Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ Telegram Channel

ይህ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የቴሌግራም ገጽ ነው። የዩኒቨርሲቲያችን ወቅታዊ መረጃዎች፣ ልዩ ልዩ ሁነቶች እና የስራ እና የትምህርት ማስታወቂያዎች ይተላለፉበታል። አሁንኑ ቤተሰብ ለመሆን ይቀላቀሉ!!
This is Our Official Telegram Channel. We Provide up-to-date Information about our University.
Join Us Now!🙏

View in Telegram

Recent Posts

#የስራ_ኃላፊነት_ውድድር_ማስታወቂያ!
የደብረማርቆስ ዩንቨርስቲ ስፖርት ሳይንስ አካዳሚ

የ2016 ዓ/ም የስፖርት ሳይንስ አካዳሚያችን
የስልጠና ሰዓታት ፦
ጠዋት ከ1:00 - 2:00
ከሰዓት ከ10:30-11:30 ሲሆን ከስልጠናው በተጨማሪ የአካል ብቃትና ጤና የማማከሪያ ማዕከል ስራ ስለጀመረ ማንኛውም የግቢና የአካባቢ ማህበረሰብ
መጠቀም የምትችሉ መሆኑን በደስታ እናሳወቃለን።

ከግቢ ውጭ ተሽከርካሪ ይዛችሁ የምትመጡ የጅም ደንበኞቻችን ተሽከርካሪዎቻችሁን ከግቢ በር አካባቢ ማቆም ይጠብቅባችኋል።

ጅማችን ከሚያዚያ 1/08/2016ዓ፡ም ጀምሮ
አግልግሎት ይሰጣል።

===============

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የእውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ!

ለተጨማሪ እና አዳዲስ መረጃዎች
👇👇
#ቴሌግራም፡ https://bit.ly/3HbDPCB
#ፌስቡክ፡ https://bit.ly/3mYfnNW
#ዩቱዩብ፡ https://bit.ly/3L73hu3
#ዌብሳይትwww.dmu.edu.et
በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ዓይነስውራንን በቴክኖሎጅ ተጠቃሚ የሚያደርግ የኮምፒውተር ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

<><<<><><><><><>

ደ.ማ.ዩ ፡- | መጋቢት 21/2016 ዓ.ም | ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት| የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አካል ጉዳተኞች ማዕከል  አይነስውር ተማሪዎችን ዓለም ከደረሰበት የቴክኖሎጅ ደረጃ በማድረስ  እኩል ተጠቃሚ ለማድረግ JAWS(Job Access with Speech) በተሰኘ ሶፍትዌር  የኮምፒውተር ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚደንት እንዲሁም የነርቸር ፕሮጀክት አስተባባሪ አስካለ ማርያም አዳሙ (ዶ/ር) በስልጠናው 67 የሚደርሱ 1ኛ ዓመት ዓይነስውር ተማሪዎች በ3 ዙር እንደሚሳተፉ በመግለፅ   ዓይነ ስውር ተማሪዎችን ከገንዘብ እርዳታ ይልቅ በዲጂታል ቴክኖሎጅ ተጠቃሚ በማድረግ ከሰዎች ጥገኝነት ተላቅቀው ስራ ፈጣሪና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል ያለመ ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት በባሶ ሊበን ወረዳ የሶሺዮ-ኢኮኖሚ ባለሙያ አቶ አክሎክ ይሄይስ እንደገለፁት ስልጠናው (JAWS) የተሰኘውን ሶፈትዌር በመጠቀም ዓነስውር ተማሪዎች  በኮምፒውተር ላይ  እንዴት መፃፍና ማንበብ እንደሚችሉ እንዲሁም የተለያዩ መረጃዎችን ፈልገው ለማግኘት የሚያስችላቸውን እውቀት የሚያገኙበትና ባጠቃላይ ሁሉንም መሰረታዊ የኮምፒውተር ክህሎት ማግኘት የሚችሉበትና ዘመኑ ከደረሰበት የቴክኖሎጅ ደረጃ በመድረስ እኩል ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

===============

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የእውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ!

ለተጨማሪ እና አዳዲስ መረጃዎች
👇👇

#ቴሌግራም፡ https://bit.ly/3HbDPCB

#ፌስቡክ፡ https://bit.ly/3mYfnNW

#ዩቱዩብ፡ https://bit.ly/3L73hu3

#ዌብሳይትwww.dmu.edu.et

View in Telegram

Telegram Channel