኒየም እያበለጸገች ነው ተባለ

የበለጸገ ዩራኒየም ክምችቷ ሶስት አቶሚክ ቦምቦችን መስራት እንደሚያስችልም ነው ለአለማቀፉ አቶሚክ ሃይል ኤጀንሲ የቀረበ ሪፖርት የሚያሳየው።

https://bit.ly/4bVre3b
ታጣቂ ኃይሎችን አግኝቶ ለማናገር ሙከራ መጀመሩን ምክክር ኮሚሽኑ ገለጸ

በግጭቱ ውስጥ ያሉ የታጠቁ ኃይሎች መሳተፋቸው አለመረጋገጡ እና በሀገሪቱ በተለያዩ ማዕዘናት ያሉ ግጭቶች በምክክሩ ውጤታማነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራሉ የሚሉ ስጋቶችን ፈጥሯል።
አል ዐይን አማርኛ በጉዳዩ ዙሪያ ኮሚሽንኑን አነጋግራል።
https://bit.ly/3WZBsLU
የሰሜን ኮሪያን ሁለተኛ የስለላ ሳተላይት ለማምጠቅ የተወነጨፈችው ሮኬት ፈነዳች

ፒዮንግያንግ ሙከራውን ያደረገችው ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን በሴኡል የሶስትዮሽ ምክክር ማድረግ በጀመሩበት ወቅት ነው።

https://bit.ly/4dYo2FN
የኤምሬትስ እና ደቡብ ኮሪያ ስትራቴጂካዊ ትብብር

የአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ለሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ሴኡል ገብተዋል።

በፈረንጆቹ በ1980 ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት ኤምሬትስ እና ደቡብ ኮሪያ፥ በ2009 የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ወደ ስትራቴጂካዊ ትብብር አሳድገዋል።

ስለሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነትና የፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ጉብኝት ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://bit.ly/4bzQqwu
የኤምሬትስ እና ደቡብ ኮሪያ ስትራቴጂካዊ ትብብር

የአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ለሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ሴኡል ገብተዋል።

በፈረንጆቹ በ1980 ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት ኤምሬትስ እና ደቡብ ኮሪያ፥ በ2009 የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ወደ ስትራቴጂካዊ ትብብር አሳድገዋል።

ስለሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነትና የፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ጉብኝት ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://bit.ly/4bzQqwu
ኔታንያሁ የራፋው ጥቃት በአሳዛኝ ሁኔታ በስህተት የተፈጸሙ ነው አሉ

እስራኤል በራፋ በመጠለያ ድንኳን ላይ ባደረሰችው የአየር ጥቃት ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 45 ሰዎች ተገድለዋል ተብሏል።
ይህ ጥቃት በእስራኤል ላይ ከፍተኛ ውግዘትን አስከትሎባታል።
https://bit.ly/451M12H
የአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በደቡብ ኮሪያ ገቡ

ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በሴዑል የሁለት ቀናት ጉብኝት ደርጋሉ። ፕሬዝዳንቱ ይፋዊ ጉብኝቱን የሚያደርጉት በደቡብ ኮሪያ አቻቸው ዮን ሱክ የል በተደረገላቸው ግብዣ ነው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4bzQqwu
ግጭቶችና ጦርነቶች በአለም አቀፍ ደረጃ አዳዲስ በሽታዎች እንዲከሰቱ ምክንያት መሆናቸውን የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ተናገሩ።

ዋና ጸሀፊው በ2024 ብቻ በደንጌ፣ ኮሌራና ሌሎች በሽታዎች ተይዘው ክትባት የሚሹ 20 ሚሊየን ህጻናት መኖራቸውን ይፋ አድርገዋል።

በጋዛ እና ሱዳን ሚሊየኖች በጥይት ብቻ ሳይሆን መታከም ባልቻሉ በሽታዎችና በምግብ እጥረት ህይወታቸው አደጋ ላይ እንደሚገኝም ነው ያነሱት።

በጤና ተቋማት ላይ የሚደረሰው ጉዳት መጠን በሀላፊነት ዘመኔ አይቸው የማላውቀው ነው ያሉት የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ የፊታችን ሀሙስ የሚጀመረው የአለም ጤና ጉባኤ ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠውም አሳስበዋል።

ቀጣዩን ሊንክ በመጫን ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡ፦ https://bit.ly/44XwUaC
በፈረንሳይ አግዴ የተሰኘችው የባህር ዳርቻ ከተማ ከንቲባ በጠንቋይ ተታሎ የህዝብ ሀብትን አባክኗል በሚል በቁጥጥር ስር ውሏል።

ጊሌ ኢሮር የተባለው ከንቲባ ከዓመታት በፊት በሞት የተለየውን ወላጅ አባቱን አናግራለው ከምትል ጠንቋይ ጋር ግንኙነት ነበረው ተብሏል።

በጥንቆላ የምትተዳደረው እንስት "አባትህ እንዲህ ብሏል፤ እንዲህ አድርግ" እያለች የምትነግረውን ሁሉ ሲፈጽም እንደነበርም ነው የተገለጸው።

ከንቲባው ጠንቋዩዋ ለሰራችው ውለታ ወደ ታይላንድ እንድትዝናና ወጪዋን በመሸፈን መላኩ የተነገረ ሲሆን፥ ዘመዶቿን ስራ ማስቀጠሩንና ሌሎች ስጦታዎችን ማበርከቱንም ፖሊስ አስታውቋል።

ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡ፦ https://bit.ly/44WvvB2
ብሪታንያ 18 ዓመት የሞላቸው ዜጎች በብሔራዊ ውትድር እንዲያገለግሉ ልታስገድድ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሽ ሱናክ 18 አመት የሞላቸው ወጣቶች በብሔራዊ ውትድርና ለአንድ አመት እንዲያገለግሉ የሚያስገድድ ፖሊሲ አስተዋውቀዋል።

በፖሊሲው ለወጣቶች ሁለት አማራጮች ቀርበዋል፤ በብሔራዊ ውትድርና ማገለገል ወይንም ለአንድ አመት በየወሩ የሰባት ቀናት ማህበራዊ አገልግሎት መስጠት።

በአመት 2.5 ቢሊየን ፓውንድ ያስወጣል የተባለው ፖሊሲ ተቃውሞዎችም እያስተናገደ ነው።

አዲሱ የብሄራዊ ውትድርና ፖሊሲ ምን ምን አካቷል? ቀጣዩን ሊንክ ተጭነው ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://bit.ly/3UZh8Yd
እስራኤል በራፋህ የፈጸመችው የአየር ጥቃት የበርካታ ንጹሃንን ህይወት መቅጠፉ አለም አቀፍ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡

ከጦርነት ነጻ በተባለው የከተማዋ ክፍል የተፈጸመው የአየር ጥቃት ተፈናቃዮች በተጠለሉባቸው ድንኳኖች ላይ ቃጠሎ አስነስቶ ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ የ45 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

ይህን ተከትሎ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን ጨምሮ የተለያዩ የአለም ሀገራት መሪዎች አለም አቀፉ ፍርድ ቤት እስራኤል ጦርነቱን እንድታቆም ትዕዛዝ እንዲያወጣ ጠይቀዋል፡፡

የእስራኤል ጦር በበኩሉ የእሁዱ የአየር ጥቃት በተጠና መረጃ የተመረኮዘና በሀማስ ታጣቂዎች ላይ ያነጣጠረ ነው ሲል ወቀሳውን አስተባብሏል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡ፦ https://bit.ly/4510psa
ቻይና ከአረብ ሀገራት መሪዎች ጋር በእስራኤል እና ፍልስጤም ጉዳይ ልትመክር ነው።

የአረብ ኢምሬትስ፣ ባህሬን፣ ቱኒዚያ እና ግብጽ መሪዎች በጋዛ ወቅታዊ ጉዳይ ከቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር በቤጂንግ እንደሚወያዩ ተገልጿል።

ሀገራቱ ከስብሰባው መጠናቀቅ በኋላም በእስራኤል እና ፍልስጤም ጉዳይ የጋራ አቋም እንደሚያወጡ ይጠበቃል።

በሀማስ እና በእስራኤል መካከል የአሸማጋይነት ሚና እንዲኖራት የምትፈልገው ቤጂንግ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ከአረቡ አለም ጋር ጠንካራ ወዳጅነትን ለመፍጠር እየሞከረች ትገኛለች።

የቤጂንግን የአሸማጋይነት ጥረት በዝርዝር ያንብቡ፦ https://bit.ly/3yAEX1b

View in Telegram

Telegram Channel